ኦሪት ዘፍጥረት Orit ZeFiTret
Genesis / Bereisheit #49
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

ኦሪት ዘፍጥረት 49

Genesis 49

1 ያዕቆብም ልጆቹን ጠርቶ እንዲህ አለ፦ በኋለኛው ዘመን የሚያገኛችሁን እንድነግራችሁ ተሰብሰቡ።

1 And Jacob called unto his sons, and said, Gather yourselves together, that I may tell you that which shall befall you in the last days.

2 እናንት የያዕቆብ ልጆች ተሰብሰቡ፥ ስሙም አባታችሁ እስራኤልንም አድምጡ።

2 Gather yourselves together, and hear, ye sons of Jacob; and hearken unto Israel your father.

3 ሮቤል፥ አንተ በኵር ልጄና ኃይሌ፥ የጕብዝናዬም መጀመሪያ ነህ የክብር አለቃና የኃይል አለቃ።

3 Reuben, thou art my firstborn, my might, and the beginning of my strength, the excellency of dignity, and the excellency of power:

4 እንደ ውኃ የምትዋልል ነህ አለቅነት ለአንተ አይሁን ወደ አባትህ መኝታ ወጥተሃልና አረከስኸውም ወደ አልጋዬም ወጣ።

4 Unstable as water, thou shalt not excel; because thou wentest up to thy father’s bed; then defiledst thou it: he went up to my couch.

5 ስምዖንና ሌዊ ወንድማማች ናቸው ሰይፎቻቸው የዓመፃ መሣሪያ ናቸው።

5 Simeon and Levi are brethren; instruments of cruelty are in their habitations.

6 በምክራቸው፥ ነፍሴ፥ አትግባ ከጉባኤአቸውም ጋር፥ ክብሬ፥ አትተባበር በቍጣቸው ሰውን ገድለዋልና፥ በገዛ ፈቃዳቸውም በሬን አስነክሰዋልና።

6 O my soul, come not thou into their secret; unto their assembly, mine honour, be not thou united: for in their anger they slew a man, and in their selfwill they digged down a wall.

7 ቍጣቸው ርጉም ይሁን፥ ጽኑ ነበርና ኵርፍታቸውም፥ ብርቱ ነበርና በያዕቆብ እከፋፍላቸዋለሁ፥ በእስራኤልም እበታትናቸዋለሁ።

7 Cursed be their anger, for it was fierce; and their wrath, for it was cruel: I will divide them in Jacob, and scatter them in Israel.

8 ይሁዳ፥ ወንድሞችህ አንተን ያመሰግኑሃል እጅህ በጠላቶችህ ደንደስ ላይ ነው የአባትህ ልጆች በፊትህ ይሰግዳሉ።

8 Judah, thou art he whom thy brethren shall praise: thy hand shall be in the neck of thine enemies; thy father’s children shall bow down before thee.

9 ይሁዳ የአንበሳ ደቦል ነው ልጄ ሆይ፥ ከአደንህ ወጣህ እንደ አንበሳ አሸመቀ፥ እንደ ሴት አንበሳም አደባ ያስነሣውስ ዘንድ ማን ይችላል?

9 Judah is a lion’s whelp: from the prey, my son, thou art gone up: he stooped down, he couched as a lion, and as an old lion; who shall rouse him up?

10 በትረ መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም፥ የገዥም ዘንግ ከእግሮቹ መካከል፥ ገዥ የሆነው እስኪመጣ ድረስ የአሕዛብ መታዘዝም ለእርሱ ይሆናል።

10 The sceptre shall not depart from Judah, nor a lawgiver from between his feet, until Shiloh come; and unto him shall the gathering of the people be.

11 ውርንጫውን በወይን ግንድ ያስራል፥ የአህያይቱንም ግልገል በወይን አረግ ልብሱን በወይን ያጥባል፥ መጎናጸፊያውንም በወይን ደም።

11 Binding his foal unto the vine, and his ass’s colt unto the choice vine; he washed his garments in wine, and his clothes in the blood of grapes:

12 ዓይኑም ከወይን ይቀላል ጥርሱም ከወተት ነጭ ይሆናል።

12 His eyes shall be red with wine, and his teeth white with milk.

13 ዛብሎን በባሕር ዳር ይቀመጣል እርሱም ለመርከቦች ወደብ ይሆናል ዳርቻውም እስከ ሲዶና ድረስ ነው።

13 Zebulun shall dwell at the haven of the sea; and he shall be for an haven of ships; and his border shall be unto Zidon.

14 ይሳኮር አጥንተ ብርቱ አህያ ነው፥ በበጎች ጕረኖም መካከል ያርፋል።

14 Issachar is a strong ass couching down between two burdens:

15 ዕረፍትም መልካም መሆንዋን አየ፥ ምድሪቱም የለማች መሆንዋን ትከሻውን ለመሸከም ዝቅ አደረገ፥ በሥራም ገበሬ ሆነ።

15 And he saw that rest was good, and the land that it was pleasant; and bowed his shoulder to bear, and became a servant unto tribute.

16 ዳን በወገኑ ይፈርዳል፥ ከእስራኤል ነገድ እንደ አንዱ።

16 Dan shall judge his people, as one of the tribes of Israel.

17 ዳን በጐዳና ላይ እንደ እባብ ይሆናል፥ በመንገድም እንደ ቀንዳም እባብ ፈረሱን ከሰኮናው ይነክሳል፥ ፈረሰኛም ወደ ኋላው ይወድቃል።

17 Dan shall be a serpent by the way, an adder in the path, that biteth the horse heels, so that his rider shall fall backward.

