ኦሪት ዘፍጥረት Orit ZeFiTret
Genesis / Bereisheit #25
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

ኦሪት ዘፍጥረት 25

Genesis 25

1 አብርሃምም ደግሞ ስምዋ ኬጡራ የተባለች ሚስት አገባ።

1 Then again Abraham took a wife, and her name was Keturah.

2 እርስዋም ዘምራንን፥ ዮቅሳንን፥ ሜዳንን፥ ምድያምን፥ የስቦቅን፥ ስዌሕን ወለደችለት።

2 And she bare him Zimran, and Jokshan, and Medan, and Midian, and Ishbak, and Shuah.

3 ዮቅሳንም ሳባንና ድዳንን ወለደ። የድዳንም ልጆች አሦርያውያን፥ ለጡሳውያን፥ ለኡማውያን ናቸው።

3 And Jokshan begat Sheba, and Dedan. And the sons of Dedan were Asshurim, and Letushim, and Leummim.

4 የምድያምም ልጆች ጌፌር፥ ዔፌር፥ ሄኖኅ፥ አቢዳዕ፥ ኤልዳዓ ናቸው። እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ልጆች ናቸው።

4 And the sons of Midian; Ephah, and Epher, and Hanoch, and Abida, and Eldaah. All these were the children of Keturah.

5 አብርሃምም የነበረውን ሁሉ ለይስሐቅ ሰጠው

5 And Abraham gave all that he had unto Isaac.

6 የአብርሃምም ለነበሩ ለቁባቶቹ ልጆች አብርሃም ስጦታን ሰጣቸው እርሱም ገና በሕይወቱ ሳለ ከልጁ ከይስሐቅ ለይቶ ወደ ፀሐይ መውጫ ወደ ምሥራቅ አገር ሰደዳቸው።

6 But unto the sons of the concubines, which Abraham had, Abraham gave gifts, and sent them away from Isaac his son, while he yet lived, eastward, unto the east country.

7 አብርሃምም የኖረበት የዕድሜው ዓመታት እነዚህ ናቸው መቶ ሰባ አምስት ዓመት ኖረ።

7 And these are the days of the years of Abraham’s life which he lived, an hundred threescore and fifteen years.

8 አብርሃምም ነፍሱን ሰጠ፥ በመልካም ሽምግልናም ሞተ ሸመገለም፥ ብዙ ዘመንም ጠገበ ወደ ወገኖቹም ተከማቸ።

8 Then Abraham gave up the ghost, and died in a good old age, an old man, and full of years; and was gathered to his people.

9 ልጆቹ ይስሐቅና እስማኤልም በመምሬ ፊት ለፊት ባለው በኬጢያዊ በሰዓር ልጅ በኤፍሮን እርሻ ላይ ባለ ድርብ ክፍል በሆነው ዋሻ ውስጥ ቀበሩት።

9 And his sons Isaac and Ishmael buried him in the cave of Machpelah, in the field of Ephron the son of Zohar the Hittite, which is before Mamre;

10 አብርሃም ከኬጢ ልጆች የገዛው እርሻ ይህ ነው አብርሃምና ሚስቱ ሣራ ከዚያ ተቀበሩ።

10 The field which Abraham purchased of the sons of Heth: there was Abraham buried, and Sarah his wife.

11 አብርሃምም ከሞተ በኋላ እግዚአብሔር ልጁን ይስሐቅን ባረከው ይስሐቅም ብኤርለሃይሮኢ ተብሎ በሚጠራው ምንጭ አጠገብ ኖረ።

11 And it came to pass after the death of Abraham, that God blessed his son Isaac; and Isaac dwelt by the well Lahai–roi.

12 የሣራ ባሪያ ግብፃዊቱ አጋር ለአብርሃም የወለደችው የአብርሃም ልጅ የእስማኤል ትውልድ ይህ ነው

12 Now these are the generations of Ishmael, Abraham’s son, whom Hagar the Egyptian, Sarah’s handmaid, bare unto Abraham:

13 የእስማኤልም የልጆቹ ስም በየስማቸውና በየትውልዳቸው እንዲህ ነው የእስማኤል የበኵር ልጁ

13 And these are the names of the sons of Ishmael, by their names, according to their generations: the firstborn of Ishmael, Nebajoth; and Kedar, and Adbeel, and Mibsam,

14 ነባዮት፥ ቄዳር፥ ነብዳኤል፥ መብሳም፥ ማስማዕ፥

14 And Mishma, and Dumah, and Massa,

15 ዱማ፥ ማሣ፥ ኩዳን፥ ቴማን፥ ኢጡር፥ ናፌስ፥ ቄድማ።

15 Hadar, and Tema, Jetur, Naphish, and Kedemah:

16 የእስማኤል ልጆች እነዚህ ናቸው፥ ስማቸውም በየመንደራቸውና በየሰፈራቸው ይኸው ነው በየወገናቸውም አሥራ ሁለት አለቆች ናቸው።

16 These are the sons of Ishmael, and these are their names, by their towns, and by their castles; twelve princes according to their nations.

17 እስማኤልም የኖረበት የዕድሜው ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው ነፍሱን ሰጠ ሞተም ወደ ወገኖቹም ተከማቸ።

17 And these are the years of the life of Ishmael, an hundred and thirty and seven years: and he gave up the ghost and died; and was gathered unto his people.

