መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David #102
In Amharic and English
መዝሙረ ዳዊት 102 |
Psalm 102 |
1 አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማኝ፥ ጩኸቴም ወደ አንተ ይድረስ። |
1 Hear my prayer, O Lord, and let my cry come unto thee. |
2 በመከራዬ ቀን ፊትህን ከኔ አትመልስ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል በጠራሁህ ቀን ፈጥነህ ስማኝ። |
2 Hide not thy face from me in the day when I am in trouble; incline thine ear unto me: in the day when I call answer me speedily. |
3 ዘመኔ እንደ ጢስ አልቃለችና፥ አጥንቶቼም እንደ መቃጠያ ተቃጥለዋልና። |
3 For my days are consumed like smoke, and my bones are burned as an hearth. |
4 እህል መብላት ተረስቶኛልና ተቀሠፍሁ ልቤም እንደ ሣር ደረቀ። |
4 My heart is smitten, and withered like grass; so that I forget to eat my bread. |
5 ከጩኸቴ ድምፅ የተነሣ አጥንቶቼ ከሥጋዬ ጋር ተጣበቁ። |
5 By reason of the voice of my groaning my bones cleave to my skin. |
6 እንደ ምድረ በዳ እርኩም መሰልሁ በፈረሰ ቤት እንዳለ እንደ ጕጕት ሆንሁ። |
6 I am like a pelican of the wilderness: I am like an owl of the desert. |
7 ተጋሁ፥ በሰገነትም እንደሚኖር ብቸኛ ድንቢጥ ሆንሁ። |
7 I watch, and am as a sparrow alone upon the house top. |
8 ጠላቶቼ ሁልጊዜ ይሰድቡኛል፥ የሚያሳድዱኝም ተማማሉብኝ። |
8 Mine enemies reproach me all the day; and they that are mad against me are sworn against me. |
9 አመድን እንደ እህል ቅሜአለሁና፥ መጠጤንም ከእንባዬ ጋር ቀላቅያለሁና፥ |
9 For I have eaten ashes like bread, and mingled my drink with weeping, |
10 ከቍጣህና ከመዓትህም የተነሣ አንሥተኸኛልና፥ ጥለኸኝማልና። |
10 Because of thine indignation and thy wrath: for thou hast lifted me up, and cast me down. |
11 ዘመኖቼ እንደ ጥላ አዘንብለዋል እኔም እንደ ሣር ደርቄአለሁ። |
11 My days are like a shadow that declineth; and I am withered like grass. |
12 አንተ ግን፥ አቤቱ፥ ለዘላለም ትኖራለህ፥ መታሰቢያህም ለልጅ ልጅ ነው። |
12 But thou, O Lord, shalt endure for ever; and thy remembrance unto all generations. |
13 አንተ ተነሥ ጽዮንንም ይቅር በላት፥ የምሕረትዋ ጊዜ ነውና፥ ዘመንዋም ደርሶአልና |
13 Thou shalt arise, and have mercy upon Zion: for the time to favour her, yea, the set time, is come. |
14 ባሪያዎችህም ድንጋዮችዋን ወድደዋልና፥ ለመሬትዋም አዝነዋልና። |
14 For thy servants take pleasure in her stones, and favour the dust thereof. |
15 አቤቱ፥ አሕዛብ ስምህን፥ ነገሥታትም ሁሉ ክብርህን ይፈራሉ |
15 So the heathen shall fear the name of the Lord, and all the kings of the earth thy glory. |
16 እግዚአብሔር ጽዮንን ይሠራታልና፥ በክብሩም ይገለጣልና። |
16 When the Lord shall build up Zion, he shall appear in his glory. |
17 ወደ ችግረኞች ጸሎት ተመለከተ፥ ልመናቸውንም አልናቀም። |
17 He will regard the prayer of the destitute, and not despise their prayer. |
18 ይህ ለሚመጣ ትውልድ ይጻፍ፥ የሚፈጠርም ሕዝብ ለእግዚአብሔር እልል ይላል |
18 This shall be written for the generation to come: and the people which shall be created shall praise the Lord. |
19 እግዚአብሔር ከመቅደሱ ከፍታ ሆኖ ተመልክቶአልና፥ ከሰማይ ሆኖ ምድርን አይቶአልና |
19 For he hath looked down from the height of his sanctuary; from heaven did the Lord behold the earth; |
20 የእስረኞችን ጩኸት ይሰማ ዘንድ፥ ሊገድሉ የተፈረደባቸውን ያድን ዘንድ |
20 To hear the groaning of the prisoner; to loose those that are appointed to death; |
21 የእግዚአብሔርን ስም በጽዮን ምስጋናውንም በኢየሩሳሌም ይናገሩ ዘንድ |
21 To declare the name of the Lord in Zion, and his praise in Jerusalem; |
22 አሕዛብ በአንድነት በተሰበሰቡ ጊዜ መንግሥታትም ለእግዚአብሔር ይገዙ ዘንድ። |
22 When the people are gathered together, and the kingdoms, to serve the Lord. |
23 በኃይሉ ጎዳና መለሰለት። የዘመኔን አነስተኛነት ንገረኝ። |
23 He weakened my strength in the way; he shortened my days. |
24 በዘመኔ እኵሌታ አትውሰደኝ ዓመቶችህ ለልጅ ልጅ ናቸው። |
24 I said, O my God, take me not away in the midst of my days: thy years are throughout all generations. |
25 አቤቱ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማያትም የእጅህ ሥራ ናቸው። |
25 Of old hast thou laid the foundation of the earth: and the heavens are the work of thy hands. |
26 እነርሱ ይጠፋሉ፥ አንተ ግን ትኖራለህ ሁላቸው እንደ ልብስ ያረጃሉ፥ እንደ መጐናጸፊያም ትለውጣቸዋለህ፥ ይለወጡማል |
26 They shall perish, but thou shalt endure: yea, all of them shall wax old like a garment; as a vesture shalt thou change them, and they shall be changed: |
27 አንተ ግን ያው አንተ ነህ፥ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም። |
27 But thou art the same, and thy years shall have no end. |
28 የባሪያዎችህም ልጆች ይኖራሉ፥ ዘራቸውም ለዘላለም ትጸናለች። |
28 The children of thy servants shall continue, and their seed shall be established before thee. |