ኦሪት ዘኍልቍ Orit ZeHwilQwi
Numbers / Bamidbar #26
In Amharic and English
|
ኦሪት ዘኍልቍ 26 |
Numbers 26 |
1 እንዲህም ሆነ መቅሠፍቱ ከሆነ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴንና የካህኑን የአሮን ልጅ አልዓዛርን። |
1 And it came to pass after the plague, that the Lord spake unto Moses and unto Eleazar the son of Aaron the priest, saying, |
2 ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለውን፥ በእስራኤል ወደ ሰልፍ የሚወጣውን ሁሉ፥ የእስራኤልን ልጆች ማኅበር ሁሉ በየአባቶቻቸው ቤት ቍጠሩ ብሎ ተናገራቸው። |
2 Take the sum of all the congregation of the children of Israel, from twenty years old and upward, throughout their fathers’ house, all that are able to go to war in Israel. |
3 ሙሴና ካህኑ አልዓዛር በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ለፊት በሞዓብ ሜዳ ላይ። |
3 And Moses and Eleazar the priest spake with them in the plains of Moab by Jordan near Jericho, saying, |
4 እግዚአብሔር ሙሴን ከግብፅም ምድር የወጡትን የእስራኤልን ልጆች እንዳዘዛቸው፥ ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለውን ሕዝቡን ቍጠሩ ብለው ተናገሩአቸው። |
4 Take the sum of the people, from twenty years old and upward; as the Lord commanded Moses and the children of Israel, which went forth out of the land of Egypt. |
5 የእስራኤል በኵር ሮቤል የሮቤል ልጆች ከሄኖኅ የሄኖኀውያን ወገን፥ ከፈሉስ የፈሉሳውያን ወገን፥ |
5 Reuben, the eldest son of Israel: the children of Reuben; Hanoch, of whom cometh the family of the Hanochites: of Pallu, the family of the Palluites: |
6 ከአስሮን የአስሮናውያን ወገን፥ ከከርሚ የከርማውያን ወገን። |
6 Of Hezron, the family of the Hezronites: of Carmi, the family of the Carmites. |
7 እነዚህ የሮቤላውያን ወገኖች ናቸው ከእነርሱም የተቈጠሩት አርባ ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ሠላሳ ነበሩ። |
7 These are the families of the Reubenites: and they that were numbered of them were forty and three thousand and seven hundred and thirty. |
8 የፈሉስም ልጆች ኤልያብ። |
8 And the sons of Pallu; Eliab. |
9 የኤልያብም ልጆች ነሙኤል፥ ዳታን፥ አቤሮን እነዚህ ዳታንና አቤሮን ከማኅበሩ የተመረጡ ነበሩ ከቆሬ ወገን ጋር በእግዚአብሔር ላይ ባመፁ ጊዜ ሙሴንና አሮንን ተጣሉ |
9 And the sons of Eliab; Nemuel, and Dathan, and Abiram. This is that Dathan and Abiram, which were famous in the congregation, who strove against Moses and against Aaron in the company of Korah, when they strove against the Lord: |
10 ያም ወገን በሞተ ጊዜ ምድሪቱ አፍዋን ከፍታ ከቆሬ ጋር ዋጠቻቸው በዚያም ጊዜ እሳቲቱ ሁለት መቶ አምሳውን ሰዎች አቃጠለቻቸው እነርሱም ለምልክት ሆኑ። |
10 And the earth opened her mouth, and swallowed them up together with Korah, when that company died, what time the fire devoured two hundred and fifty men: and they became a sign. |
11 የቆሬ ልጆች ግን አልሞቱም። |
11 Notwithstanding the children of Korah died not. |
12 የስምዖን ልጆች በየወገናቸው ከነሙኤል የነሙኤላውያን ወገን፥ ከያሚን የያሚናውያን ወገን፥ ከያኪን የያኪናውያን ወገን፥ ከዛራ የዛራውያን ወገን፥ |
12 The sons of Simeon after their families: of Nemuel, the family of the Nemuelites: of Jamin, the family of the Jaminites: of Jachin, the family of the Jachinites: |
