ኦሪት ዘኍልቍ Orit ZeHwilQwi
Numbers / Bamidbar #24
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

 

ኦሪት ዘኍልቍ 24

Numbers 24

1 በለዓምም እግዚአብሔር እስራኤልን ይባርክ ዘንድ እንዲወድድ ባየ ጊዜ፥ አስቀድሞ ያደርግ የነበረውን አስማት ይሻ ዘንድ አልሄደም ነገር ግን ወደ ምድረ በዳ ፊቱን አቀና።

1 And when Balaam saw that it pleased the Lord to bless Israel, he went not, as at other times, to seek for enchantments, but he set his face toward the wilderness.

2 በለዓምም ዓይኑን አንሥቶ እስራኤል በየነገዱ ተቀምጦ አየ የእግዚአብሔርም መንፈስ በላዩ መጣ።

2 And Balaam lifted up his eyes, and he saw Israel abiding in his tents according to their tribes; and the spirit of God came upon him.

3 ምሳሌውን ይመስል ጀመር፥እንዲህም አለ፦ የቢዖር ልጅ በለዓም እንዲህ ይላል፥ ዓይኖቹ የተከፈቱለት ሰው እንዲህ ይላል፤

3 And he took up his parable, and said, Balaam the son of Beor hath said, and the man whose eyes are open hath said:

4 የእግዚአብሔርን ቃል የሚሰማ፥ ሁሉን የሚችል የአምላክን ራእይ የሚያይ፥ የወደቀው፥ ዓይኖቹም የተከፈቱለት እንዲህ ይላል።

4 He hath said, which heard the words of God, which saw the vision of the Almighty, falling into a trance, but having his eyes open:

5 ያዕቆብ ሆይ፥ ድንኳኖችህ፥ እስራኤል ሆይ ማደሪያዎችህ ምንኛ ያምራሉ!

5 How goodly are thy tents, O Jacob, and thy tabernacles, O Israel!

6 እንደ ሸለቆች፥ በወንዝ ዳር እንዳሉ አትክልቶች፥ እግዚአብሔር እንደ ተከለው እሬት በውኃም ዳር እንዳሉ ዝግባዎች ተዘርግተዋል።

6 As the valleys are they spread forth, as gardens by the river’s side, as the trees of lign aloes which the Lord hath planted, and as cedar trees beside the waters.

7 ከማድጋዎቹ ውኃ ይፈስሳል፥ ዘሩም በብዙ ውኆች ይሆናል፥ ንጉሡም ከአጋግ ይልቅ ከፍ ከፍ ይላል፥ መንግሥቱም ይከበራል።

7 He shall pour the water out of his buckets, and his seed shall be in many waters, and his king shall be higher than Agag, and his kingdom shall be exalted.

8 እግዚአብሔርም ከግብፅ አውጥቶታል ጕልበቱ አንድ ቀንድ እንዳለው ነው፤ ጠላቶቹን አሕዛብን ይበላል፥ አጥንቶቻቸውንም ይሰባብራል፥ በፍላጾቹም ይወጋቸዋል።

8 God brought him forth out of Egypt; he hath as it were the strength of an unicorn: he shall eat up the nations his enemies, and shall break their bones, and pierce them through with his arrows.

9 እንደ አንበሳ ዐርፎ ተኝቶአል፥ እንደ እንስቲቱም አንበሳ ተጋድሞአል፤ ማን ያስነሣዋል? የሚመርቅህ ሁሉ የተመረቀ ይሁን፥ የሚረግምህም ሁሉ የተገመ ይሁን።

9 He couched, he lay down as a lion, and as a great lion: who shall stir him up? Blessed is he that blesseth thee, and cursed is he that curseth thee.

10 የባላቅም ቍጣ በበለዓም ላይ ነደደ እጆቹንም አጨበጨበ ባላቅም በለዓምን። ጠላቶቼን ትረግም ዘንድ ጠራሁህ፥ እነሆም፥ ሦስት ጊዜ ፈጽመህ መረቅሃቸው አሁንም እንግዲህ ወደ ስፍራህ ሽሽ

10 And Balak’s anger was kindled against Balaam, and he smote his hands together: and Balak said unto Balaam, I called thee to curse mine enemies, and, behold, thou hast altogether blessed them these three times.

11 እኔ አከብርህ ዘንድ ወድጄ ነበር እግዚአብሔር ግን፥ እነሆ፥ ክብርህን ከለከለ አለው።

11 Therefore now flee thou to thy place: I thought to promote thee unto great honour; but, lo, the Lord hath kept thee back from honour.

