መጽሐፈ ምሳሌ | MeTsiHaFe MiSaLae
Proverbs of Solomon | Mishlei Shlomo #23
In Amharic and English
መጽሐፈ ምሳሌ 23 |
Proverbs 23 |
1 ከመኰንን ጋር ለመብላት በተቀመጥህ ጊዜ፥ በፊትህ ያለውን በደኅና አስተውል |
1 When thou sittest to eat with a ruler, consider diligently what is before thee: |
2 ሰውነትህም ቢሳሳ፥ በጕሮሮህ ላይ ካራ አድርግ። |
2 And put a knife to thy throat, if thou be a man given to appetite. |
3 ጣፋጩ መብል አይመርህ የሐሰት እንጀራ ነውና። |
3 Be not desirous of his dainties: for they are deceitful meat. |
4 ባለጠጋ ለመሆን አትድከም የገዛ ራስህን ማስተዋል ተው። |
4 Labour not to be rich: cease from thine own wisdom. |
5 በእርሱ ላይ ዓይንህን ብታዘወትርበት ይጠፋል ባለጠግነት ወደ ሰማይ እንደሚበርር እንደ ንስር ለራሱ ክንፍ ያበጃልና። |
5 Wilt thou set thine eyes upon that which is not? for riches certainly make themselves wings; they fly away as an eagle toward heaven. |
6 የቀናተኛን ሰው እንጀራ አትብላ፥ ጣፋጩ መብልም አይመርህ |
6 Eat thou not the bread of him that hath an evil eye, neither desire thou his dainty meats: |
7 በልቡ እንዳሰበ እንዲሁ ነውና ብላ ጠጣ ይልሃል፥ ልቡ ግን ካንተ ጋር አይደለም። |
7 For as he thinketh in his heart, so is he: Eat and drink, saith he to thee; but his heart is not with thee. |
8 የበላኸውን መብል ትተፋዋለህ፥ ያማረውንም ቃልህን ታጠፋዋለህ። |
8 The morsel which thou hast eaten shalt thou vomit up, and lose thy sweet words. |
9 በሰነፍ ጆሮ አንዳች አትናገር፥ የቃልህን ጥበብ ያፌዝብሃልና። |
9 Speak not in the ears of a fool: for he will despise the wisdom of thy words. |
10 የቀድሞውን የድንበር ምልክት አታፍልስ ወደ ድሀ አደጎች እርሻ አትግባ |
10 Remove not the old landmark; and enter not into the fields of the fatherless: |
11 ታዳጊአቸው ጽኑ ነውና፥ እርሱም ፍርዳቸውን ከአንተ ጋር ይፋረዳልና። |
11 For their redeemer is mighty; he shall plead their cause with thee. |
12 ልብህን ለተግሣጽ ስጥ፥ ጆሮህንም ወደ እውቀት ቃል። |
12 Apply thine heart unto instruction, and thine ears to the words of knowledge. |
13 ሕፃንን ከመቅጣት ቸል አትበል፥ በበትር ብትመታው አይሞትምና። |
13 Withhold not correction from the child: for if thou beatest him with the rod, he shall not die. |
14 በበትር ትመታዋለህ፥ ነፍሱንም ትታደጋለህ። |
14 Thou shalt beat him with the rod, and shalt deliver his soul from hell. |
15 ልጄ ሆይ፥ ልብህ ጠቢብ ቢሆን ልቤ ደግሞ ደስ ይለዋል |
15 My son, if thine heart be wise, my heart shall rejoice, even mine. |
16 ከንፈሮችህም በቅን ቢናገሩ ኵላሊቶቼ ደስ ይላቸዋል። |
16 Yea, my reins shall rejoice, when thy lips speak right things. |
17 ልብህ በኃጢአተኞች አይቅና ነገር ግን ቀኑን ሙሉ እግዚአብሔርን በመፍራት ኑር |
17 Let not thine heart envy sinners: but be thou in the fear of the Lord all the day long. |
18 በእውነት ፍጻሜ አለህና፥ ተስፋህም አይጠፋምና። |
18 For surely there is an end; and thine expectation shall not be cut off. |
19 ልጄ ሆይ፥ ስማ ጠቢብም ሁን ልብህንም በቀናው መንገድ ምራ። |
