መጽሐፈ ምሳሌ | MeTsiHaFe MiSaLae
Proverbs of Solomon
| Mishlei Shlomo #13
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

መጽሐፈ ምሳሌ 13

Proverbs 13

1 ባለ አእምሮ ልጅ የአባቱን ተግሣጽ ይሰማል። ፌዘኛ ግን ተግሣጽን አይሰማም።

1 A wise son heareth his father’s instruction: but a scorner heareth not rebuke.

2 ሰው ከአፉ ፍሬ መልካምን ይበላል የዓመፀኞች ነፍስ ግን ግፍን ትሻለች።

2 A man shall eat good by the fruit of his mouth: but the soul of the transgressors shall eat violence.

3 አፉን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል ከንፈሩን የሚያሞጠሙጥ ግን ጥፋትን ያገኘዋል።

3 He that keepeth his mouth keepeth his life: but he that openeth wide his lips shall have destruction.

4 የታካች ሰው ነፍስ ትመኛለች አንዳችም አታገኝም የትጉ ነፍስ ግን ትጠግባለች።

4 The soul of the sluggard desireth, and hath nothing: but the soul of the diligent shall be made fat.

5 ጻድቅ ሐሰትን ይጠላል ኀጥእ ግን ያሳፍራል ያስነውራልም።

5 A righteous man hateth lying: but a wicked man is loathsome, and cometh to shame.

6 በመንገዱ ያለ ነውር የሚሄደውን ጽድቅ ይጠብቀዋል ኃጢአት ግን ኃጢአተኛውን ይጥለዋል።

6 Righteousness keepeth him that is upright in the way: but wickedness overthroweth the sinner.

7 ራሱን ባለጠጋ የሚያስመስል ሰው አለ፥ ነገር ግን አንዳች የለውም ራሱን ድሀ የሚያስመስል አለ፥ ነገር ግን እጅግ ባለጠግነት አለው።

7 There is that maketh himself rich, yet hath nothing: there is that maketh himself poor, yet hath great riches.

8 ለሰው ነፍስ ቤዛው ሀብቱ ነው ድሀ ግን ተግሣጽን አይሰማም።

8 The ransom of a man’s life are his riches: but the poor heareth not rebuke.

9 ሁልጊዜ ለጻድቃን ብርሃን ነው የኀጥኣን መብራት ግን ይጠፋል።

9 The light of the righteous rejoiceth: but the lamp of the wicked shall be put out.

10 በትዕቢት ጠብ ብቻ ይሆናል ጥበብ ግን ምክርን በሚቀበሉ ዘንድ ናት።

10 Only by pride cometh contention: but with the well advised is wisdom.

11 በችኰላ የምትከማች ሀብት ትጐድላለች ጥቂት በጥቂት የተከማቸች ግን ትበዛለች።

11 Wealth gotten by vanity shall be diminished: but he that gathereth by labour shall increase.

12 የምትዘገይ ተስፋ ልብን ታሳዝናለች የተገኘች ፈቃድ ግን የሕይወት ዛፍ ናት።

12 Hope deferred maketh the heart sick: but when the desire cometh, it is a tree of life.

13 ትእዛዝን የሚያቃልል በትእዛዝ ተይዞ ይጠፋል ትእዛዝን የሚፈራ ግን በደኅንነት ይኖራል።

13 Whoso despiseth the word shall be destroyed: but he that feareth the commandment shall be rewarded.

14 ሰው ከሞት ወጥመድ ያመልጥ ዘንድ የጠቢብ ሰው ትምህርት የሕይወት ምንጭ ነው።

14 The law of the wise is a fountain of life, to depart from the snares of death.

15 መልካም እውቀት ሞገስን ይሰጣል የወስላቶች መንገድ ግን ሸካራ ናት።

15 Good understanding giveth favour: but the way of transgressors is hard.

16 ብልህ ሁሉ በእውቀት ይሠራል ሰነፍ ግን ስንፍናውን ይገልጣል።

16 Every prudent man dealeth with knowledge: but a fool layeth open his folly.

17 መጥፎ መልእክተኛ በክፉ ላይ ይወድቃል የታመነ መልእክተኛ ግን ፈውስ ነው።

17 A wicked messenger falleth into mischief: but a faithful ambassador is health.

18 ድህነትና ነውር ተግሣጽን ቸል ለሚሉ ነው ዘለፋን የሚሰማ ግን ይከብራል።

18 Poverty and shame shall be to him that refuseth instruction: but he that regardeth reproof shall be honoured.

19 የተፈጸመች ፈቃድ ሰውነትን ደስ ታሰኛለች ሰነፎች ግን ከክፉ መራቅን ይጸየፋሉ።

19 The desire accomplished is sweet to the soul: but it is abomination to fools to depart from evil.

20 ከጠቢባን ጋር የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል የሰነፎች ባልንጀራ ግን ክፉ መከራን ይቀበላል።

20 He that walketh with wise men shall be wise: but a companion of fools shall be destroyed.

21 ክፉ ነገር ኃጢአተኞችን ያሳድዳቸዋል ጻድቃን ግን መልካሙን ዋጋ ይቀበላሉ።

21 Evil pursueth sinners: but to the righteous good shall be repayed.

22 ጻድቅ ሰው ለልጅ ልጆቹ ያወርሳል የኃጢአተኛ ብልጥግና ግን ለጻድቅ ትጠበቃለች።

22 A good man leaveth an inheritance to his children’s children: and the wealth of the sinner is laid up for the just.

23 በድሆች እርሻ ላይ ብዙ ሲሳይ አለ ከፍርድ መጕደል የተነሣ ግን ይጠፋል።

23 Much food is in the tillage of the poor: but there is that is destroyed for want of judgment.

24 በበትር ከመምታት የሚራራ ሰው ልጁን ይጠላል ልጁን የሚወድድ ግን ተግቶ ይገሥጻዋል።

24 He that spareth his rod hateth his son: but he that loveth him chasteneth him betimes.

25 ጻድቅ ሰውነቱ እስክትጠግብ ድረስ ይበላል የኀጥኣን ሆድ ግን ይራባል።

25 The righteous eateth to the satisfying of his soul: but the belly of the wicked shall want.