ኦሪት ዘፍጥረት Orit ZeFiTret
Genesis / Bereisheit #50
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

ኦሪት ዘፍጥረት 50

Genesis 50

1 ዮሴፍም በአባቱ ፊት ወደቀ፥ በእርሱም ላይ አለቀሰ፥ ሳመውም።

1 And Joseph fell upon his father’s face, and wept upon him, and kissed him.

2 ዮሴፍም ባለመድኃኒቶች አገልጋዮቹ አባቱን በሽቱ ያሹት ዘንድ አዘዘ ባለመድኃኒቶችም እስራኤልን በሽቱ አሹት።

2 And Joseph commanded his servants the physicians to embalm his father: and the physicians embalmed Israel.

3 አርባ ቀንም ፈጸሙለት የሽቱ መደረጊያው ወራት እንደዚሁ ይፈጸማልና የግብፅም ሰዎች ሰባ ቀን አለቀሱለት።

3 And forty days were fulfilled for him; for so are fulfilled the days of those which are embalmed: and the Egyptians mourned for him threescore and ten days.

4 የልቅሶውም ወራት ባለፈ ጊዜ ዮሴፍ ለፈርዖን ቤተ ሰቦች እንዲህ ብሎ ተናገረ። እኔ በፊታችሁ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆንሁ ለፈርዖን እንዲህ ብላችሁ ንገሩት።

4 And when the days of his mourning were past, Joseph spake unto the house of Pharaoh, saying, If now I have found grace in your eyes, speak, I pray you, in the ears of Pharaoh, saying,

5 አባቴ አምሎኛል እንዲህ ሲል፦ እነሆ እኔ እሞታለሁ በቈፈርሁት መቃብር በከነዓን ምድር ከዚያ ቅበረኝ። አሁንም ወጥቼ አባቴን ልቅበርና ልመለስ።

5 My father made me swear, saying, Lo, I die: in my grave which I have digged for me in the land of Canaan, there shalt thou bury me. Now therefore let me go up, I pray thee, and bury my father, and I will come again.

6 ፈርዖንም። ውጣ፥ አባትህንም እንዳማለህ ቅበረው አለው።

6 And Pharaoh said, Go up, and bury thy father, according as he made thee swear.

7 ዮሴፍም አባቱን ሊቀብር ወጣ የፈርዖን ሎላልትም ሁሉ ከእርሱ ጋር ወጡ፥ የቤቱ ሽማግሌዎችም የግብፅ ምድር ሽማግሌዎችም ሁሉ

7 And Joseph went up to bury his father: and with him went up all the servants of Pharaoh, the elders of his house, and all the elders of the land of Egypt,

8 የዮሴፍም ቤተ ሰቦች ሁሉ ወንድሞቹም የአባቱም ቤተ ሰቦች ወጡ ልጆቻቸውንና በጎቻቸውን ከብቶቻቸውን ብቻ በጌሤም ተዉ።

8 And all the house of Joseph, and his brethren, and his father’s house: only their little ones, and their flocks, and their herds, they left in the land of Goshen.

9 ሰረገሎችም ፈረሰኞችም ከእርሱ ጋር ወጡ፥ ሠራዊቱም እጅግ ብዙ ነበረ።

9 And there went up with him both chariots and horsemen: and it was a very great company.

10 በዮርዳኖስ ማዶ ወዳለችው ወደ አጣድ አውድማ መጡ፥ እጅግ ታላቅ በሆነ በጽኑ ልቅሶም አለቀሱለት ለአባቱም ሰባት ቀን ልቅሶ አደረገለት።

10 And they came to the threshingfloor of Atad, which is beyond Jordan, and there they mourned with a great and very sore lamentation: and he made a mourning for his father seven days.

11 በዚያች ምድር የሚኖሩ የከነዓን ሰዎችም በአጣድ አውድማ የሆነውን ልቅሶ ባዩ ጊዜ። ይህ ለግብፅ ሰዎች ታላቅ ልቅሶ ነው አሉ ስለዚህም የዚያን ቦታ ስም አቤል ምጽራይም ብለው ጠሩት እርሱም በዮርዳኖስ ማዶ ነው።

11 And when the inhabitants of the land, the Canaanites, saw the mourning in the floor of Atad, they said, This is a grievous mourning to the Egyptians: wherefore the name of it was called Abel–mizraim, which is beyond Jordan.

12 ልጆቹም እንዳዘዛቸው እንደዚያው አደረጉለት

12 And his sons did unto him according as he commanded them:

13 ልጆቹም ወደ ከነዓን ምድር አጓዙት፥ ባለ ሁለት ክፍል በሆነች ዋሻም ቀበሩት እርስዋም በመምሬ ፊት ያለች፥ አብርሃም ለመቃብር ርስት ከኬጢያዊ ከኤፍሮን ከእርሻው ጋር የገዛት ዋሻ ናት።

13 For his sons carried him into the land of Canaan, and buried him in the cave of the field of Machpelah, which Abraham bought with the field for a possession of a buryingplace of Ephron the Hittite, before Mamre.

