ኦሪት ዘፍጥረት Orit ZeFiTret
Genesis / Bereisheit #50
In Amharic and English
ኦሪት ዘፍጥረት 50 |
Genesis 50 |
1 ዮሴፍም በአባቱ ፊት ወደቀ፥ በእርሱም ላይ አለቀሰ፥ ሳመውም። |
1 And Joseph fell upon his father’s face, and wept upon him, and kissed him. |
2 ዮሴፍም ባለመድኃኒቶች አገልጋዮቹ አባቱን በሽቱ ያሹት ዘንድ አዘዘ ባለመድኃኒቶችም እስራኤልን በሽቱ አሹት። |
2 And Joseph commanded his servants the physicians to embalm his father: and the physicians embalmed Israel. |
3 አርባ ቀንም ፈጸሙለት የሽቱ መደረጊያው ወራት እንደዚሁ ይፈጸማልና የግብፅም ሰዎች ሰባ ቀን አለቀሱለት። |
3 And forty days were fulfilled for him; for so are fulfilled the days of those which are embalmed: and the Egyptians mourned for him threescore and ten days. |
4 የልቅሶውም ወራት ባለፈ ጊዜ ዮሴፍ ለፈርዖን ቤተ ሰቦች እንዲህ ብሎ ተናገረ። እኔ በፊታችሁ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆንሁ ለፈርዖን እንዲህ ብላችሁ ንገሩት። |
4 And when the days of his mourning were past, Joseph spake unto the house of Pharaoh, saying, If now I have found grace in your eyes, speak, I pray you, in the ears of Pharaoh, saying, |
5 አባቴ አምሎኛል እንዲህ ሲል፦ እነሆ እኔ እሞታለሁ በቈፈርሁት መቃብር በከነዓን ምድር ከዚያ ቅበረኝ። አሁንም ወጥቼ አባቴን ልቅበርና ልመለስ። |
5 My father made me swear, saying, Lo, I die: in my grave which I have digged for me in the land of Canaan, there shalt thou bury me. Now therefore let me go up, I pray thee, and bury my father, and I will come again. |
6 ፈርዖንም። ውጣ፥ አባትህንም እንዳማለህ ቅበረው አለው። |
6 And Pharaoh said, Go up, and bury thy father, according as he made thee swear. |
7 ዮሴፍም አባቱን ሊቀብር ወጣ የፈርዖን ሎላልትም ሁሉ ከእርሱ ጋር ወጡ፥ የቤቱ ሽማግሌዎችም የግብፅ ምድር ሽማግሌዎችም ሁሉ |
7 And Joseph went up to bury his father: and with him went up all the servants of Pharaoh, the elders of his house, and all the elders of the land of Egypt, |
8 የዮሴፍም ቤተ ሰቦች ሁሉ ወንድሞቹም የአባቱም ቤተ ሰቦች ወጡ ልጆቻቸውንና በጎቻቸውን ከብቶቻቸውን ብቻ በጌሤም ተዉ። |
8 And all the house of Joseph, and his brethren, and his father’s house: only their little ones, and their flocks, and their herds, they left in the land of Goshen. |
9 ሰረገሎችም ፈረሰኞችም ከእርሱ ጋር ወጡ፥ ሠራዊቱም እጅግ ብዙ ነበረ። |
9 And there went up with him both chariots and horsemen: and it was a very great company. |
10 በዮርዳኖስ ማዶ ወዳለችው ወደ አጣድ አውድማ መጡ፥ እጅግ ታላቅ በሆነ በጽኑ ልቅሶም አለቀሱለት ለአባቱም ሰባት ቀን ልቅሶ አደረገለት። |
10 And they came to the threshingfloor of Atad, which is beyond Jordan, and there they mourned with a great and very sore lamentation: and he made a mourning for his father seven days. |
11 በዚያች ምድር የሚኖሩ የከነዓን ሰዎችም በአጣድ አውድማ የሆነውን ልቅሶ ባዩ ጊዜ። ይህ ለግብፅ ሰዎች ታላቅ ልቅሶ ነው አሉ ስለዚህም የዚያን ቦታ ስም አቤል ምጽራይም ብለው ጠሩት እርሱም በዮርዳኖስ ማዶ ነው። |
11 And when the inhabitants of the land, the Canaanites, saw the mourning in the floor of Atad, they said, This is a grievous mourning to the Egyptians: wherefore the name of it was called Abel–mizraim, which is beyond Jordan. |
12 ልጆቹም እንዳዘዛቸው እንደዚያው አደረጉለት |
12 And his sons did unto him according as he commanded them: |
13 ልጆቹም ወደ ከነዓን ምድር አጓዙት፥ ባለ ሁለት ክፍል በሆነች ዋሻም ቀበሩት እርስዋም በመምሬ ፊት ያለች፥ አብርሃም ለመቃብር ርስት ከኬጢያዊ ከኤፍሮን ከእርሻው ጋር የገዛት ዋሻ ናት። |
