መጽሐፈ ምሳሌ | MeTsiHaFe MiSaLae
Proverbs of Solomon | Mishlei Shlomo #14
In Amharic and English
መጽሐፈ ምሳሌ 14 |
Proverbs 14 |
1 ብልሃተኛ ሴት ቤትዋን ትሠራለች ሰነፍ ሴት ግን በእጅዋ ታፈርሰዋለች። |
1 Every wise woman buildeth her house: but the foolish plucketh it down with her hands. |
2 በቅን የሚሄድ ሰው እግዚአብሔርን ይፈራል መንገዱን የሚያጣምም ግን ይንቀዋል። |
2 He that walketh in his uprightness feareth the Lord: but he that is perverse in his ways despiseth him. |
3 በሰነፍ አፍ የትዕቢት በትር አለ የጠቢባን ከንፈር ግን ትጠብቃቸዋለች። |
3 In the mouth of the foolish is a rod of pride: but the lips of the wise shall preserve them. |
4 በሬ በሌለበት ስፍራ እህል አይገኝም ብዙ ሲሳይ ግን በበሬዎች ኃይል ነው። |
4 Where no oxen are, the crib is clean: but much increase is by the strength of the ox. |
5 የታመነ ምስክር አይዋሽም የሐሰት ምስክር ግን በሐሰት ይናገራል። |
5 A faithful witness will not lie: but a false witness will utter lies. |
6 ፌዘኛ ሰው ጥበብን ይፈልጋል አያገኛትም ለአስተዋይ ግን እውቀትን ማግኘት አያስቸግረውም። |
6 A scorner seeketh wisdom, and findeth it not: but knowledge is easy unto him that understandeth. |
7 ከሰነፍ ሰው ፊት ራቅ፥ በእርሱ ዘንድ የእውቀትን ከንፈር አታገኝምና። |
7 Go from the presence of a foolish man, when thou perceivest not in him the lips of knowledge. |
8 የብልህ ሰው ጥበብ መንገዱን ያስተውል ዘንድ ነው የሰነፎች ስንፍና ግን ሽንገላ ነው። |
8 The wisdom of the prudent is to understand his way: but the folly of fools is deceit. |
9 ሰነፉ በኃጢአት ያፌዛል በቅኖች መካከል ግን ቸርነት አለች። |
9 Fools make a mock at sin: but among the righteous there is favour. |
10 የራሱን ኀዘን ልብ ያውቃል ከደስታውም ጋር ሌላ ሰው አይገናኝም። |
10 The heart knoweth his own bitterness; and a stranger doth not intermeddle with his joy. |
11 የኅጥኣን ቤት ይፈርሳል የቅኖች ማደሪያ ግን ያብባል። |
11 The house of the wicked shall be overthrown: but the tabernacle of the upright shall flourish. |
12 ለሰው ቅን የምትመስል መንገድ አለች ፍጻሜዋ ግን የሞት መንገድ ነው። |
12 There is a way which seemeth right unto a man, but the end thereof are the ways of death. |
13 በሳቅ ደግሞ ልብ ያዝናል፥ የደስታም ፍጻሜ ልቅሶ ነው። |
13 Even in laughter the heart is sorrowful; and the end of that mirth is heaviness. |
14 ልቡን ከጽድቅ የሚመልስ ሰው ከመንገዱ ፍሬ ይጠግባል፥ ጻድቅም ሰው ደግሞ በራሱ። |
14 The backslider in heart shall be filled with his own ways: and a good man shall be satisfied from himself. |
15 የዋህ ቃልን ሁሉ ያምናል ብልህ ግን አካሄዱን ይመለከታል። |
15 The simple believeth every word: but the prudent man looketh well to his going. |
16 ጠቢብ ሰው ይፈራል ከክፉም ይሸሻል ሰነፍ ግን ራሱን ታምኖ ይኰራል። |
16 A wise man feareth, and departeth from evil: but the fool rageth, and is confident. |
17 ቍጡ ሰው በስንፍና ይሠራል አስተዋይ ግን ይታገሣል። |
17 He that is soon angry dealeth foolishly: and a man of wicked devices is hated. |
