ኦሪት ዘኍልቍ Orit ZeHwilQwi
Numbers / Bamidbar #27
In Amharic and English
|
ኦሪት ዘኍልቍ 27 |
Numbers 27 |
1 ከዮሴፍ ልጅ ከምናሴ ወገኖች፥ የምናሴ ልጅ የማኪር ልጅ የገለዓድ ልጅ የኦፌር ልጅ የሰለጰዓድ ሴቶች ልጆች ቀረቡ የእነዚህም ሴቶች ልጆች ስም ማህለህ፥ ኑዓ፥ ዔግላ፥ ሚልካ፥ ቲርጻ ነበረ። |
1 Then came the daughters of Zelophehad, the son of Hepher, the son of Gilead, the son of Machir, the son of Manasseh, of the families of Manasseh the son of Joseph: and these are the names of his daughters; Mahlah, Noah, and Hoglah, and Milcah, and Tirzah. |
2 በመገናኛውም ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በሙሴና በካህኑ በአልዓዛር በአለቆቹም በማኅበሩም ሁሉ ፊት ቆመው። |
2 And they stood before Moses, and before Eleazar the priest, and before the princes and all the congregation, by the door of the tabernacle of the congregation, saying, |
3 አባታችን በምድረ በዳ ሞተ በራሱ ኃጢአት ሞተ እንጂ ከቆሬ ጋር በእግዚአብሔር ላይ በተሰበሰቡ ወገን መካከል አልነበረም ወንዶችም ልጆች አልነበሩትም። |
3 Our father died in the wilderness, and he was not in the company of them that gathered themselves together against the Lord in the company of Korah; but died in his own sin, and had no sons. |
4 ወንድ ልጅስ ባይኖረው የአባታችን ስም ከወገኑ መካከል ለምን ይጠፋል? በአባታችን ወንድሞች መካከል ርስትን ስጠን አሉ። |
4 Why should the name of our father be done away from among his family, because he hath no son? Give unto us therefore a possession among the brethren of our father. |
5 ሙሴም ነገራቸውን በእግዚአብሔር ፊት አቀረበ። |
5 And Moses brought their cause before the Lord. |
6 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው። |
6 And the Lord spake unto Moses, saying, |
7 የሰለጰዓድ ልጆች እውነት ተናግረዋል በአባታቸው ወንድሞች መካከል የርስት ድርሻ ስጣቸው የአባታቸውን ርስት ለእነርሱ አሳልፈህ ስጥ። |
7 The daughters of Zelophehad speak right: thou shalt surely give them a possession of an inheritance among their father’s brethren; and thou shalt cause the inheritance of their father to pass unto them. |
8 ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው። ሰው ቢሞት ወንድ ልጅም ባይኖረው፥ ርስቱ ለሴት ልጁ ይለፍ |
8 And thou shalt speak unto the children of Israel, saying, If a man die, and have no son, then ye shall cause his inheritance to pass unto his daughter. |
9 ሴት ልጅም ባትኖረው ርስቱን ለወንድሞቹ ስጡ |
9 And if he have no daughter, then ye shall give his inheritance unto his brethren. |
10 ወንድሞችም ባይኖሩት ርስቱን ለአባቱ ወንድሞች ስጡ |
10 And if he have no brethren, then ye shall give his inheritance unto his father’s brethren. |
11 የአባቱም ወንድሞች ባይኖሩት ከወገኑ ለቀረበ ዘመድ ርስቱን ስጡ እርሱም ይውረሰው እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘ ለእስራኤል ልጆች ሥርዓትና ፍርድ ይሁን። |
11 And if his father have no brethren, then ye shall give his inheritance unto his kinsman that is next to him of his family, and he shall possess it: and it shall be unto the children of Israel a statute of judgment, as the Lord commanded Moses. |
12 እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ ወደዚህ ወደ ዓባሪም ተራራ ውጣ፥ ለእስራኤልም ልጆች የሰጠኋትን ምድር እይ |
12 And the Lord said unto Moses, Get thee up into this mount Abarim, and see the land which I have given unto the children of Israel. |
13 ባየሃትም ጊዜ ወንድምህ አሮን እንደ ተከማቸ አንተ ደግሞ ወደ ወገንህ ትከማቻለህ። |
13 And when thou hast seen it, thou also shalt be gathered unto thy people, as Aaron thy brother was gathered. |
14 እናንተ በጺን ምድረ በዳ በማኅበሩ ጠብ በቃሌ ላይ ዐምፃችኋልና፥ በእነርሱም ፊት በውኃው ዘንድ አልቀደሳችሁኝምና። ይህም በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ ያለው የመሪባ ውኃ ነው። |
14 For ye rebelled against my commandment in the desert of Zin, in the strife of the congregation, to sanctify me at the water before their eyes: that is the water of Meribah in Kadesh in the wilderness of Zin. |
15 ሙሴም እግዚአብሔርን እንዲህ ብሎ ተናገረው። |
15 And Moses spake unto the Lord, saying, |
16-17 የእግዚአብሔር ማኅበር እረኛ እንደሌለው መንጋ እንዳይሆን፥ በፊታቸው የሚወጣውን በፊታቸውም የሚገባውን የሚያስወጣቸውንም የሚያስገባቸውንም ሰው የሥጋ ሁሉ መንፈስ አምላክ እግዚአብሔር በማኅበሩ ላይ ይሹመው። |
16 Let the Lord, the God of the spirits of all flesh, set a man over the congregation, |
18 እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ መንፈስ ያለበትን ሰው የነዌን ልጅ ኢያሱን ወስደህ እጅህን በላዩ ጫንበት |
18 And the Lord said unto Moses, Take thee Joshua the son of Nun, a man in whom is the spirit, and lay thine hand upon him; |
19 በካህኑ በአልዓዛርና በማኅበሩ ሁሉ ፊት አቁመው፥ እነርሱም እያዩ እዘዘው። |
19 And set him before Eleazar the priest, and before all the congregation; and give him a charge in their sight. |
20 የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ እንዲታዘዙት ከክብርህ አኑርበት። |
20 And thou shalt put some of thine honour upon him, that all the congregation of the children of Israel may be obedient. |
21 በካህኑም በአልዓዛር ፊት ይቁም እርሱም በእግዚአብሔር ፊት በኡሪም ፍርድ ይጠይቅለት እርሱ ከእርሱም ጋር የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በቃሉ ይውጡ፥ በቃሉም ይግቡ። |
21 And he shall stand before Eleazar the priest, who shall ask counsel for him after the judgment of Urim before the Lord: at his word shall they go out, and at his word they shall come in, both he, and all the children of Israel with him, even all the congregation. |
22 ሙሴም እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ ኢያሱንም ወስዶ በካህኑ በአልዓዛርና በማኅበሩ ሁሉ ፊት አቆመው |
22 And Moses did as the Lord commanded him: and he took Joshua, and set him before Eleazar the priest, and before all the congregation: |
23 እግዚአብሔርም በሙሴ እንደ ተናገረ፥ እጁን በላዩ ጫነበት፥ አዘዘውም። |
23 And he laid his hands upon him, and gave him a charge, as the Lord commanded by the hand of Moses. |