18 መኖሪያቸውም ከኤውላጥ አንሥቶ በግብፅ ፊት ለፊት እስከምትገኝ እስከ ሱር ድረስ ወደ አሦር በምትወስደው መንገድ ላይ ነበረ እንዲህም በወንድሞቹ ሁሉ ፊት ተቀመጠ።

18 And they dwelt from Havilah unto Shur, that is before Egypt, as thou goest toward Assyria: and he died in the presence of all his brethren.

19 የአብርሃም ልጅ የይስሐቅ ትውልድም ይህ ነው አብርሃም ይስሐቅን ወለደ

19 And these are the generations of Isaac, Abraham’s son: Abraham begat Isaac:

20 ይስሐቅም አርባ ዓመት ሲሆነው ርብቃን አገባ እርስዋም በሁለት ወንዞች መካከል ያለ የሶርያዊው የባቱኤል ልጅና የሶርያዊው የላባ እኅት ናት።

20 And Isaac was forty years old when he took Rebekah to wife, the daughter of Bethuel the Syrian of Padan–aram, the sister to Laban the Syrian.

21 ይስሐቅም ስለሚስቱ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፥ መካን ነበረችና እግዚአብሔርም ተለመነው፥ ርብቃም ሚስቱ ፀነሰች።

21 And Isaac intreated the Lord for his wife, because she was barren: and the Lord was intreated of him, and Rebekah his wife conceived.

22 ልጆችም በሆድዋ ውስጥ ይገፋፉ ነበር እርስዋም፦ እንዲህ ከሆነ ይህ ለእኔ ምኔ ነው? አለች። ከእግዚአብሔርም ትጠይቅ ዘንድ ሄደች።

22 And the children struggled together within her; and she said, If it be so, why am I thus? And she went to enquire of the Lord.

23 እግዚአብሔርም አላት፦ ሁለት ወገኖች በማኅፀንሽ ናቸው፥ ሁለቱም ሕዝብ ከሆድሽ ይከፈላሉ ሕዝብም ከሕዝብ ይበረታል ታላቁም ለታናሹ ይገዛል።

23 And the Lord said unto her, Two nations are in thy womb, and two manner of people shall be separated from thy bowels; and the one people shall be stronger than the other people; and the elder shall serve the younger.

24 ትወልድ ዘንድ ዘመንዋ በተፈጸመ ጊዜም፥ እነሆ፥ በማኅፀንዋ መንታ ነበሩ።

24 And when her days to be delivered were fulfilled, behold, there were twins in her womb.

25 በፊትም የወጣው ቀይ ነበረ፥ ሁለንተናውም ጠጕር ለብሶ ነበር ስሙም ዔሳው ተባለ።

25 And the first came out red, all over like an hairy garment; and they called his name Esau.

26 ከዚያም በኋላ ወንድሙ ወጣ፥ በእጁም የዔሳውን ተረከዝ ይዞ ነበር ስሙም ያዕቆብ ተባለ። እርስዋ ልጆችን በወለደቻቸው ጊዜ ይስሐቅ ስድሳ ዓመት ሆኖት ነበር።

26 And after that came his brother out, and his hand took hold on Esau’s heel; and his name was called Jacob: and Isaac was threescore years old when she bare them.

27 ብላቴኖቹም አደጉ ዔሳውም አደን የሚያውቅ የበረሃ ሰው ሆነ ያዕቆብ ግን ጭምት ሰው ነበረ፥ በድንኳንም ይቀመጥ ነበር።

27 And the boys grew: and Esau was a cunning hunter, a man of the field; and Jacob was a plain man, dwelling in tents.

28 ይስሐቅም ዔሳውን ይወድ ነበር፥ ካደነው ይበላ ነበርና ርብቃ ግን ያዕቆብን ትወድ ነበረች።

28 And Isaac loved Esau, because he did eat of his venison: but Rebekah loved Jacob.

29 ያዕቆብም ወጥ ሠራ ዔሳውም ደክሞ ከበረሃ ገባ

29 And Jacob sod pottage: and Esau came from the field, and he was faint:

30 ዔሳውም ያዕቆብን፦ ከዚህ ከቀዩ ወጥ አብላኝ፥ እኔ እጅግ ደክሜአለሁና አለው ስለዚህ ስሙ ኤዶም ተባለ።

30 And Esau said to Jacob, Feed me, I pray thee, with that same red pottage; for I am faint: therefore was his name called Edom.

31 ያዕቆብም፦ በመጀመሪያ ብኵርናህን ሽጥልኝ አለው።

31 And Jacob said, Sell me this day thy birthright.

32 ዔሳውም፦ እነሆ፥ እኔ ልሞት ነኝ ይህች ብኵርና ለምኔ ናት? አለ።

32 And Esau said, Behold, I am at the point to die: and what profit shall this birthright do to me?

33 ያዕቆብም፦ እስኪ በመጀመሪያ ማልልኝ አለው። ማለለትም ብኵርናውንም ለያዕቆብ ሸጠ።

33 And Jacob said, Swear to me this day; and he sware unto him: and he sold his birthright unto Jacob.

34 ያዕቆብም ለዔሳው እንጀራና የምስር ወጥ ሰጠው በላ፥ ጠጣ፥ ተነሥቶም ሄደ እንዲሁም ዔሳው ብኵርናውን አቃለላት።

34 Then Jacob gave Esau bread and pottage of lentiles; and he did eat and drink, and rose up, and went his way: thus Esau despised his birthright.