14 ዮሴፍና ወንድሞቹ አባቱንም ሊቀብሩ ከእርሱ ጋር የወጡት ሰዎች ሁሉ አባቱን ከቀበረ በኋላ ወደ ግብፅ ተመለሱ።

14 And Joseph returned into Egypt, he, and his brethren, and all that went up with him to bury his father, after he had buried his father.

15 የዮሴፍም ወንድሞች አባታቸው እንደ ሞተ ባዩ ጊዜ እንዲህ አሉ። ምናልባት ዮሴፍ ይጠላን ይሆናል፥ ባደረግንበትም ክፋት ሁሉ ብድራት ይመልስብን ይሆናል።

15 And when Joseph’s brethren saw that their father was dead, they said, Joseph will peradventure hate us, and will certainly requite us all the evil which we did unto him.

16 ወደ ዮሴፍም መልእክት ላኩ እንዲህም አሉት፦ አባትህ ገና ሳይሞት እንዲህ ብሎ አዝዞአል።

16 And they sent a messenger unto Joseph, saying, Thy father did command before he died, saying,

17 ዮሴፍን እንዲህ በሉት። እባክህ የወንድሞችህን በደል ኃጢአታቸውንም ይቅር በል፥ እነርሱ በአንተ ከፍተውብሃልና አሁንም እባክህ የአባትህ አምላክ ባሪያዎች የበደሉህን ይቅር በል።

17 So shall ye say unto Joseph, Forgive, I pray thee now, the trespass of thy brethren, and their sin; for they did unto thee evil: and now, we pray thee, forgive the trespass of the servants of the God of thy father. And Joseph wept when they spake unto him.

18 ዮሴፍም ይህን ሲሉት አለቀሰ። ወንድሞቹ ደግሞ መጡ በፊቱም ሰግደው። እነሆ እኛ ለአንተ ባሪያዎችህ ነን አሉት።

18 And his brethren also went and fell down before his face; and they said, Behold, we be thy servants.

19 ዮሴፍም አላቸው። አትፍሩ እኔ በእግዚአብሔር ፋንታ ነኝን?

19 And Joseph said unto them, Fear not: for am I in the place of God?

20 እናንተ ክፉ ነገርን አሰባችሁብኝ እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እንዲድን ለማድረግ ለመልካም አሰበው።

20 But as for you, ye thought evil against me; but God meant it unto good, to bring to pass, as it is this day, to save much people alive.

21 አሁንም አትፍሩ እኔ እናንተንና ልጆቻችሁን እመግባችኋለሁ። አጽናናቸውም ደስ አሰኛቸውም።

21 Now therefore fear ye not: I will nourish you, and your little ones. And he comforted them, and spake kindly unto them.

22 ዮሴፍም በግብፅ ተቀመጠ፥ እርሱና የአባቱም ቤተ ሰብ ዮሴፍም መቶ አሥር ዓመት ኖረ።

22 And Joseph dwelt in Egypt, he, and his father’s house: and Joseph lived an hundred and ten years.

23 ዮሴፍም የኤፍሬምን ልጆች እስከ ሦስት ትውልድ አየ የምናሴ ልጅ የማኪር ልጆችም በዮሴፍ ጭን ላይ ተወለዱ።

23 And Joseph saw Ephraim’s children of the third generation: the children also of Machir the son of Manasseh were brought up upon Joseph’s knees.

24 ዮሴፍም ወንድሞቹን አለ። እኔ እሞታለሁ እግዚአብሔርም መጎብኘትን ይጎበኛችኋል፥ ከዚህችም ምድር ያወጣችኋል ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም ወደ ማለላቸው ምድር ያደርሳችኋል።

24 And Joseph said unto his brethren, I die: and God will surely visit you, and bring you out of this land unto the land which he sware to Abraham, to Isaac, and to Jacob.

25 ዮሴፍም የእስራኤልን ልጆች። እግዚአብሔር ሲያስባችሁ አጥንቴን ከዚህ አንሥታችሁ ከእናንተ ጋር ውሰዱ ብሎ አማላቸው።

25 And Joseph took an oath of the children of Israel, saying, God will surely visit you, and ye shall carry up my bones from hence.

26 ዮሴፍም በመቶ አሥር ዓመት ዕድሜው ሞተ በሽቱም አሹት፥ በግብፅ ምድር በሣጥን ውስጥ አኖሩት።

26 So Joseph died, being an hundred and ten years old: and they embalmed him, and he was put in a coffin in Egypt.