መጽሐፈ ምሳሌ | MeTsiHaFe MiSaLae
Proverbs of Solomon | Mishlei Shlomo #7
In Amharic and English
መጽሐፈ ምሳሌ 7 |
Proverbs 7 |
1 ልጄ ሆይ፥ ቃሌን ጠብቅ ትእዛዜንም በአንተ ዘንድ ሸሽግ። |
1 My son, keep my words, and lay up my commandments with thee. |
2 ትእዛዜን ጠብቅ በሕይወትም ትኖራለህ ሕጌንም እንደ ዓይንህ ብሌን ጠብቅ |
2 Keep my commandments, and live; and my law as the apple of thine eye. |
3 በጣቶችህ እሰራቸው በልብህ ጽላት ጻፋቸው። |
3 Bind them upon thy fingers, write them upon the table of thine heart. |
4 ጥበብን፦ አንቺ እኅቴ ነሽ በላት፥ ማስተማውልንም። ወዳጄ ብለህ ጥራት፥ |
4 Say unto wisdom, Thou art my sister; and call understanding thy kinswoman: |
5 ከጋለሞታ ሴት ትጠብቅህ ዘንድ ቃልዋን ካለዘበች ከሌላይቱ ሴት። |
5 That they may keep thee from the strange woman, from the stranger which flattereth with her words. |
6 በቤቴ መስኮት ሆኜ ወደ አደባባይ ተመለከትሁ |
6 For at the window of my house I looked through my casement, |
7 ከአላዋቂዎች መካከል አስተዋልሁ ከጐበዛዝትም መካከል ብላቴናውን አእምሮ ጐድሎት አየሁ፥ |
7 And beheld among the simple ones, I discerned among the youths, a young man void of understanding, |
8 በአደባባይ ሲሄድ በቤትዋም አቅራቢያ ሲያልፍ የቤትዋን መንገድ ይዞ ወደ እርስዋ አቀና፥ |
8 Passing through the street near her corner; and he went the way to her house, |
9 ማታ ሲመሽ፥ ውድቅትም ሲሆን፥ በሌሊትም በጽኑ ጨለማ። |
9 In the twilight, in the evening, in the black and dark night: |
10 እነሆ፥ ሴት ተገናኘችው የጋለሞታ ልብስ የለበሰች፥ ነፍሳትን ለማጥመድ የተዘጋጀች። |
10 And, behold, there met him a woman with the attire of an harlot, and subtil of heart. |
11 ሁከተኛና አባያ ናት፥ እግሮችዋም በቤትዋ አይቀመጡም |
11 (She is loud and stubborn; her feet abide not in her house: |
12 አንድ ጊዜ በጎዳና፥ አንድ ጊዜ በአደባባይ፥ በማዕዘኑም ሁሉ ታደባለች። |
12 Now is she without, now in the streets, and lieth in wait at every corner.) |
13 ያዘችውም ሳመችውም ፊትዋም ያለ እፍረት ሆኖ እንዲህ አለችው። |
13 So she caught him, and kissed him, and with an impudent face said unto him, |
14 መሥዋዕትንና የደኅንነት ቍርባንን ማቅረብ ነበረብኝ ዛሬ ስእለቴን ፈጸምሁ። |
14 I have peace offerings with me; this day have I payed my vows. |
15 ስለዚህ እንድገናኝህ፥ ፊትህንም በትጋት ለመሻት ወጥቻለሁ፥ አግኝቼሃለሁም። |
15 Therefore came I forth to meet thee, diligently to seek thy face, and I have found thee. |
16 በአልጋዬ ላይ ማለፊያ ሰርፍ ዘርግቼበታለሁ፥ የግብጽንም ሽመልመሌ ለሀፍ። |
16 I have decked my bed with coverings of tapestry, with carved works, with fine linen of Egypt. |
17 በመኝታዬ ከርቤንና ዓልሙን ቀረፋም ረጭቼበታለሁ። |
17 I have perfumed my bed with myrrh, aloes, and cinnamon. |
18 ና፥ እስኪነጋ ድረስ በፍቅር እንርካ፥ በተወደደ መተቃቀፍም ደስ ይበለን። |
18 Come, let us take our fill of love until the morning: let us solace ourselves with loves. |
19 ባለቤቴ በቤቱ የለምና፥ ወደ ሩቅ መንገድ ሄዶአልና |
19 For the goodman is not at home, he is gone a long journey: |
20 በእጁም የብር ከረጢት ወስዶአል ሙሉ ጨረቃ በሆነች ጊዜ ወደ ቤቱ ይመለሳል። |
20 He hath taken a bag of money with him, and will come home at the day appointed. |
21 በብዙ ጨዋታዋ እንዲስት ታደርገዋለች በከንፈርዋ ልዝብነት ትጐትተዋለች። |
21 With her much fair speech she caused him to yield, with the flattering of her lips she forced him. |
22 እርሱ እንዲህ ስቶ ይከተላታል፥ በሬ ለመታረድ እንዲነዳ፥ ውሻም ወደ እስራት እንዲሄድ፥ |
22 He goeth after her straightway, as an ox goeth to the slaughter, or as a fool to the correction of the stocks; |
23 ወፍ ወደ ወጥመድ እንደሚቸኩል፥ ለነፍሱ ጥፋት እንደሚሆን ሳያውቅ፥ ፍላጻ ጕበቱን እስኪሰነጥቀው ድረስ። |
23 Till a dart strike through his liver; as a bird hasteth to the snare, and knoweth not that it is for his life. |
24 ልጆቼ ሆይ፥ አሁን እንግዲህ ስሙኝ ወደ አፌም ቃል አድምጡኝ። |
24 Hearken unto me now therefore, O ye children, and attend to the words of my mouth. |
25 ልብህ ወደ መንገድዋ አያዘንብል በጎዳናዋ አትሳት። |
25 Let not thine heart decline to her ways, go not astray in her paths. |
26 ወግታ የጣለቻቸው ብዙ ናቸውና እርስዋም የገደለቻቸው እጅግ ብዙ ናቸው። |
26 For she hath cast down many wounded: yea, many strong men have been slain by her. |
27 ቤትዋ የሲኦል መንገድ ነው ወደ ሞት ማጀት የሚወርድ ነው። |
27 Her house is the way to hell, going down to the chambers of death. |