መጽሐፈ ምሳሌ | MeTsiHaFe MiSaLae
Proverbs of Solomon | Mishlei Shlomo #30
In Amharic and English
መጽሐፈ ምሳሌ 30 |
Proverbs 30 |
1 የማሣ አገር ሰው የያቄ ልጅ የአጉር ቃል ሰውየው ለኢቲኤልና ለኡካል እንደዚህ ይናገራል። |
1 The words of Agur the son of Jakeh, even the prophecy: the man spake unto Ithiel, even unto Ithiel and Ucal, |
2 እኔ በእውነት ከሰው ሁሉ ይልቅ ደንቆሮ ነኝ፥ የሰውም ማስተዋል የለብኛም። |
2 Surely I am more brutish than any man, and have not the understanding of a man. |
3 ጥበብንም አልተማርሁም፥ ቅዱሱንም አላወቅሁትም። |
3 I neither learned wisdom, nor have the knowledge of the holy. |
4 ወደ ሰማይ የወጣ የወረደስ ማን ነው? ነፋስንስ በእጁ የጨበጠ ማን ነው? ውኃንስ በልብሱ የቋጠረ ማን ነው? የምድርን ዳርቻ ሁሉ ያጸና ማን ነው? ይህን ታውቅ እንደ ሆንህ፥ ስሙ ማን የልጁስ ስም ማን ነው? |
4 Who hath ascended up into heaven, or descended? who hath gathered the wind in his fists? who hath bound the waters in a garment? who hath established all the ends of the earth? what is his name, and what is his son’s name, if thou canst tell? |
5 የእግዚአብሔር ቃል ሁሉ ተፈትናለች እርሱ ለሚታመኑት ጋሻ ነው። |
5 Every word of God is pure: he is a shield unto them that put their trust in him. |
6 እንዳይዘልፍህ፥ ሐሰተኛም እንዳትሆን በቃሉ አንዳች አትጨምር። |
6 Add thou not unto his words, lest he reprove thee, and thou be found a liar. |
7 ሁለትን ነገር ከአንተ እሻለሁ፥ ሳልሞትም አትከልክለኝ |
7 Two things have I required of thee; deny me them not before I die: |
8 ከንቱነትንና ሐሰተኛነትን ከእኔ አርቃቸው ድኅነትንና ባለጠግነትን አትስጠኝ ነገር ግን የሚያስፈልገኝን እንጀራ ስጠኝ፥ |
8 Remove far from me vanity and lies: give me neither poverty nor riches; feed me with food convenient for me: |
9 እንዳልጠግብ እንዳልክድህም። እግዚአብሔርስ ማን ነው? እንዳልል ድሀም እንዳልሆን እንዳልሰርቅም፥ በአምላኬም ስም በሐሰት እንዳልምል። |
9 Lest I be full, and deny thee, and say, Who is the Lord? or lest I be poor, and steal, and take the name of my God in vain. |
10 እንዳይሰድብህ በደለኛም እንዳትሆን ባሪያን በጌታው ፊት አትማ። |
10 Accuse not a servant unto his master, lest he curse thee, and thou be found guilty. |
11 አባቱን የሚረግም፥ እናቱንም የማይባርክ ትውልድ አለ። |
11 There is a generation that curseth their father, and doth not bless their mother. |
12 ለራሱ ንጹሕ የሆነ የሚመስለው ከርኵሰቱ ያልጠራ ትውልድ አለ። |
12 There is a generation that are pure in their own eyes, and yet is not washed from their filthiness. |
13 ከፍ ከፍ ያሉ ዓይኖች ያሉት፥ ሽፋሽፍቶቹም ወደ ላይ የሚያዩ ትውልድ አለ። |
13 There is a generation, O how lofty are their eyes! and their eyelids are lifted up. |
14 ድሆችን ከምድር ላይ ችግረኞችንም ከሰው መካከል ያጠፋና ይጨርስ ዘንድ ጥርሶቹ ሰይፍ መንጋጎቹም ካራ የሆኑ ትውልድ አለ። |
14 There is a generation, whose teeth are as swords, and their jaw teeth as knives, to devour the poor from off the earth, and the needy from among men. |
15 አልቅት። ስጠን ስጠን የሚሉ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉት። ሦስቱ የማይጠግቡ አራቱም። በቃን የማይሉ ናቸው |
15 The horseleach hath two daughters, crying, Give, give. There are three things that are never satisfied, yea, four things say not, It is enough: |
16 እነርሱም ሲኦልና የማትወልድ ማኅፀን ውኃ የማትጠግብ ምድርና። በቃኝ የማትል እሳት ናቸው። |
