መጽሐፈ ምሳሌ | MeTsiHaFe MiSaLae
Proverbs of Solomon
| Mishlei Shlomo #20
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

መጽሐፈ ምሳሌ 20

Proverbs 20

1 የወይን ጠጅ ፌዘኛ ያደርጋል፥ ብርቱ መጠጥም ጠበኛ ያደርጋል በዚህም የሳተ ሁሉ ጠቢብ አይደለም።

1 Wine is a mocker, strong drink is raging: and whosoever is deceived thereby is not wise.

2 የንጉሥ ቍጣ እንደ አንበሳ ግሣት ነው የሚያስቈጣውም ሰው የራሱን ነፍስ ይበድላል።

2 The fear of a king is as the roaring of a lion: whoso provoketh him to anger sinneth against his own soul.

3 ከክርክር ይርቅ ዘንድ ለሰው ክብሩ ነው ሰነፍ ሁሉ ግን እንዲህ ባለ ነገር ይጣመራል።

3 It is an honour for a man to cease from strife: but every fool will be meddling.

4 ታካች ሰው በብርድ ምክንያት አያርስም ስለዚህ በመከር ይለምናል፥ ምንም አያገኝም።

4 The sluggard will not plow by reason of the cold; therefore shall he beg in harvest, and have nothing.

5 ምክር በሰው ልብ እንደ ጠሊቅ ውኃ ነው አእምሮ ያለው ሰው ግን ይቀዳዋል።

5 Counsel in the heart of man is like deep water; but a man of understanding will draw it out.

6 ብዙ ሰዎች ቸርነታቸውን ያወራሉ የታመነውን ሰው ግን ማን ያገኘዋል?

6 Most men will proclaim every one his own goodness: but a faithful man who can find?

7 ጻድቅ ያለ ነውር ይሄዳል፥ ልጆቹም ከእርሱ በኋላ ምስጉኖች ናቸው።

7 The just man walketh in his integrity: his children are blessed after him.

8 በፍርድ ወንበር የተቀመጠ ንጉሥ ክፉውን ሁሉ በዓይኖቹ ይበትናል።

8 A king that sitteth in the throne of judgment scattereth away all evil with his eyes.

9 ልቤን አነጻሁ፥ ከኃጢአትም ጠራሁ የሚል ማን ነው?

9 Who can say, I have made my heart clean, I am pure from my sin?

10 ሁለት ዓይነት ሚዛንና ሁለት ዓይነት መስፈሪያ፥ ሁለቱ በእግዚአብሔር ፊት ርኩሳን ናቸው።

10 Divers weights, and divers measures, both of them are alike abomination to the Lord.

11 ሕፃን ቅንና ንጹሕ መሆኑ በሚያደርገው ሥራ ይታወቃል።

11 Even a child is known by his doings, whether his work be pure, and whether it be right.

12 የሚሰማ ጆሮንና የሚያይ ዓይንን፥ ሁለቱን እግዚአብሔር ፈጠራቸው።

12 The hearing ear, and the seeing eye, the Lord hath made even both of them.

13 ድሀ እንዳትሆን እንቅልፍን አትውደድ ዓይንህን ክፈት፥ እንጀራም ትጠግባለህ።

13 Love not sleep, lest thou come to poverty; open thine eyes, and thou shalt be satisfied with bread.

14 የሚገዛ ሰው። ክፉ ነው ክፉ ነው ይላል በሄደ ጊዜ ግን ይመካል።

14 It is naught, it is naught, saith the buyer: but when he is gone his way, then he boasteth.

15 ወርቅና ብዙ ቀይ ዕንቍ ይገኛል የእውቀት ከንፈር ግን የከበረች ጌጥ ናት።

15 There is gold, and a multitude of rubies: but the lips of knowledge are a precious jewel.

16 ለማያውቀው ከተዋሰ ሰው ልብሱን ውሰድ፥ ለእንግዳ የተዋሰውንም እርሱን አግተው።

16 Take his garment that is surety for a stranger: and take a pledge of him for a strange woman.

17 የሐሰት እንጀራ ለሰው የጣፈጠ ነው ከዚያ በኋላ ግን አፉ ጭንጫ ይሞላል።

17 Bread of deceit is sweet to a man; but afterwards his mouth shall be filled with gravel.

18 አሳብ በምክር ትጸናለች፥ በመልካምም ምክር ሰልፍ አድርግ።

18 Every purpose is established by counsel: and with good advice make war.

19 ዘዋሪ ሐሜተኛ ምሥጢርን ይገልጣል ከንፈሩን የሚያሞጠሙጥ ሰውን አትገናኘው።

19 He that goeth about as a talebearer revealeth secrets: therefore meddle not with him that flattereth with his lips.

20 አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ፥ በጽቅድቅ ጨለማ መብራቱ ይጠፋል።

20 Whoso curseth his father or his mother, his lamp shall be put out in obscure darkness.

21 በመጀመሪያ ፈጥኖ የተከማቸ ርስት ፍጻሜው አይባረክም።

21 An inheritance may be gotten hastily at the beginning; but the end thereof shall not be blessed.

22 ክፉ እመልሳለሁ አትበል እግዚአብሔርን ተማመን፥ እርሱም ያድንሃል።

22 Say not thou, I will recompense evil; but wait on the Lord, and he shall save thee.

23 ሁለት ዓይነት ሚዛን በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ ሐሰተኛ ሚዛንም መልካም አይደለም።

23 Divers weights are an abomination unto the Lord; and a false balance is not good.

24 የሰው አካሄዱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው እንግዲያስ ሰው መንገዱን እንዴት ያስተውላል?

24 Man’s goings are of the Lord; how can a man then understand his own way?

25 ሰው በችኰላ። ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው ብሎ ቢሳል፥ ከተሳለም በኋላ ቢፀፀት ወጥመድ ነው።

25 It is a snare to the man who devoureth that which is holy, and after vows to make enquiry.

26 ጠቢብ ንጉሥ ኀጥኣንን በመንሽ ይበትናቸዋል፥ መንኰራኵሩንም በእነርሱ ላይ ያንኰራኵርባቸዋል።

26 A wise king scattereth the wicked, and bringeth the wheel over them.

27 የሰው መንፈስ የእግዚአብሔር መብራት ነው የሆዱን ጕርጆች ሁሉ የሚመረምር።

27 The spirit of man is the candle of the Lord, searching all the inward parts of the belly.

28 ቸርነትና እውነት ንጉሥን ይጠብቁታል ዙፋኑም በቸርነት ይበረታል።

28 Mercy and truth preserve the king: and his throne is upholden by mercy.

29 የጎበዛዝት ክብር ጕልበታቸው ናት፥ የሽማግሌዎችም ጌጥ ሽበት ነው።

29 The glory of young men is their strength: and the beauty of old men is the gray head.

30 የሰንበር ቍስል ክፉዎችን ያነጻል ግርፋትም ወደ ሆድ ጕርጆች ይገባል።

30 The blueness of a wound cleanseth away evil: so do stripes the inward parts of the belly.