13 ከሳኡል የሳኡላውያን ወገን። |
13 Of Zerah, the family of the Zarhites: of Shaul, the family of the Shaulites. |
14 እነዚህ የስምዖናውያን ወገኖች ናቸው ሀያ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ። |
14 These are the families of the Simeonites, twenty and two thousand and two hundred. |
15 የጋድ ልጆች በየወገናቸው ከጽፎን የጽፎናውያን ወገን፥ ከሐጊ የሐጋውያን ወገን፥ |
15 The children of Gad after their families: of Zephon, the family of the Zephonites: of Haggi, the family of the Haggites: of Shuni, the family of the Shunites: |
16 ከሹኒ የሹናውያን ወገን፥ ከኤስናን የኤስናናውያን ወገን፥ ከዔሪ የዔራውያን ወገን፥ |
16 Of Ozni, the family of the Oznites: of Eri, the family of the Erites: |
17 ከአሮድ የአሮዳውያን ወገን፥ ከአርኤሊ የአርኤላውያን ወገን። |
17 Of Arod, the family of the Arodites: of Areli, the family of the Arelites. |
18 እነዚህ የጋድ ልጆች ወገኖች ናቸው ከእነርሱም የተቈጠሩት አርባ ሺህ አምስት መቶ ነበሩ። |
18 These are the families of the children of Gad according to those that were numbered of them, forty thousand and five hundred. |
19 የይሁዳ ልጆች ዔርና አውናን ዔርና አውናንም በከነዓን ምድር ሞቱ። |
19 The sons of Judah were Er and Onan: and Er and Onan died in the land of Canaan. |
20 የይሁዳም ልጆች በየወገናቸው ከሴሎም የሴሎማውያን ወገን፥ ከፋሬስ የፋሬሳውያን ወገን፥ ከዛራ የዛራውያን ወገን። |
20 And the sons of Judah after their families were; of Shelah, the family of the Shelanites: of Pharez, the family of the Pharzites: of Zerah, the family of the Zarhites. |
21 የፋሬስም ልጆች ከኤስሮም የኤስሮማውያን ወገን፥ ከሐሙል የሐሙላውያን ወገን። |
21 And the sons of Pharez were; of Hezron, the family of the Hezronites: of Hamul, the family of the Hamulites. |
22 እነዚህ የይሁዳ ወገኖች ናቸው ከእነርሱም የተቈጠሩት ሰባ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ነበሩ። |
22 These are the families of Judah according to those that were numbered of them, threescore and sixteen thousand and five hundred. |
23 የይሳኮር ልጆች በየወገናቸው ከቶላ የቶላውያን ወገን፥ ከፉዋ የፉዋውያን ወገን፥ |
23 Of the sons of Issachar after their families: of Tola, the family of the Tolaites: of Pua, the family of the Punites: |
24 ከያሱብ የያሱባውያን ወገን፥ ከሺምሮን የሺምሮናውያን ወገን። |
24 Of Jashub, the family of the Jashubites: of Shimron, the family of the Shimronites. |
25 እነዚህ የይሳኮር ወገኖች ናቸው ከእነርሱም የተቈጠሩት ስድሳ አራት ሺህ ሦስት መቶ ነበሩ። |
25 These are the families of Issachar according to those that were numbered of them, threescore and four thousand and three hundred. |
26 የዛብሎን ወገኖች በየወገናቸው ከሴሬድ የሴሬዳውያን ወገን፥ ከኤሎን የኤሎናውያን ወገን፥ ከያሕልኤል የያሕልኤላውያን ወገን። |
26 Of the sons of Zebulun after their families: of Sered, the family of the Sardites: of Elon, the family of the Elonites: of Jahleel, the family of the Jahleelites. |
27 እነዚህ የዛብሎናውያን ወገኖች ናቸው ከእነርሱም የተቈጠሩት ስድሳ ሺህ አምስት መቶ ነበሩ። |
27 These are the families of the Zebulunites according to those that were numbered of them, threescore thousand and five hundred. |
