መጽሐፈ ምሳሌ | MeTsiHaFe MiSaLae
Proverbs of Solomon
| Mishlei Shlomo #31
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

መጽሐፈ ምሳሌ 31

Proverbs 31

1 እናቱ እርሱን ያስተማረችበት የማሣ ንጉሥ የልሙኤል ቃል።

1 The words of king Lemuel, the prophecy that his mother taught him.

2 ልጄ ሆይ፥ ምንድር ነው? የሆዴ ልጅ ሆይ፥ ምንድር ነው? የስእለቴ ልጅ ሆይ፥ ምንድር ነው?

2 What, my son? and what, the son of my womb? and what, the son of my vows?

3 ጕልበትህን ለሴቶች አትስጥ፥ መንገድህንም ነገሥታትን ለሚያጠፉ።

3 Give not thy strength unto women, nor thy ways to that which destroyeth kings.

4 ለነገሥታት አይገባም፥ ልሙኤል ሆይ፥ ነገሥታት የወይን ጠጅ ይጠጡ ዘንድ አይገባም። መሳፍንትም። ብርቱ መጠጥ ወዴት ነው? ይሉ ዘንድ

4 It is not for kings, O Lemuel, it is not for kings to drink wine; nor for princes strong drink:

5 እንዳይጠጡና ሕግን እንዳይረሱ፥ የድሀ ልጆችንም ፍርድ እንዳያጐድሉ።

5 Lest they drink, and forget the law, and pervert the judgment of any of the afflicted.

6 ለጥፋት ለቀረበው ሰው ብርቱ መጠጥ ስጡት፥ ነፍሱ ለመረረውም የወይን ጠጅ ስጡት

6 Give strong drink unto him that is ready to perish, and wine unto those that be of heavy hearts.

7 ይጠጣ ድህነቱንም ይርሳ፥ ጕስቍልናውንም ከእንግዲህ ወዲህ አያስብ።

7 Let him drink, and forget his poverty, and remember his misery no more.

8 አፍህን ስለ ዲዳው ክፈት፥ ተስፋ ስለሌላቸውም ሁሉ ተፋረድ።

8 Open thy mouth for the dumb in the cause of all such as are appointed to destruction.

9 አፍህን ክፍት፥ በእውነትም ፍረድ ለድሀና ለምስኪን ፍረድ።

9 Open thy mouth, judge righteously, and plead the cause of the poor and needy.

10 ልባም ሴትን ማን ሊያገኛት ይችላል? ዋጋዋ ከቀይ ዕንቍ እጅግ ይበልጣል።

10 Who can find a virtuous woman? for her price is far above rubies.

11 የባልዋ ልብ ይታመንባታል። ምርኮም አይጐድልበትም።

11 The heart of her husband doth safely trust in her, so that he shall have no need of spoil.

12 ዕድሜዋን ሙሉ መልካም ታደርግለታለች፥ ክፉም አታደርግም።

12 She will do him good and not evil all the days of her life.

13 የበግ ጠጕርና የተልባ እግር ትፈልጋለች፥ በእጆችዋም ደስ ብሎአት ትሠራለች።

13 She seeketh wool, and flax, and worketh willingly with her hands.

14 እርስዋ እንደ ነጋዴ መርከብ ናት ከሩቅ አገር ምግብዋን ትሰበስባለች።

14 She is like the merchants’ ships; she bringeth her food from afar.

15 ገና ሌሊት ሳለ ትነሣለች ለቤትዋም ሰዎች ምግባቸውን፥ ለገረዶችዋም ተግባራቸውን ትሰጣለች።

15 She riseth also while it is yet night, and giveth meat to her household, and a portion to her maidens.

16 እርሻንም ተመልክታ ትገዛለች ከእጅዋም ፍሬ ወይን ትተክላለች።

16 She considereth a field, and buyeth it: with the fruit of her hands she planteth a vineyard.

17 ወገብዋን በኃይል ትታጠቃለች፥ ክንድዋንም ታበረታለች።

17 She girdeth her loins with strength, and strengtheneth her arms.

18 ንግድዋ መልካም እንደ ሆነ ትመለከታለች መብራትዋ በሌሊት አይጠፋም።

18 She perceiveth that her merchandise is good: her candle goeth not out by night.

19 እጅዋን ወደ አመልማሎ ትዘረጋለች፥ ጣቶችዋም እንዝርትን ይይዛሉ።

19 She layeth her hands to the spindle, and her hands hold the distaff.

20 እጅዋን ወደ ድሀ ትዘረጋለች፥ ወደ ችግረኛም እጅዋን ትሰድዳለች።

20 She stretcheth out her hand to the poor; yea, she reacheth forth her hands to the needy.

21 ለቤትዋ ሰዎች ከበረዶ ብርድ የተነሣ አትፈራም፥ የቤትዋ ሰዎች ሁሉ እጥፍ ድርብ የለበሱ ናቸውና።

21 She is not afraid of the snow for her household: for all her household are clothed with scarlet.

22 ለራስዋም ግብረ መርፌ ስጋጃ ትሠራለች ጥሩ በፍታና ቀይ ግምጃ ትለብሳለች።

22 She maketh herself coverings of tapestry; her clothing is silk and purple.

23 ባልዋ በአገር ሽማግሌዎች መካከል በሸንጎ በተቀመጠ ጊዜ በበር የታወቀ ይሆናል።

23 Her husband is known in the gates, when he sitteth among the elders of the land.

24 የበፍታ ቀሚስ እየሠራች ትሸጣለች፥ ለነጋዴም ድግ ትሸጣለች።

24 She maketh fine linen, and selleth it; and delivereth girdles unto the merchant.

25 ብርታትና ከበሬታ ልብስዋ ነው በኋላም ዘመን ላይ ትስቃለች።

25 Strength and honour are her clothing; and she shall rejoice in time to come.

26 አፍዋን በጥበብ ትከፍታለች የርኅራኄም ሕግ በምላስዋ አለ።

26 She openeth her mouth with wisdom; and in her tongue is the law of kindness.

27 የቤትዋንም ሰዎች አካሄድ በደኅና ትመለከታለች፥ የሀኬትንም እንጀራ አትበላም።

27 She looketh well to the ways of her household, and eateth not the bread of idleness.

28 ልጆችዋ ይነሣሉ፥ ምስጋናዋንም ይናገራሉ ባልዋ ደግሞ እንዲህ ብሎ ያመሰግናታል።

28 Her children arise up, and call her blessed; her husband also, and he praiseth her.

29 መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ፥ አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ።

29 Many daughters have done virtuously, but thou excellest them all.

30 ውበት ሐሰት ነው፥ ደም ግባትም ከንቱ ነው እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርስዋ ትመሰገናለች።

30 Favour is deceitful, and beauty is vain: but a woman that feareth the Lord, she shall be praised.

31 ከእጅዋ ፍሬ ስጡአት፥ ሥራዎችዋም በሸንጎ ያመስግኑአት።

31 Give her of the fruit of her hands; and let her own works praise her in the gates.