ኦሪት ዘፍጥረት Orit ZeFiTret
Genesis / Bereisheit #46
In Amharic and English
ኦሪት ዘፍጥረት 46 |
Genesis 46 |
1 እስራኤልም ለእርሱ ያለውን ሁሉ ይዞ ተነሣ፥ ወደ ቤርሳቤህ መጣ፥ መሥዋዕትንም ለአባቱ ለይስሐቅ አምላክ ሠዋ። |
1 And Israel took his journey with all that he had, and came to Beer–sheba, and offered sacrifices unto the God of his father Isaac. |
2 እግዚአብሔርም በሌሊት ራእይ። ያዕቆብ ያዕቆብ ብሎ ለእስራኤል ተናገረው። እርሱም፦ እነሆኝ አለ። |
2 And God spake unto Israel in the visions of the night, and said, Jacob, Jacob. And he said, Here am I. |
3 አለውም፦ የአባቶችህ አምላክ እግዚአብሔር እኔ ነኝ ወደ ግብፅ መውረድ አትፍራ፥ በዚያ ትልቅ ሕዝብ አደርግሃለሁና። |
3 And he said, I am God, the God of thy father: fear not to go down into Egypt; for I will there make of thee a great nation: |
4 እኔ ወደ ግብፅ አብሬህ እወርዳለሁ፥ ከዚያም ደግሞ እኔ አወጣሃለሁ ዮሴፍም እጁን በዓይንህ ላይ ያኖራል። |
4 I will go down with thee into Egypt; and I will also surely bring thee up again: and Joseph shall put his hand upon thine eyes. |
5 ያዕቆብም ከቤርሳቤህ ተነሣ የእስራኤልም ልጆች ያዕቆብን ይወስዱ ዘንድ ፈርዖን በሰደዳቸው ሰረገሎች አባታቸውን ያዕቆብንና ሕፃናቶቻቸውን ሴቶቻቸውንም ወሰዱ። |
5 And Jacob rose up from Beer–sheba: and the sons of Israel carried Jacob their father, and their little ones, and their wives, in the wagons which Pharaoh had sent to carry him. |
6 እንስሶቻቸውንም በከነዓን አገርም ያገኙትን ከብታቸውን ሁሉ ይዘው ያዕቆብና ዘሩ ሁሉ ከእርሱ ጋር ወደ ግብፅ መጡ |
6 And they took their cattle, and their goods, which they had gotten in the land of Canaan, and came into Egypt, Jacob, and all his seed with him: |
7 ወንዶች ልጆቹንና የልጆቹን ወንዶች ልጆች፥ ሴቶች ልጆቹንና የወንዶች ልጆቹን ሴቶች ልጆች፥ ዘሩንም ሁሉ ከእርሱ ጋር ወደ ግብፅ አስገባቸው። |
7 His sons, and his sons’ sons with him, his daughters, and his sons’ daughters, and all his seed brought he with him into Egypt. |
8 ወደ ግብፅም የገቡት የእስራኤል ልጆች ስም ይህ ነው፥ ያዕቆብና ልጆቹ የያዕቆብ በኵር ሮቤል። |
8 And these are the names of the children of Israel, which came into Egypt, Jacob and his sons: Reuben, Jacob’s firstborn. |
9 የሮቤልም ልጆች ሄኖኅ፥ ፈሉሶ፥ አስሮን፥ ከርሚ። |
9 And the sons of Reuben; Hanoch, and Phallu, and Hezron, and Carmi. |
10 የስሞዖን ልጆች ይሙኤል፥ ያሚን፥ ኦሃድ፥ ያኪን፥ ጾሐር፥ የከነዓናዊት ልጅ ሳኡል። |
10 And the sons of Simeon; Jemuel, and Jamin, and Ohad, and Jachin, and Zohar, and Shaul the son of a Canaanitish woman. |
11 የሌዊም ልጆች ጌድሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ። |
11 And the sons of Levi; Gershon, Kohath, and Merari. |