12-13 በለዓምም ባላቅን አለው። ባላቅ በቤቱ የሞላውን ብርና ወርቅ ቢሰጠኝ፥ መልካሙን ወይም ክፉውን ከልቤ ለማድረግ የእግዚአብሔርን ቃል እተላለፍ ዘንድ አይቻለኝም እግዚአብሔር የተናገረውን እርሱን እናገራለሁ ብዬ ወደ እኔ ለላክሃቸው መልእክተኞች አልተናገርኋቸውምን?

12 And Balaam said unto Balak, Spake I not also to thy messengers which thou sentest unto me, saying,
13 If Balak would give me his house full of silver and gold, I cannot go beyond the commandment of the Lord, to do either good or bad of mine own mind; but what the Lord saith, that will I speak?

14 አሁንም፥ እነሆ፥ ወደ ሕዝቤ እሄዳለሁ ና፥ ይህ ሕዝብ በኋለኛው ዘመን በሕዝብህ ላይ የሚያደርገውን እነግርሃለሁ።

14 And now, behold, I go unto my people: come therefore, and I will advertise thee what this people shall do to thy people in the latter days.

15 ምሳሌውንም ይመስል ጀመር፥እንዲህም አለ፦ የቢዖር ልጅ በለዓም እንዲህ ይላል፥ ዓይኖቹም የተከፈቱለት ሰው እንዲህ ይላል፤

15 And he took up his parable, and said, Balaam the son of Beor hath said, and the man whose eyes are open hath said:

16 የእግዚአብሔርን ቃል የሚሰማ፥ የልዑልንም እውቀት የሚያውቅ፥ ሁሉን የሚችል የአምላክን ራእይ የሚያይ፥ የወደቀው፥ ዓይኖቹም የተከፈቱለት እንዲህ ይላል።

16 He hath said, which heard the words of God, and knew the knowledge of the most High, which saw the vision of the Almighty, falling into a trance, but having his eyes open:

17 አየዋለሁ፥ አሁን ግን አይደለም እመለከተዋለሁ፥ በቅርብ ግን አይደለም፤ ከያዕቆብ ኮከብ ይወጣል፥ ከእስራኤል በትር ይነሣል፥ የሞዓብንም ማዕዘኖች ይመታል፥ የሤትንም ልጆች ያጠፋል።

17 I shall see him, but not now: I shall behold him, but not nigh: there shall come a Star out of Jacob, and a Sceptre shall rise out of Israel, and shall smite the corners of Moab, and destroy all the children of Sheth.

18 ኤዶምያስም ርስቱ ይሆናል፥ ጠላቱ ሴይር ደግሞ ርስቱ ይሆናል፤ እስራኤልም በኃይል ያደርጋል።

18 And Edom shall be a possession, Seir also shall be a possession for his enemies; and Israel shall do valiantly.

19 ከያዕቆብም የሚወጣ ገዥ ይሆናል፥ ከከተማውም የቀሩትን ያጠፋል።

19 Out of Jacob shall come he that shall have dominion, and shall destroy him that remaineth of the city.

20 አማሌቅንም አይቶ ምሳሌውን ይመስል ጀመር፥እንዲህም አለ፦ አማሌቅ የአሕዛብ አለቃ ነበረ፤ ፍጻሜው ግን ወደ ጥፋት ይመጣል።

20 And when he looked on Amalek, he took up his parable, and said, Amalek was the first of the nations; but his latter end shall be that he perish for ever.

21 ቄናውያንንም አይቶ ምሳሌውን ይምስል ጀመር፥እንዲህም አለ፦ ማደሪያህ የጸና ነው፥ ጎጆህም በአምባ ላይ ተሠርቶአል፤

21 And he looked on the Kenites, and took up his parable, and said, Strong is thy dwellingplace, and thou puttest thy nest in a rock.

22 ነገር ግን አሦር እስኪማርክህ ድረስ ቄናዊው ለጥፋት ይሆናል።

22 Nevertheless the Kenite shall be wasted, until Asshur shall carry thee away captive.

23 ምሳሌውንም ይመስል ጀመር፥እንዲህም አለ፦ እግዚአብሔር ይህን ሲያደርግ አወይ! ማን በሕይወት ይኖራል?

23 And he took up his parable, and said, Alas, who shall live when God doeth this!

24 ከኪቲም ዳርቻ መርከቦች ይመጣሉ፥ አሦርንም ያስጨንቃሉ፥ ዔቦርንም ያስጨንቃሉ፤ እርሱም ደግሞ ወደ ጥፋት ይመጣል።

24 And ships shall come from the coast of Chittim, and shall afflict Asshur, and shall afflict Eber, and he also shall perish for ever.

25 በለዓምም ተነሣ፥ ተመልሶም ወደ ስፍራው ሄደ ባላቅም ደግሞ መንገዱን ሄደ።

25 And Balaam rose up, and went and returned to his place: and Balak also went his way.