28 የዮሴፍ ልጆች በየወገናቸው ምናሴና ኤፍሬም። |
28 The sons of Joseph after their families were Manasseh and Ephraim. |
29 የምናሴ ልጆች ከማኪር የማኪራውያን ወገን ማኪርም ገለዓድን ወለደ ከገለዓድ የገልዓዳውያን ወገን። |
29 Of the sons of Manasseh: of Machir, the family of the Machirites: and Machir begat Gilead: of Gilead come the family of the Gileadites. |
30 የገለዓድ ልጆች እነዚህ ናቸው ከኢዔዝር የኢዔዝራውያን ወገን፥ ከኬሌግ የኬሌጋውያን ወገን፥ |
30 These are the sons of Gilead: of Jeezer, the family of the Jeezerites: of Helek, the family of the Helekites: |
31 ከአሥሪኤል የአሥሪኤላውያን ወገን፥ |
31 And of Asriel, the family of the Asrielites: and of Shechem, the family of the Shechemites: |
32 ከሴኬም የሴኬማውያን ወገን፥ ከሸሚዳ የሸሚዳውያን ወገን፥ ከኦፌር የኦፌራውያን ወገን። |
32 And of Shemida, the family of the Shemidaites: and of Hepher, the family of the Hepherites. |
33 የኦፌርም ልጅ ሰለጰዓድ ሴቶች ልጆች እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም የሰለጰዓድም የሴቶች ልጆቹ ስም ማህለህ፥ ኑዓ፥ ዔግላ፥ ሚልካ፥ ቲርጻ ነበረ። |
33 And Zelophehad the son of Hepher had no sons, but daughters: and the names of the daughters of Zelophehad were Mahlah, and Noah, Hoglah, Milcah, and Tirzah. |
34 እነዚህ የምናሴ ወገኖች ናቸው ከእነርሱም የተቈጠሩት አምሳ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ። |
34 These are the families of Manasseh, and those that were numbered of them, fifty and two thousand and seven hundred. |
35 በየወገናቸው የኤፍሬም ልጆች እነዚህ ናቸው ከሱቱላ የሱቱላውያን ወገን፥ ከቤኬር የቤኬራውያን ወገን፥ ከታሐን የታሐናውያን ወገን። |
35 These are the sons of Ephraim after their families: of Shuthelah, the family of the Shuthalhites: of Becher, the family of the Bachrites: of Tahan, the family of the Tahanites. |
36 እነዚህ የሱቱላ ልጆች ናቸው ከዔዴን የዔዴናውያን ወገን። ከዔዴን የዔዴናውያና ወገን። |
36 And these are the sons of Shuthelah: of Eran, the family of the Eranites. |
37 እነዚህ የኤፍሬም ልጆች ወገኖች ናቸው ከእነርሱም የተቈጠሩት ሠላሳ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ነበሩ። በየወገናቸው የዮሴፍ ልጆች እነዚህ ናቸው። |
37 These are the families of the sons of Ephraim according to those that were numbered of them, thirty and two thousand and five hundred. These are the sons of Joseph after their families. |
38 የብንያም ልጆች በየወገናቸው ከቤላ የቤላውያን ወገን፥ ከአስቤል የአስቤላውያን ወገን፥ ከአኪራን የአኪራናውያን ወገን፥ ከሶፋን የሶፋናውያን ወገን፥ |
38 The sons of Benjamin after their families: of Bela, the family of the Belaites: of Ashbel, the family of the Ashbelites: of Ahiram, the family of the Ahiramites: |
39 ከሑፋም የሑፋማውያን ወገን። |
39 Of Shupham, the family of the Shuphamites: of Hupham, the family of the Huphamites. |
40 የቤላም ልጆች አርድና ናዕማን ከአርድ የአርዳውያን ወገን፥ ከናዕማን የናዕማናውያን ወገን። |
40 And the sons of Bela were Ard and Naaman: of Ard, the family of the Ardites: and of Naaman, the family of the Naamites. |
41 በየወገናቸው የብንያም ልጆች እነዚህ ናቸው ከእነርሱም የተቈጠሩት አርባ አምስት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ። |
