መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David  #110
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

መዝሙረ ዳዊት 110

Psalm 110

1 እግዚአብሔር ጌታዬን፦ ጠላቶችህን ለእግርህ መቀመጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው።

1 The Lord said unto my Lord, Sit thou at my right hand, until I make thine enemies thy footstool.

2 እግዚአብሔር የኃይልን በትር ከጽዮን ይልክልሃል በጠላቶችህም መካከል ግዛ።

2 The Lord shall send the rod of thy strength out of Zion: rule thou in the midst of thine enemies.

3 ከአንተ ጋር ቀድሞ በኃይልህ ቀን፥ በቅዱሳን ብርሃን፥ ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ ከሆድ ወለድሁህ።

3 Thy people shall be willing in the day of thy power, in the beauties of holiness from the womb of the morning: thou hast the dew of thy youth.

4 እንደ መልከ ጼዴቅ ሥርዓት አንተ ለዘላለም ካህን ነህ ብሎ፥ እግዚአብሔር ማለ አይጸጸትም።

4 The Lord hath sworn, and will not repent, Thou art a priest for ever after the order of Melchizedek.

5 እግዚአብሔር በቀኝህ ነገሥታትን በቍጣው ቀን ይቀጠቅጣቸዋል።

5 The Lord at thy right hand shall strike through kings in the day of his wrath.

6 በአሕዛብ መካከል ይፈርዳል፥ ሬሳዎችንም ያበዛል በሰፊ ምድር ላይ ራሶችን ይቀጠቅጣል።

6 He shall judge among the heathen, he shall fill the places with the dead bodies; he shall wound the heads over many countries.

7 በመንገድ ከፈሳሽ ውኃ ይጠጣል ስለዚህ ራስ ከፍ ከፍ ይላል።

7 He shall drink of the brook in the way: therefore shall he lift up the head.