18 አላዋቂዎች ሰዎች ስንፍናን ይወርሳሉ ብልሆች ግን እውቀትን እንደ ዘውድ ይጭናሉ። |
18 The simple inherit folly: but the prudent are crowned with knowledge. |
19 ኃጢአተኞች በደጎች ፊት ይጐነበሳሉ፥ ኀጥኣንም በጻድቃን በር። |
19 The evil bow before the good; and the wicked at the gates of the righteous. |
20 ድሀ በባልንጀራው ዘንድ የተጠላ ነው የባለጠጋ ወዳጆች ግን ብዙዎች ናቸው። |
20 The poor is hated even of his own neighbour: but the rich hath many friends. |
21 ባልንጀራውን የሚንቅ ይበድላል ለድሀ ግን የሚራራ ምስጉ ነው። |
21 He that despiseth his neighbour sinneth: but he that hath mercy on the poor, happy is he. |
22 ክፉ የሚያደርጉ ይስታሉ ምሕረትና እውነት ግን መልካምን ለሚያደርጉ ናቸው። |
22 Do they not err that devise evil? but mercy and truth shall be to them that devise good. |
23 በድካም ሁሉ ልምላሜ ይገኛል ብዙ ነገር በሚናገር ከንፈር ግን ድህነት ብቻ አለ። |
23 In all labour there is profit: but the talk of the lips tendeth only to penury. |
24 የጠቢባን ዘውድ ባለጠግነታቸው ነው የሰነፎች ስንፍና ግን ስንፍና ነው። |
24 The crown of the wise is their riches: but the foolishness of fools is folly. |
25 እውነተኛ ምስክር ነፍሶችን ያድናል በሐሰት የሚናገር ግን ሸንጋይ ነው። |
25 A true witness delivereth souls: but a deceitful witness speaketh lies. |
26 እግዚአብሔርን ለሚፈራ ጠንካራ መታመን አለው፥ ለልጆቹም መጠጊያ ይኖራል። |
26 In the fear of the Lord is strong confidence: and his children shall have a place of refuge. |
27 ሰው ከሞት ወጥመድ ያመልጥ ዘድን እግዚአብሔርን መፍራት የሕይወት ምንጭ ነው። |
27 The fear of the Lord is a fountain of life, to depart from the snares of death. |
28 የንጉሥ ክብር በሕዝብ ብዛት ነው በሰው ጥቂትነት ግን የገዥ ጥፋት አለ። |
28 In the multitude of people is the king’s honour: but in the want of people is the destruction of the prince. |
29 ለትግሥተኛ ሰው ብዙ ማስተዋል አለው ቍጡ ግን ስንፍናውን ከፍ ከፍ ያደርጋል። |
29 He that is slow to wrath is of great understanding: but he that is hasty of spirit exalteth folly. |
30 ትሑት ልብ የሥጋ ሕይወት ነው ቅንዓት ግን አጥንትን ያነቅዛል። |
30 A sound heart is the life of the flesh: but envy the rottenness of the bones. |
31 ድሀን የሚያስጨንቅ ፈጣሪውን ይሰድባል ለድሀ ምሕረትን የሚያደርግ ግን ያከብረዋል። |
31 He that oppresseth the poor reproacheth his Maker: but he that honoureth him hath mercy on the poor. |
32 ኀጥእ በክፋቱ ይደፋል ጻድቅ ግን በእውነቱ ይታመናል። |
32 The wicked is driven away in his wickedness: but the righteous hath hope in his death. |
33 በአዋቂ ልብ ጥበብ ትቀመጣለች በሰነፎች ውስጥ ግን አትታወቅም። |
33 Wisdom resteth in the heart of him that hath understanding: but that which is in the midst of fools is made known. |
34 ጽድቅ ሕዝብን ከፍ ከፍ ታደርጋለች ኃጢአት ግን ሕዝብን ታስነውራለች። |
34 Righteousness exalteth a nation: but sin is a reproach to any people. |
35 አስተዋይ አገልጋይ በንጉሥ ዘንድ ይወደዳል በሚያሳፍር ላይ ግን ቍጣው ይሆናል። |
35 The king’s favour is toward a wise servant: but his wrath is against him that causeth shame. |