ኦሪት ዘጸአት Orit ZeTseAt
Exodus / Shemot #1
In Amharic and English
ኦሪት ዘጸአት 1 |
Exodus 1 |
1 ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብፅ የገቡት የእስራኤል ልጆች ስሞች እነዚህ ናቸው ሰው ሁሉ ከቤተ ሰቡ ጋር ገባ። |
1 Now these are the names of the children of Israel, which came into Egypt; every man and his household came with Jacob. |
2 ሮቤል፥ |
2 Reuben, Simeon, Levi, and Judah, |
3 ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮር፥ ዛብሎን፥ |
3 Issachar, Zebulun, and Benjamin, |
4 ብንያም፥ ዳን፥ ንፍታሌም፥ ጋድ፥ አሴር። |
4 Dan, and Naphtali, Gad, and Asher. |
5 ከያቆብ ጕልበት የወጡት ሰዎች ሁሉ ሰባ ነፍሶች ነበሩ ዮሴፍም አስቀድሞ በግብፅ ነበረ። |
5 And all the souls that came out of the loins of Jacob were seventy souls: for Joseph was in Egypt already. |
6 ዮሴፍም ሞተ፥ ወንድሞቹም፥ ያም ትውልድ ሁሉ። |
6 And Joseph died, and all his brethren, and all that generation. |
7 የእስራኤልም ልጆች አፈሩ፥ እጅግም በዙ፥ ተባዙም፥ አጅግም ጸኑ ምድሪቱም በእነርሱ ሞላች። |
7 And the children of Israel were fruitful, and increased abundantly, and multiplied, and waxed exceeding mighty; and the land was filled with them. |
8 በግብፅም ዮሴፍን ያላወቀ አዲስ ንጉሥ ተነሣ። |
8 Now there arose up a new king over Egypt, which knew not Joseph. |
9 እርሱም ሕዝቡን። እነሆ፥ የእስራኤል ልጆች ሕዝብ ከእኛ ይልቅ በዝተዋል በርትተውማል |
9 And he said unto his people, Behold, the people of the children of Israel are more and mightier than we: |
10 እንዳይበዙ፥ ሰልፍም በተነሳብን ጊዜ ጠላቶቻችንን አግዘው እንዳይወጉን ከምድሪቱም እንዳይወጡ፥ ኑ እንጠበብባቸው አለ። |
10 Come on, let us deal wisely with them; lest they multiply, and it come to pass, that, when there falleth out any war, they join also unto our enemies, and fight against us, and so get them up out of the land. |
11 በብርቱ ሥራም ያስጨንቁአቸው ዘንድ ግብር አስገባሪዎችን ሾመባቸው ለፈርዖንም ፊቶምንና ራምሴን ጽኑ ከተሞች አድርገው ሠሩ። |
11 Therefore they did set over them taskmasters to afflict them with their burdens. And they built for Pharaoh treasure cities, Pithom and Raamses. |
12 ነገር ግን እንዳስጨነቁአቸው መጠን እንዲሁ በዙ፥ እጅግም ጸኑ ከእስራኤልም ልጆች የተነሣ ተጸይፈዋቸው ነበር። |
12 But the more they afflicted them, the more they multiplied and grew. And they were grieved because of the children of Israel. |
13 ግብፃውያንም የእስራኤልን ልጆች በመከራ ገዙአቸው። |
13 And the Egyptians made the children of Israel to serve with rigour: |
14 በጽኑ ሥራ፥ በጭቃ፥ በጡብም በእርሻም ሥራ ሁሉ፥ በመከራም በሚያሠሩአቸው ሥራ ሁሉ፥ ሕይወታቸውን ያስመርሩአቸው ነበር። |
14 And they made their lives bitter with hard bondage, in morter, and in brick, and in all manner of service in the field: all their service, wherein they made them serve, was with rigour. |
15 የግብፅም ንጉሥ አንዲቱ ሲፓራ ሁለተኛይቱም ፉሐ የሚባሉትን የዕብራውያንን አዋላጆች እንዲህ ብሎ ተናገረ። |
15 And the king of Egypt spake to the Hebrew midwives, of which the name of the one was Shiphrah, and the name of the other Puah: |
16 እናንተ የዕብራውያንን ሴቶች ስታዋልዱ፥ ለመውለድ እንደደረሱ ባያችሁ ጊዜ፥ ወንድ ቢሆን ግደሉት ሴት ብትሆን ግን በሕይወት ትኑር። |
16 And he said, When ye do the office of a midwife to the Hebrew women, and see them upon the stools; if it be a son, then ye shall kill him: but if it be a daughter, then she shall live. |
17 አዋላጆች ግን እግዚአብሔርን ፈሩ፥ የግብፅ ንጉሥም እንዳዘዛቸው አላደረጉም፥ ወንዶቹን ሕፃናትንም አዳኑአቸው። |
17 But the midwives feared God, and did not as the king of Egypt commanded them, but saved the men children alive. |
18 የግብፅም ንጉሥ አዋላጆችን ጠርቶ። ለምን እንዲህ አደረጋችሁ? ወንዶቹን ሕፃናትንስ ለምን አዳናችሁ? አላቸው። |
18 And the king of Egypt called for the midwives, and said unto them, Why have ye done this thing, and have saved the men children alive? |
19 አዋላጆቹም ፈርዖንን፦ የዕብራውያን ሴቶች እንደ ግብፅ ሴቶች ስላልሆኑ እነርሱ ጠንካሮች ናቸውና አዋላጆች ሳይገቡ ስለሚወልዱ ነው አሉት። |
19 And the midwives said unto Pharaoh, Because the Hebrew women are not as the Egyptian women; for they are lively, and are delivered ere the midwives come in unto them. |
20 እግዚአብሔርም ለአዋላጆች መልካም አደረገላቸው ሕዝቡም በዛ፥ እጅግም ጸና። |
20 Therefore God dealt well with the midwives: and the people multiplied, and waxed very mighty. |
21 እንዲህም ሆነ አዋላጆች እግዚአብሔርን ስለ ፈሩ ቤቶችን አደረገላቸው። |
21 And it came to pass, because the midwives feared God, that he made them houses. |
22 ፈርዖንም። የሚወለደውን ወንድ ልጅ ሁሉ ወደ ወንዝ ጣሉት፥ ሴትን ልጅ ሁሉ ግን በሕይወት አድኑአት ብሎ ሕዝቡን ሁሉ አዘዘ። |
22 And Pharaoh charged all his people, saying, Every son that is born ye shall cast into the river, and every daughter ye shall save alive. |