41 These are the sons of Benjamin after their families: and they that were numbered of them were forty and five thousand and six hundred. |
42 በየወገናቸው የዳን ልጆች እነዚህ ናቸው ከሰምዔ የሰምዔያውያን ወገን በየወገናቸው የዳን ወገኖች እነዚህ ናቸው። |
42 These are the sons of Dan after their families: of Shuham, the family of the Shuhamites. These are the families of Dan after their families. |
43 የሰምዔያውያን ወገኖች ሁሉ ከእነርሱ እንደ ተቈጠሩ ስድሳ አራት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። |
43 All the families of the Shuhamites, according to those that were numbered of them, were threescore and four thousand and four hundred. |
44 የአሴር ልጆች በየወገናቸው ከዪምና የዪምናውያን ወገን፥ ከየሱዋ የየሱዋውያን ወገን፥ ከበሪዓ የበሪዓውያን ወገን። |
44 Of the children of Asher after their families: of Jimna, the family of the Jimnites: of Jesui, the family of the Jesuites: of Beriah, the family of the Beriites. |
45 ከበሪዓ ልጆች ከሔቤር የሔቤራውያን ወገን፥ ከመልኪኤል የመልኪኤላውያን ወገን። |
45 Of the sons of Beriah: of Heber, the family of the Heberites: of Malchiel, the family of the Malchielites. |
46 የአሴርም የሴት ልጁ ስም ሤራሕ ነበረ። |
46 And the name of the daughter of Asher was Sarah. |
47 እነዚህ የአሴር ልጆች ወገኖች ናቸው ከእነርሱም የተቈጠሩት አምሳ ሦስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። |
47 These are the families of the sons of Asher according to those that were numbered of them; who were fifty and three thousand and four hundred. |
48 የንፍታሌም ልጆች በየወገናቸው ከያሕጽኤል የያሕጽኤላውያን ወገን፥ ከጉኒ የጉናውያን ወገን፥ |
48 Of the sons of Naphtali after their families: of Jahzeel, the family of the Jahzeelites: of Guni, the family of the Gunites: |
49 ከዬጽር የዬጽራውያን ወገን፥ ከሺሌም የሺሌማውያን ወገን። |
49 Of Jezer, the family of the Jezerites: of Shillem, the family of the Shillemites. |
50 በየወገናቸው የንፍታሌም ወገኖች እነዚህ ናቸው ከእነርሱም የተቈጠሩት አርባ አምስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። |
50 These are the families of Naphtali according to their families: and they that were numbered of them were forty and five thousand and four hundred. |
51 ከእስራኤል ልጆች የተቈጠሩት እነዚህ ናቸው ስድስት መቶ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሠላሳ ነበሩ። |
51 These were the numbered of the children of Israel, six hundred thousand and a thousand seven hundred and thirty. |
52 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው። |
52 And the Lord spake unto Moses, saying, |
53 ለእነዚህ በየስማቸው ቍጥር ምድሪቱ ርስት ሆና ትከፈላለች። |
53 Unto these the land shall be divided for an inheritance according to the number of names. |
54 ለብዙዎቹ እንደ ብዛታቸው፥ ለጥቂቶቹም እንደ ጥቂትነታቸው መጠን ርስትን ትሰጣቸዋለህ። ለሁሉ እንደ ቍጥራቸው መጠን ርስታቸው ይሰጣቸዋል። |
54 To many thou shalt give the more inheritance, and to few thou shalt give the less inheritance: to every one shall his inheritance be given according to those that were numbered of him. |
