ኦሪት ዘፍጥረት Orit ZeFiTret
Genesis / Bereisheit #23
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

ኦሪት ዘፍጥረት 23

Genesis 23

1 የሣራም ዕድሜ መቶ ሀያ ሰባት ዓመት ሆነ።

1 And Sarah was an hundred and seven and twenty years old: these were the years of the life of Sarah.

2 በቂርያትአርባቅም ሞተች እርስዋም በከነዓን ምድር ያለች ኬብሮን ናት አብርሃምም ለሣራ ሊያዝንላትና ሊያለቅስላት ተነሣ።

2 And Sarah died in Kirjath–arba; the same is Hebron in the land of Canaan: and Abraham came to mourn for Sarah, and to weep for her.

3 አብርሃምም ከሬሳው አጠገብ ተነሣ፥

3 And Abraham stood up from before his dead, and spake unto the sons of Heth, saying,

4 ለኬጢ ልጆችም እንዲህ ሲል ተናገረ፦ እኔ በእናንተ ዘንድ ስደተኛና መጻተኛ ነኝ በእናንተ ዘንድ የመቃብር ርስት ስጡኝ፥ ሬሳዬንም ከፊቴ ልቅበር።

4 I am a stranger and a sojourner with you: give me a possession of a buryingplace with you, that I may bury my dead out of my sight.

5 የኬጢ ልጆችም ለአብርሃም መለሱ፥ አሉትም።

5 And the children of Heth answered Abraham, saying unto him,

6 ጌታ ሆይ፥ ስማን አንተ በእኛ መካከል ከእግዚአብሔር አለቃ ነህ ከመቃብር ስፍራችን በመልካሙ ቦታ ሬሳህን ቅበር ሬሳህን ትቀብር ዘንድ ከእኛ መቃብሩን የሚከለክልህ የለም።

6 Hear us, my lord: thou art a mighty prince among us: in the choice of our sepulchres bury thy dead; none of us shall withhold from thee his sepulchre, but that thou mayest bury thy dead.

7 አብርሃምም ተነሣ፥ ለምድሩ ሕዝብም፥ ለኬጢ ልጆች፥ ሰገደ።

7 And Abraham stood up, and bowed himself to the people of the land, even to the children of Heth.

8 እንዲህም አላቸው፦ ሬሳዬን ከፊቴ እንድቀብር ከወደዳችሁስ ስሙኝ፥ ከሰዓር ልጅ ከኤፍሮንም ለምኑልኝ

8 And he communed with them, saying, If it be your mind that I should bury my dead out of my sight; hear me, and intreat for me to Ephron the son of Zohar,

9 በእርሻው ዳር ያለችውን ድርብ ክፍል ያላትን ዋሻውን በሙሉ ዋጋ በመካከላችሁ ይስጠኝ፥ መቃብሩ የእኔ ርስት እንዲሆን።

9 That he may give me the cave of Machpelah, which he hath, which is in the end of his field; for as much money as it is worth he shall give it me for a possession of a buryingplace amongst you.

10 ኤፍሮንም በኬጢ ልጆች መካከል ተቀምጦ ነበር የኬጢ ሰው ኤፍሮንም የኬጢ ልጆችና ወደ ከተማ የሚገቡ ሁሉ ሲሰሙ ለአብርሃም እንዲህ ሲል መለሰለት።

10 And Ephron dwelt among the children of Heth: and Ephron the Hittite answered Abraham in the audience of the children of Heth, even of all that went in at the gate of his city, saying,

11 አይደለም፥ ጌታዬ፥ ስማኝ እርሻውን ሰጥቼሃለሁ በእርሱም ዳር ያለውን ዋሻ ሰጥቼሃለሁ በወገኔ ልጆች ፊት ሰጥቼሃለሁ ሬሳህን ቅበር።

11 Nay, my lord, hear me: the field give I thee, and the cave that is therein, I give it thee; in the presence of the sons of my people give I it thee: bury thy dead.

12 አብርሃምም በአገሩ ሰዎች ፊት ሰገደ

12 And Abraham bowed down himself before the people of the land.

13 የአገሩ ሰዎችም ሲሰሙ ለኤፍሮን እንዲህ ሲል ተናገረ፦ ነገሬን ትሰማ ዘንድ እለምንሃለሁ የእርሻውን ዋጋ እሰጥሃለሁ አንተም ከእኔ ዘንድ ውሰድ፥ ሬሳዬንም በዚያ እቀብራለሁ።

13 And he spake unto Ephron in the audience of the people of the land, saying, But if thou wilt give it, I pray thee, hear me: I will give thee money for the field; take it of me, and I will bury my dead there.

14 ኤፍሮንም ለአብርሃም እንዲህ ሲል መለሰለት።

14 And Ephron answered Abraham, saying unto him,

15 ጌታዬ ሆይ፥ እኔን ስማኝ የአራት መቶ ሰቅል ዋጋ ምድር በእኔና በአንተ መካከል ምንድር ነው? ሬሳህንም ቅበር።

15 My lord, hearken unto me: the land is worth four hundred shekels of silver; what is that betwixt me and thee? bury therefore thy dead.

16 አብርሃምም የኤፍሮንን ነገር ሰማ አብርሃምም በኬጢ ልጆች ፊት የነገረውን አራት መቶ ሰቅል መዝኖ ለኤፍሮን ሰጠው ብሩም ለመሸጫ ለመለወጫ የሚተላለፍ ነበረ።

16 And Abraham hearkened unto Ephron; and Abraham weighed to Ephron the silver, which he had named in the audience of the sons of Heth, four hundred shekels of silver, current money with the merchant.

17 በመምሬ ፊት ያለው ባለድርብ ክፍል የሆነው የኤፍሮን እርሻ ለአብርሃም ጸና

17 And the field of Ephron, which was in Machpelah, which was before Mamre, the field, and the cave which was therein, and all the trees that were in the field, that were in all the borders round about, were made sure

18 እርሻው በእርሱም ያለው ዋሻው፥ በእርሻውም ውስጥ በዙሪያውም ያለው እንጨት ሁሉ በኬጢ ልጆችና በከተማይቱ በር በሚገቡ ሁሉ ፊት ለአብርሃም ርስቱ ሆነ።

18 Unto Abraham for a possession in the presence of the children of Heth, before all that went in at the gate of his city.

19 ከዚህም በኋላ ኬብሮን በምትባል በመምሬ ፊት በከነዓን ምድር ባለው እርሻ ባለ ድርብ ክፍል በሆነው ዋሻ ውስጥ አብርሃም ሚስቱን ሣራን ቀበረ።

19 And after this, Abraham buried Sarah his wife in the cave of the field of Machpelah before Mamre: the same is Hebron in the land of Canaan.

20 እርሻውና በእርሱ ያለው ዋሻው በኬጢ ልጆች ዘንድ ለአብርሃም የመቃብር ርስት ሆኖ ጸና።

20 And the field, and the cave that is therein, were made sure unto Abraham for a possession of a buryingplace by the sons of Heth.