16 The grave; and the barren womb; the earth that is not filled with water; and the fire that saith not, It is enough. |
17 በአባትዋ የምታላግጥን የእናትዋንም ትእዛዝ የምትንቅን ዓይን የሸለቆ ቍራዎች ይጐጠጕጡአታል፥ አሞራዎችም ይበሉአታል። |
17 The eye that mocketh at his father, and despiseth to obey his mother, the ravens of the valley shall pick it out, and the young eagles shall eat it. |
18 ሦስት ነገር ይገርመኛል፥ አራተኛውንም ከቶ አላስተውለውም። |
18 There be three things which are too wonderful for me, yea, four which I know not: |
19 እነርሱም የንስር መንገድ በሰማይ፥ የእባብ መንገድ በድንጋይ ላይ፥ የመርከብ መንገድ በባሕር ላይ፥ የሰውም መንገድ ከቈንጆ ጋር ናቸው። |
19 The way of an eagle in the air; the way of a serpent upon a rock; the way of a ship in the midst of the sea; and the way of a man with a maid. |
20 እንዲሁ በልታ አፍዋን የምታብስ። አንዳች ክፉ ነገር አላደረግሁም የምትልም የአመንዝራ ሴት መንገድ ናት። |
20 Such is the way of an adulterous woman; she eateth, and wipeth her mouth, and saith, I have done no wickedness. |
21 በሦስት ነገር ምድር ትናወጣለች፥ አራተኛውንም ትሸከም ዘንድ አይቻላትም። |
21 For three things the earth is disquieted, and for four which it cannot bear: |
22 ባሪያ በነገሠ ጊዜ ሰነፍም እንጀራ በጠገበ ጊዜ፥ |
22 For a servant when he reigneth; and a fool when he is filled with meat; |
23 የተጠላች ሴት ባል ባገኘች ጊዜ፥ ሴት ባሪያም እመቤቷን በወረሰች ጊዜ። |
23 For an odious woman when she is married; and an handmaid that is heir to her mistress. |
24 በምድር ላይ አራት ጥቃቅን ፍጥረቶች አሉ እነርሱ ግን እጅግ ጠቢባን ናቸው |
24 There be four things which are little upon the earth, but they are exceeding wise: |
25 ገብረ ጕንዳን ኃይል የሌላቸው ሕዝቦች ናቸው፥ ነገር ግን በበጋ መኖዋቸውን ይሰበስባሉ። |
25 The ants are a people not strong, yet they prepare their meat in the summer; |
26 ሽኮኮዎች ያልበረቱ ሕዝቦች ናቸው፥ ቤታቸውን ግን በቋጥኝ ድንጋይ ውስጥ ያደርጋሉ። |
26 The conies are but a feeble folk, yet make they their houses in the rocks; |
27 አንበጣዎች ንጉሥ የላቸውም፥ ሁላቸው ግን በመልካም ሥርዓት ይሄዳሉ። |
27 The locusts have no king, yet go they forth all of them by bands; |
28 እንሽላሊት በእጅ ይያዛል፥ በነገሥታት ግቢ ግን ይኖራል። |
28 The spider taketh hold with her hands, and is in kings’ palaces. |
29 መልካም አረማመድን የሚራመዱ ሦስት ፍጥረቶች አሉ፥ አራተኛውም መልካም አካሄድን ይሄዳል |
29 There be three things which go well, yea, four are comely in going: |
30 የአንበሳ ደቦል ከእንስሳ ሁሉ የሚበረታ፥ የማይመለስ፥ እንስሳንም የማይፈራ |
30 A lion which is strongest among beasts, and turneth not away for any; |
31 በእንስቶች መካከል በድፍረት የሚራመድ አውራ ዶሮ መንጋን የምመራ አውራ ፍየል በሕዝብ ፊት በግልጥ የሚናገር ንጉሥ። |
31 A greyhound; an he goat also; and a king, against whom there is no rising up. |
32 ከፍ ከፍ ስትል ስንፍናን ያደረግህ እንደሆነ፥ ክፉም ያሰብህ እንደ ሆነ፥ እጅህን በአፍህ ላይ ጫን። |
32 If thou hast done foolishly in lifting up thyself, or if thou hast thought evil, lay thine hand upon thy mouth. |
33 ወተት መግፋት ቅቤን ያወጣል፥ አፍንጫንም መጭመቅ ደምን ያወጣ እንዲሁም ቍጣን መጐተት ጠብን ያወጣል። |
33 Surely the churning of milk bringeth forth butter, and the wringing of the nose bringeth forth blood: so the forcing of wrath bringeth forth strife. |