55 ነገር ግን ምድሪቱ በዕጣ ትከፈላለች እንደ አባቶቻቸው ነገድ ስም ይወርሳሉ። |
55 Notwithstanding the land shall be divided by lot: according to the names of the tribes of their fathers they shall inherit. |
56 በብዙዎችና በጥቂቶች መካከል ርስታቸው በዕጣ ትከፈላለች። |
56 According to the lot shall the possession thereof be divided between many and few. |
57 ከሌዋውያንም በየወገናቸው የተቈጠሩት እነዚህ ናቸው ከጌድሶን የጌድሶናውያን ወገን፥ ከቀዓት የቀዓታውያን ወገን፥ ከሜራሪ የሜራራውያን ወገን። |
57 And these are they that were numbered of the Levites after their families: of Gershon, the family of the Gershonites: of Kohath, the family of the Kohathites: of Merari, the family of the Merarites. |
58 እነዚህ የሌዊ ወገኖች ናቸው የሊብናውያን ወገን፥ የኬብሮናውያን ወገን፥ የሞሖላውያን ወገን፥ የሙሳውያን ወገን፥ የቆሬያውያን ወገን። ቀዓትም እንበረምን ወለደ። |
58 These are the families of the Levites: the family of the Libnites, the family of the Hebronites, the family of the Mahlites, the family of the Mushites, the family of the Korathites. And Kohath begat Amram. |
59 የእንበረም ሚስት ስም ዮካብድ ነበረ። እርስዋ በግብፅ ከሌዊ የተወለደች የሌዊ ልጅ ነበረች ለእንበረምም አሮንንና ሙሴን እኅታቸውንም ማርያምን ወለደችለት። |
59 And the name of Amram’s wife was Jochebed, the daughter of Levi, whom her mother bare to Levi in Egypt: and she bare unto Amram Aaron and Moses, and Miriam their sister. |
60 ለአሮንም ናዳብ፥ አብዩድ፥ አልዓዛር፥ ኢታምር ተወለዱለት። |
60 And unto Aaron was born Nadab, and Abihu, Eleazar, and Ithamar. |
61 በእግዚአብሔርም ፊት ሌላ እሳት ባቀረቡ ጊዜ ናዳብና አብዩድ ሞቱ። |
61 And Nadab and Abihu died, when they offered strange fire before the Lord. |
62 ከአንድ ወርም ጀምሮ ከዚያም በላይ ያሉ ወንዶች ሁሉ ከእነርሱ የተቈጠሩ ሀያ ሦስት ሺህ ነበሩ። ከእስራኤልም ልጆች መካከል ርስት አልተሰጣቸውምና ከእስራኤል ልጆች ጋር አልተቈጠሩም። |
62 And those that were numbered of them were twenty and three thousand, all males from a month old and upward: for they were not numbered among the children of Israel, because there was no inheritance given them among the children of Israel. |
63 በሞዓብ ሜዳ ላይ በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ለፊት ሲቈጥሩ፥ ሙሴና ካህኑ አልዓዛር የቈጠሩአቸው የእስራኤል ልጆች እነዚህ ናቸው። |
63 These are they that were numbered by Moses and Eleazar the priest, who numbered the children of Israel in the plains of Moab by Jordan near Jericho. |
64 ነገር ግን ሙሴና ካህኑ አሮን በሲና ምድረ በዳ የእስራኤልን ልጆች በቈጠሩአቸው ጊዜ ከነበሩት ከእነዚያ መካከል አንድም ሰው አልነበረም። |
64 But among these there was not a man of them whom Moses and Aaron the priest numbered, when they numbered the children of Israel in the wilderness of Sinai. |
65 እግዚአብሔር ስለ እነርሱ። በእውነት በምድረ በዳ ይሞታሉ ብሎ ተናግሮአልና። ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብ ከነዌም ልጅ ከኢያሱ በቀር ከእነርሱ አንድ ሰው ስንኳ አልቀረም። |
65 For the Lord had said of them, They shall surely die in the wilderness. And there was not left a man of them, save Caleb the son of Jephunneh, and Joshua the son of Nun. |