13 For his sons carried him into the land of Canaan, and buried him in the cave of the field of Machpelah, which Abraham bought with the field for a possession of a buryingplace of Ephron the Hittite, before Mamre. |
14 ዮሴፍና ወንድሞቹ አባቱንም ሊቀብሩ ከእርሱ ጋር የወጡት ሰዎች ሁሉ አባቱን ከቀበረ በኋላ ወደ ግብፅ ተመለሱ። |
14 And Joseph returned into Egypt, he, and his brethren, and all that went up with him to bury his father, after he had buried his father. |
15 የዮሴፍም ወንድሞች አባታቸው እንደ ሞተ ባዩ ጊዜ እንዲህ አሉ። ምናልባት ዮሴፍ ይጠላን ይሆናል፥ ባደረግንበትም ክፋት ሁሉ ብድራት ይመልስብን ይሆናል። |
15 And when Joseph’s brethren saw that their father was dead, they said, Joseph will peradventure hate us, and will certainly requite us all the evil which we did unto him. |
16 ወደ ዮሴፍም መልእክት ላኩ እንዲህም አሉት፦ አባትህ ገና ሳይሞት እንዲህ ብሎ አዝዞአል። |
16 And they sent a messenger unto Joseph, saying, Thy father did command before he died, saying, |
17 ዮሴፍን እንዲህ በሉት። እባክህ የወንድሞችህን በደል ኃጢአታቸውንም ይቅር በል፥ እነርሱ በአንተ ከፍተውብሃልና አሁንም እባክህ የአባትህ አምላክ ባሪያዎች የበደሉህን ይቅር በል። |
17 So shall ye say unto Joseph, Forgive, I pray thee now, the trespass of thy brethren, and their sin; for they did unto thee evil: and now, we pray thee, forgive the trespass of the servants of the God of thy father. And Joseph wept when they spake unto him. |
18 ዮሴፍም ይህን ሲሉት አለቀሰ። ወንድሞቹ ደግሞ መጡ በፊቱም ሰግደው። እነሆ እኛ ለአንተ ባሪያዎችህ ነን አሉት። |
18 And his brethren also went and fell down before his face; and they said, Behold, we be thy servants. |
19 ዮሴፍም አላቸው። አትፍሩ እኔ በእግዚአብሔር ፋንታ ነኝን? |
19 And Joseph said unto them, Fear not: for am I in the place of God? |
20 እናንተ ክፉ ነገርን አሰባችሁብኝ እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እንዲድን ለማድረግ ለመልካም አሰበው። |
20 But as for you, ye thought evil against me; but God meant it unto good, to bring to pass, as it is this day, to save much people alive. |
21 አሁንም አትፍሩ እኔ እናንተንና ልጆቻችሁን እመግባችኋለሁ። አጽናናቸውም ደስ አሰኛቸውም። |
21 Now therefore fear ye not: I will nourish you, and your little ones. And he comforted them, and spake kindly unto them. |
22 ዮሴፍም በግብፅ ተቀመጠ፥ እርሱና የአባቱም ቤተ ሰብ ዮሴፍም መቶ አሥር ዓመት ኖረ። |
22 And Joseph dwelt in Egypt, he, and his father’s house: and Joseph lived an hundred and ten years. |
23 ዮሴፍም የኤፍሬምን ልጆች እስከ ሦስት ትውልድ አየ የምናሴ ልጅ የማኪር ልጆችም በዮሴፍ ጭን ላይ ተወለዱ። |
23 And Joseph saw Ephraim’s children of the third generation: the children also of Machir the son of Manasseh were brought up upon Joseph’s knees. |
24 ዮሴፍም ወንድሞቹን አለ። እኔ እሞታለሁ እግዚአብሔርም መጎብኘትን ይጎበኛችኋል፥ ከዚህችም ምድር ያወጣችኋል ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም ወደ ማለላቸው ምድር ያደርሳችኋል። |
24 And Joseph said unto his brethren, I die: and God will surely visit you, and bring you out of this land unto the land which he sware to Abraham, to Isaac, and to Jacob. |
25 ዮሴፍም የእስራኤልን ልጆች። እግዚአብሔር ሲያስባችሁ አጥንቴን ከዚህ አንሥታችሁ ከእናንተ ጋር ውሰዱ ብሎ አማላቸው። |
25 And Joseph took an oath of the children of Israel, saying, God will surely visit you, and ye shall carry up my bones from hence. |
26 ዮሴፍም በመቶ አሥር ዓመት ዕድሜው ሞተ በሽቱም አሹት፥ በግብፅ ምድር በሣጥን ውስጥ አኖሩት። |
26 So Joseph died, being an hundred and ten years old: and they embalmed him, and he was put in a coffin in Egypt. |