19 Hear thou, my son, and be wise, and guide thine heart in the way. |
20 የወይን ጠጅ ከሚጠጡ ጋር አትቀመጥ ለሥጋም ከሚሣሡ ጋር |
20 Be not among winebibbers; among riotous eaters of flesh: |
21 ሰካርና ሆዳም ይደኸያሉና፥ የእንቅልፍም ብዛት የተቦጫጨቀ ጨርቅ ያስለብሳልና። |
21 For the drunkard and the glutton shall come to poverty: and drowsiness shall clothe a man with rags. |
22 የወለደህን አባትህን ስማ፥ እናትህም ባረጀች ጊዜ አትናቃት። |
22 Hearken unto thy father that begat thee, and despise not thy mother when she is old. |
23 እውነትን ግዛ አትሽጣትም፥ ጥበብን ተግሣጽን ማስተዋልንም። |
23 Buy the truth, and sell it not; also wisdom, and instruction, and understanding. |
24 የጻድቅ አባት እጅግ ደስ ይለዋል፥ ጠቢብንም ልጅ የወለደ ሐሤትን ያገኛል። |
24 The father of the righteous shall greatly rejoice: and he that begetteth a wise child shall have joy of him. |
25 አባትህና እናትህ ደስ ይበላቸው፥ አንተንም የወለደች ደስ ይበላት። |
25 Thy father and thy mother shall be glad, and she that bare thee shall rejoice. |
26 ልጄ ሆይ፥ ልብህን ስጠኝ፥ ዓይኖችህም መንገዴን ይውደዱ |
26 My son, give me thine heart, and let thine eyes observe my ways. |
27 ጋለሞታ ሴት የጠለቀች ዐዘቅት ናትና፥ ሌላይቱም ሴት የጠበበች ጕድጓድ ናትና። |
27 For a whore is a deep ditch; and a strange woman is a narrow pit. |
28 እንደ ሌባ ታደባለች ወስላቶችንም በሰው ልጆች መካከል ታበዛለች። |
28 She also lieth in wait as for a prey, and increaseth the transgressors among men. |
29 ዋይታ ለማን ነው? ኀዘን ለማን ነው? ጠብ ለማን ነው? ጩኸት ለማን ነው? ያለ ምክንያት መቍሰል ለማን ነው? የዓይን ቅላት ለማን ነው? |
29 Who hath woe? who hath sorrow? who hath contentions? who hath babbling? who hath wounds without cause? who hath redness of eyes? |
30 የወይን ጠጅ በመጠጣት ለሚዘገዩ አይደለምን? የተደባለቀ የወይንን ጠጅ ይፈትኑ ዘንድ ለሚከተሉ አይደለምን? |
30 They that tarry long at the wine; they that go to seek mixed wine. |
31 ወደ ወይን ጠጅ አትመልከት በቀላ ጊዜ፥ መልኩም በብርሌ ባንጸባረቀ ጊዜ፥ እየጣፈጠም በገባ ጊዜ። |
31 Look not thou upon the wine when it is red, when it giveth his colour in the cup, when it moveth itself aright. |
32 በኋላ እንደ እባብ ይነድፋል፥ እንደ እፉኝትም መርዙን ያፈስሳል። |
32 At the last it biteth like a serpent, and stingeth like an adder. |
33 ዓይኖችህ ጋለሞታዎችን ያያሉ፥ ልብህም ጠማማ ነገርን ይናገራል። |
33 Thine eyes shall behold strange women, and thine heart shall utter perverse things. |
34 በባሕር ውስጥ እንደ ተኛ ትሆናለህ፥ በደቀልም ላይ እንደ ተኛ። |
34 Yea, thou shalt be as he that lieth down in the midst of the sea, or as he that lieth upon the top of a mast. |
35 መቱኝ፥ ያውም አልተሰማኝም ጐሰሙኝ፥ አላወቅሁምም። መቼ እነሣለሁ? ደግሞ ጨምሬ እሻታለሁ ትላለህ። |
35 They have stricken me, shalt thou say, and I was not sick; they have beaten me, and I felt it not: when shall I awake? I will seek it yet again. |