ኦሪት ዘኍልቍ Orit ZeHwilQwi
Numbers / Bamidbar #25
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

 

ኦሪት ዘኍልቍ 25

Numbers 25

1 እስራኤልም በሰጢም ተቀመጡ ሕዝቡም ከሞዓብ ልጆች ጋር ያመነዝሩ ጀመር።

1 And Israel abode in Shittim, and the people began to commit whoredom with the daughters of Moab.

2 ሕዝቡንም ወደ አምላኮቻቸው መሥዋዕት ጠሩ ሕዝቡም በሉ፥ ወደ አምላኮቻቸውም ሰገዱ።

2 And they called the people unto the sacrifices of their gods: and the people did eat, and bowed down to their gods.

3 እስራኤልም ብዔልፌጎርን ተከተለ የእግዚአብሔርም ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ።

3 And Israel joined himself unto Baal–peor: and the anger of the Lord was kindled against Israel.

4 እግዚአብሔርም ሙሴን፦ የእግዚአብሔር የቍጣው ጽናት ከእስራኤል እንዲመለስ የሕዝቡን አለቆች ሁሉ ወስደህ በፀሐዩ ፊት ወደ እግዚአብሔር ስቀላቸው አለው።

4 And the Lord said unto Moses, Take all the heads of the people, and hang them up before the Lord against the sun, that the fierce anger of the Lord may be turned away from Israel.

5 ሙሴም የእስራኤልን ዳኞች። እናንተ ሁሉ ብዔልፌጎርን የተከተሉትን ሰዎቻችሁን ግደሉ አላቸው።

5 And Moses said unto the judges of Israel, Slay ye every one his men that were joined unto Baal–peor.

6 እነሆም፥ ከእስራኤል ልጆች አንዱ መጥቶ በሙሴና በእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ ፊት ምድያማዊቱን አንዲቱን ሴት ወደ ወንድሞቹ አመጣት እነርሱም በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ያለቅሱ ነበር።

6 And, behold, one of the children of Israel came and brought unto his brethren a Midianitish woman in the sight of Moses, and in the sight of all the congregation of the children of Israel, who were weeping before the door of the tabernacle of the congregation.

7 የካህኑም የአሮን ልጅ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ ባየው ጊዜ ከማኅበሩ መካከል ተነሥቶ በእጁ ጦር አነሣ

7 And when Phinehas, the son of Eleazar, the son of Aaron the priest, saw it, he rose up from among the congregation, and took a javelin in his hand;

8 ያንንም የእስራኤልን ሰው ተከትሎ ወደ ድንኳኑ ገባ። እስራኤላዊውንም ሰውና ሴቲቱን ሁለቱን ሆዳቸውን ወጋቸው። ከእስራኤልም ልጆች መቅሠፍቱ ተከለከለ።

8 And he went after the man of Israel into the tent, and thrust both of them through, the man of Israel, and the woman through her belly. So the plague was stayed from the children of Israel.

9 በመቅሠፍትም የሞተው ሀያ አራት ሺህ ነበረ።

9 And those that died in the plague were twenty and four thousand.

10 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው።

10 And the Lord spake unto Moses, saying,

11 የካህኑ የአሮን ልጅ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ በቅንዓቴ በመካከላቸው ቀንቶአልና ቍጣዬን ከእስራኤል ልጆች መለሰ እኔም የእስራኤልን ልጆች በቅንዓቴ አላጠፋሁም።

11 Phinehas, the son of Eleazar, the son of Aaron the priest, hath turned my wrath away from the children of Israel, while he was zealous for my sake among them, that I consumed not the children of Israel in my jealousy.

12 ስለዚህ፥ እነሆ፥ የሰላሜን ቃል ኪዳን እሰጠዋለሁ።

12 Wherefore say, Behold, I give unto him my covenant of peace:

13 ለአምላኩም ቀንቶአልና፥ ለእስራኤልም ልጆች አስተስርዮአልና ለእርሱ ከእርሱም በኋላ ለዘሩ ለዘላለም ክህነት ቃል ኪዳን ይሆንለታል።

13 And he shall have it, and his seed after him, even the covenant of an everlasting priesthood; because he was zealous for his God, and made an atonement for the children of Israel.

14 ከምድያማዊቱም ጋር የተገደለው የእስራኤላዊው ሰው ስም ዘንበሪ ነበረ የአባቱ ቤት አለቃ የስምዖናውያን የሆነ የሰሉ ልጅ ነበረ።

14 Now the name of the Israelite that was slain, even that was slain with the Midianitish woman, was Zimri, the son of Salu, a prince of a chief house among the Simeonites.

15 የተገደለችውም ምድያማዊት ስምዋ ከስቢ ነበረ እርስዋም የሱር ልጅ ነበረች እርሱም በምድያም ዘንድ የአባቱ ቤት ወገን አለቃ ነበረ።

15 And the name of the Midianitish woman that was slain was Cozbi, the daughter of Zur; he was head over a people, and of a chief house in Midian.

16 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው።

16 And the Lord spake unto Moses, saying,

17-18 በፌጎር በመቅሠፍቱ ቀን ስለተገደለችው ስለ ምድያም አለቃ ልጅ ስለ እኅታቸው ስለ ከስቢ በፌጎር ምክንያት በሸነገሉአችሁ ሽንገላ አስጨንቀዋችኋልና ምድያማውያንን አስጨንቁአቸው ግደሉአቸውም።

17 Vex the Midianites, and smite them:
18 For they vex you with their wiles, wherewith they have beguiled you in the matter of Peor, and in the matter of Cozbi, the daughter of a prince of Midian, their sister, which was slain in the day of the plague for Peor’s sake.