18 እግዚአብሔር ሆይ፥ መድኃኒትህን እጠብቃለሁ።

18 I have waited for thy salvation, O Lord.

19 ጋድን ዘማቾች ይዘምቱበታል እርሱ ግን ተከታትሎ ይዘምትባቸዋል።

19 Gad, a troop shall overcome him: but he shall overcome at the last.

20 የአሴር እንጀራው ወፍራም ነው፥ ለነገሥታቱም ደስ የሚያሰኝ መብልን ይሰጣል።

20 Out of Asher his bread shall be fat, and he shall yield royal dainties.

21 ንፍታሌም የተፈታ ሚዳቋ ነው መልካም ቃልን ይሰጣል።

21 Naphtali is a hind let loose: he giveth goodly words.

22 ዮሴፍ ትንሹ የፍሬ ዛፍ ነው፥ በምንጭ አጠገብ የሚያፈራ የፍሬ ዛፍ አረጎቹ በቅጥር ላይ ያድጋሉ።

22 Joseph is a fruitful bough, even a fruitful bough by a well; whose branches run over the wall:

23 ቀስተኞች አስቸገሩት፥ ነደፉትም፥ ተቃወሙትም

23 The archers have sorely grieved him, and shot at him, and hated him:

24 ነገር ግን ቀስቱ እንደ ጸና ቀረ የእጆቹም ክንድ በያዕቆብ አምላክ እጅ በረታ፥ በዚያው በጠባቂው በእስራኤል ዓምድ፥

24 But his bow abode in strength, and the arms of his hands were made strong by the hands of the mighty God of Jacob; (from thence is the shepherd, the stone of Israel:)

25 በአባትህ አምላክ እርሱም የሚረዳህ፥ ሁሉንም በሚችል አምላክ እርሱም የሚባርክህ፥ በሰማይ በረከት ከላይ በሚገኝ፥ በጥልቅም በረከት ከታች በሚሠራጭ፥ በጡትና በማኅፀን በረከት።

25 Even by the God of thy father, who shall help thee; and by the Almighty, who shall bless thee with blessings of heaven above, blessings of the deep that lieth under, blessings of the breasts, and of the womb:

26 የአባትህ በረከቶች ጽኑዓን ከሆኑ ከተራሮች በረከቶች ይልቅ ኃያላን ናቸው ዘላለማውያን ከሆኑ ከኮረፍቶችም በረከቶች ይልቅ ኃያላን ናቸው እነርሱም በዮሴፍ ራስ ላይ ይሆናሉ፥ በወንድሞቹ መካከል አለቃ በሆነው ራስ አናት ላይ።

26 The blessings of thy father have prevailed above the blessings of my progenitors unto the utmost bound of the everlasting hills: they shall be on the head of Joseph, and on the crown of the head of him that was separate from his brethren.

27 ብንያም ነጣቂ ተኵላ ነው የበዘበዘውን በጥዋት ይበላል፥ የማረከውንም በማታ ይካፈላል።

27 Benjamin shall ravin as a wolf: in the morning he shall devour the prey, and at night he shall divide the spoil.

28 እነዚህም ሁሉ አሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ናቸው አባታቸው የነገራቸው ይህ ነው፥ ባረካቸውም እያንዳንዳቸውን እንደ በረከታቸው ባረካቸው።

28 All these are the twelve tribes of Israel: and this is it that their father spake unto them, and blessed them; every one according to his blessing he blessed them.

29 እንዲህ ብሎም አዘዛቸው። እኔ ወደ ወገኖቼ እሰበሰባለሁ በኬጢያዊ በኤፍሮን እርሻ ላይ ባለችው ዋሻ ከአባቶቼ ጋር ቅበሩኝ

29 And he charged them, and said unto them, I am to be gathered unto my people: bury me with my fathers in the cave that is in the field of Ephron the Hittite,

30 እርስዋም በከነዓን ምድር በመምሬ ፊት ያለች፥ አብርሃም ለመቃብር ርስት ከኬጢያዊ ከኤፍሮን ከእርሻው ጋር የገዛት፥ ባለ ድርብ ክፍል ዋሻ ናት።

30 In the cave that is in the field of Machpelah, which is before Mamre, in the land of Canaan, which Abraham bought with the field of Ephron the Hittite for a possession of a buryingplace.

31 አብርሃምና ሚስቱ ሣራ ከዚያ ተቀበሩ ይስሐቅና ሚስቱ ርብቃ ከዚያ ተቀበሩ ከዚያም እኔ ልያን ቀበርኋት

31 There they buried Abraham and Sarah his wife; there they buried Isaac and Rebekah his wife; and there I buried Leah.

32 እርሻውና በእርስዋ ላይ ያለችው ዋሻ ከኬጢ ልጆች የተገዙ ናቸው።

32 The purchase of the field and of the cave that is therein was from the children of Heth.

33 ያዕቆብም ትእዛዙን ለልጆቹ ተናግሮ በፈጸመ ጊዜ እግሮቹን በአልጋው ላይ ሰብስቦ ሞተ፥ ወደ ወገኖቹም ተከማቸ።

33 And when Jacob had made an end of commanding his sons, he gathered up his feet into the bed, and yielded up the ghost, and was gathered unto his people.