12 የይሁዳም ልጆች ዔር፥ አውናን፥ ሴሎም፥ ፋሬስ፥ ዛራ ዔርና አውናን በከነዓን ምድር ሞቱ የፋሬስም ልጆች ኤስሮም፥ ሐሙል። |
12 And the sons of Judah; Er, and Onan, and Shelah, and Pharez, and Zerah: but Er and Onan died in the land of Canaan. And the sons of Pharez were Hezron and Hamul. |
13 የይሳኮርም ልጆች ቶላ፥ ፉዋ፥ ዮብ፥ ሺምሮን። |
13 And the sons of Issachar; Tola, and Phuvah, and Job, and Shimron. |
14 የዛብሎንም ልጆች ሴሬድ፥ ኤሎን፥ ያሕልኤል። |
14 And the sons of Zebulun; Sered, and Elon, and Jahleel. |
15 ልያ በመስጴጦምያ በሶርያ ለያዕቆብ የወለደቻቸው ልጆችና ሴቲቱ ልጅዋ ዲና እነዚህ ናቸው ወንዶችም ሴቶችም ልጆችዋ ሁሉ ሠላሳ ሦስት ነፍስ ናቸው። |
15 These be the sons of Leah, which she bare unto Jacob in Padan–aram, with his daughter Dinah: all the souls of his sons and his daughters were thirty and three. |
16 የጋድም ልጆች ጽፎን፥ ሐጊ፥ ሹኒ፥ ኤስቦን፥ ዔሪ፥ አሮዲ፥ አርኤሊ። |
16 And the sons of Gad; Ziphion, and Haggi, Shuni, and Ezbon, Eri, and Arodi, and Areli. |
17 የአሴርም ልጆች ዪምና፥ የሱዋ፥ የሱዊ፥ በሪዓ፥ እኅታቸው ሤራሕ የበሪዓ ልጆችም ሔቤር፥ መልኪኤል። |
17 And the sons of Asher; Jimnah, and Ishuah, and Isui, and Beriah, and Serah their sister: and the sons of Beriah; Heber, and Malchiel. |
18 ላባ ለልጁ ለልያ የሰጣት የዘለፋ ልጆች እነዚህ ናቸው እነዚህን አሥራ ስድስቱንም ነፍስ ለያዕቆብ ወለደች። |
18 These are the sons of Zilpah, whom Laban gave to Leah his daughter, and these she bare unto Jacob, even sixteen souls. |
19 የያዕቆብ ሚስት የራሔል ልጆች ዮሴፍና ብንያም ናቸው። |
19 The sons of Rachel Jacob’s wife; Joseph, and Benjamin. |
20 ለዮሴፍም በግብፅ ምድር ምናሴና ኤፍሬም ተወለዱለት የሄልዮቱ ከተማ ካህን የጶጥፌራ ልጅ አስናት የወለደቻቸው ናቸው። |
20 And unto Joseph in the land of Egypt were born Manasseh and Ephraim, which Asenath the daughter of Poti–pherah priest of On bare unto him. |
21 የብንያምም ልጆች ቤላ፥ ቤኬር፥ አስቤል የቤላ ልጆችም ጌራ፥ ናዕማን፥ አኪ፥ ሮስ፥ ማንፌን፥ ሑፊም ጌራም አርድን ወለደ። |
21 And the sons of Benjamin were Belah, and Becher, and Ashbel, Gera, and Naaman, Ehi, and Rosh, Muppim, and Huppim, and Ard. |
22 ለያዕቆብ የተወለዱለት የራሔልም ልጆች እነዚህ ናቸው ሁሉም አሥራ አራት ነፍስ ናቸው። |
22 These are the sons of Rachel, which were born to Jacob: all the souls were fourteen. |
23 የዳንም ልጆች ሑሺም። |
23 And the sons of Dan; Hushim. |
24 የንፍታሌምም ልጆች ያሕጽኤል፥ ጉኒ፥ ዬጽር፥ ሺሌም። |
24 And the sons of Naphtali; Jahzeel, and Guni, and Jezer, and Shillem. |
25 ላባ ለልጁ ለራሔል የሰጣት የባላ ልጆች እነዚህ ናቸው እነዚህንም ለያዕቆብ ወለደችለት ሁሉም ሰባት ነፍስ ናቸው። |
