ኦሪት ዘዳግም Orit ZeDaGim
Deuteronomy / Devarim #34
In Amharic and English
|
ኦሪት ዘዳግም 34 |
Deuteronomy 34 |
1 ሙሴም ከሞዓብ ሜዳ በኢያሪኮ ፊት ለፊት ወዳለው ወደ ናባው ተራራ ወደ ፈስጋ ራስ ወጣ እግዚአብሔርም እስከዳን ድረስ ያለውን የገለዓድን ምድር፥ |
1 And Moses went up from the plains of Moab unto the mountain of Nebo, to the top of Pisgah, that is over against Jericho. And the Lord shewed him all the land of Gilead, unto Dan, |
2 የንፍታሌምንም ምድር ሁሉ፥ የኤፍሬምንና የምናሴንም ምድር፥ እስከ ምዕራብም ባሕር ድረስ ያለውን የይሁዳን ምድር ሁሉ፥ ደቡብንም፥ |
2 And all Naphtali, and the land of Ephraim, and Manasseh, and all the land of Judah, unto the utmost sea, |
3 እስከ ዞዓር ድረስ ያለውንም የዘንባባ ዛፎች ያሉባትን ከተማ የኢያሪኮን ሸለቆ ሜዳ አሳየው። |
3 And the south, and the plain of the valley of Jericho, the city of palm trees, unto Zoar. |
4 እግዚአብሔርም፦ ለዘርህ እሰጣታለሁ ብዬ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም የማልሁላቸው ምድር ይህች ናት በዓይንህ እንድታያት አደረግሁህ፥ ነገር ግን ወደዚያች አትሻገርም አለው። |
4 And the Lord said unto him, This is the land which I sware unto Abraham, unto Isaac, and unto Jacob, saying, I will give it unto thy seed: I have caused thee to see it with thine eyes, but thou shalt not go over thither. |
5 የእግዚአብሔር ባሪያም ሙሴ እንደ እግዚአብሔር ቃል በዚያ በሞዓብ ምድር ሞተ። |
5 So Moses the servant of the Lord died there in the land of Moab, according to the word of the Lord. |
6 በቤተ ፌጎርም ፊት ለፊት በሞዓብ ምድር በሸለቆው ውስጥ ተቀበረ እስከ ዛሬም ድረስ መቃብሩን ማንም አላወቀም። |
6 And he buried him in a valley in the land of Moab, over against Beth–peor: but no man knoweth of his sepulchre unto this day. |
7 ሙሴም በሞተ ጊዜ ዕድሜው መቶ ሀያ ዓመት ነበረ ዓይኑ አልፈዘዘም፥ ጕልበቱም አልደነገዘም። |
7 And Moses was an hundred and twenty years old when he died: his eye was not dim, nor his natural force abated. |
8 የእስራኤልም ልጆች በሞዓብ ሜዳ ሠላሳ ቀን ለሙሴ አለቀሱለት ለሙሴም ያለቀሱለት የልቅሶው ወራት ተፈጸመ። |
8 And the children of Israel wept for Moses in the plains of Moab thirty days: so the days of weeping and mourning for Moses were ended. |
9 ሙሴም እጆቹን ስለ ጫነበት የነዌ ልጅ ኢያሱ የጥበብን መንፈስ ተሞላ የእስራኤልም ልጆች ታዘዙለት፥ እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ። |
9 And Joshua the son of Nun was full of the spirit of wisdom; for Moses had laid his hands upon him: and the children of Israel hearkened unto him, and did as the Lord commanded Moses. |
10 እግዚአብሔርን ፊት ለፊት እንዳወቀው እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ ከዚያ ወዲህ በእስራኤል ዘንድ አልተነሣም |
10 And there arose not a prophet since in Israel like unto Moses, whom the Lord knew face to face, |
11 በግብፅ ምድር በፈርዖንና በባሪያዎቹ ሁሉ ላይ በምድሪቱም ሁሉ ላይ ምልክትንና ድንቅን ያደርግ ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ላከው ያለ፥ |
11 In all the signs and the wonders, which the Lord sent him to do in the land of Egypt to Pharaoh, and to all his servants, and to all his land, |
12 በእስራኤል ሁሉ ፊት በጸናች እጅ ሁሉና በታላቅ ማስደንገጥ ሁሉ እንዳደረገው እንደ ሙሴ ያለ አልተነሣም። |
12 And in all that mighty hand, and in all the great terror which Moses shewed in the sight of all Israel. |