25 These are the sons of Bilhah, which Laban gave unto Rachel his daughter, and she bare these unto Jacob: all the souls were seven. |
26 ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብፅ የገቡት ሰዎች ሁሉ ከጉልበቱ የወጡት፥ ከልጆቹ ሚስቶች ሌላ፥ ሁላቸው ስድሳ ስድስት ናቸው። |
26 All the souls that came with Jacob into Egypt, which came out of his loins, besides Jacob’s sons’ wives, all the souls were threescore and six; |
27 በግብፅ ምድር የተወለዱለት የዮሴፍም ልጆች ሁለት ናቸው ወደ ግብፅ የገቡት የያዕቆብ ቤተ ሰዎች ሁሉ ሰባ ናቸው። |
27 And the sons of Joseph, which were born him in Egypt, were two souls: all the souls of the house of Jacob, which came into Egypt, were threescore and ten. |
28 ይሁዳንም በጌሤም እንዲቀበለው በፊቱ ወደ ዮሴፍ ላከ ወደ ጌሤም ምድርም ደረሱ። |
28 And he sent Judah before him unto Joseph, to direct his face unto Goshen; and they came into the land of Goshen. |
29 ዮሴፍም ሰረገላውን አዘጋጀ፥ አባቱንም እስራኤልን ሊገናኘው ወደ ጌሤም ወጣ ባየውም ጊዜ በአንገቱ ላይ ወደቀ፥ አቅፎትም ረጅም ጊዜ አለቀሰ። |
29 And Joseph made ready his chariot, and went up to meet Israel his father, to Goshen, and presented himself unto him; and he fell on his neck, and wept on his neck a good while. |
30 እስራኤልም ዮሴፍን፦ አንተ ገና በሕይወት ሳለህ ፊትህን አይቼአለሁና አሁን ልሙት አለው። |
30 And Israel said unto Joseph, Now let me die, since I have seen thy face, because thou art yet alive. |
31 ዮሴፍም ወንድሞቹንና የአባቱን ቤተ ሰዎች እንዲህ አላቸው፦ እኔ መጥቼ ለፈርዖን እንዲህ ብዬ እነግረዋለሁ። በከነዓን ምድር የነበሩት ወንድሞቼና የአባቴ ቤተ ሰዎች ወደ እኔ መጥተዋል |
31 And Joseph said unto his brethren, and unto his father’s house, I will go up, and shew Pharaoh, and say unto him, My brethren, and my father’s house, which were in the land of Canaan, are come unto me; |
32 እነርሱም በግ የሚጠብቁ ሰዎች ናቸው፥ እንስሳ ያረቡ ነበርና በጎቻቸውንና ላሞቻቸውን ያላቸውንም ሁሉ አመጡ። |
32 And the men are shepherds, for their trade hath been to feed cattle; and they have brought their flocks, and their herds, and all that they have. |
33 ፈርዖንም ቢጠራችሁ። ተግባራችሁስ ምንድር ነው? ቢላችሁ፥ |
33 And it shall come to pass, when Pharaoh shall call you, and shall say, What is your occupation? |
34 በግ ጠባቂ ሁሉ ለግብፅ ሰዎች ርኵስ ነውና በጌሤም እንድትቀመጡ እንዲህ በሉት። እኛ ባሪያዎችህ ከብላቴናነታችን ጀምረን እስከ አሁን ድረስ፥ እኛም አባቶቻችንም፥ እንስሳ አርቢዎች ነን። |
34 That ye shall say, Thy servants’ trade hath been about cattle from our youth even until now, both we, and also our fathers: that ye may dwell in the land of Goshen; for every shepherd is an abomination unto the Egyptians. |