መጽሐፈ ምሳሌ | MeTsiHaFe MiSaLae
Proverbs of Solomon | Mishlei Shlomo #22
In Amharic and English
መጽሐፈ ምሳሌ 22 |
Proverbs 22 |
1 መልካም ስም ከብዙ ባለጠግነት ይሻላል፥ መልካምም ሞገስ ከብርና ከወርቅ ይበልጣል። |
1 A good name is rather to be chosen than great riches, and loving favour rather than silver and gold. |
2 ባለጠና ድሀ ተገናኙ እግዚአብሔር የሁላቸው ፈጣሪ ነው። |
2 The rich and poor meet together: the Lord is the maker of them all. |
3 ብልህ ሰው ክፉን አይቶ ይሸሸጋል አላዋቂዎች ግን አልፈው ይጐዳሉ። |
3 A prudent man foreseeth the evil, and hideth himself: but the simple pass on, and are punished. |
4 ትሕትናና እግዚአብሔርን መፍራት ባለጠግነት ክብር ሕይወትም ነው። |
4 By humility and the fear of the Lord are riches, and honour, and life. |
5 እሾህና ወጥመድ በጠማማ ሰው መንገድ ናቸው ነፍሱን ግን የሚጠብቅ ከእነርሱ ይርቃል። |
5 Thorns and snares are in the way of the froward: he that doth keep his soul shall be far from them. |
6 ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው፥ በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም። |
6 Train up a child in the way he should go: and when he is old, he will not depart from it. |
7 ባለጠጋ ድሆችን ይገዛል፥ ተበዳሪም የአበዳሪ ባሪያ ነው። |
7 The rich ruleth over the poor, and the borrower is servant to the lender. |
8 ኃጢአትን የሚዘራ መከራን ያጭዳል፥ የቍጣውም በትር ይጠፋል። |
8 He that soweth iniquity shall reap vanity: and the rod of his anger shall fail. |
9 ርኅሩህ የተባረከ ይሆናል፥ ከእንጀራው ለድሀ ሰጥቶአልና። |
9 He that hath a bountiful eye shall be blessed; for he giveth of his bread to the poor. |
10 ፌዘኛን ብታወጣ ክርክር ይወጣል፥ ጠብና ስድብም ያልቃል። |
10 Cast out the scorner, and contention shall go out; yea, strife and reproach shall cease. |
11 የልብን ንጽሕና የሚወድድና ሞገስ በከንፈሩ ያለች፥ ንጉሥ ወዳጁ ይሆናል። |
11 He that loveth pureness of heart, for the grace of his lips the king shall be his friend. |
12 የእግዚአብሔር ዓይኖች እውቀትን ይጠብቃሉ እርሱ ግን የወስላታውን ቃል ይገለብጣል። |
12 The eyes of the Lord preserve knowledge, and he overthroweth the words of the transgressor. |
13 ታካች ሰው። አንበሳ በሜዳ ነው በመንገዱ ላይ እሞታለሁ ይላል። |
13 The slothful man saith, There is a lion without, I shall be slain in the streets. |
14 የጋለሞታ ሴት አፍ የጠለቀ ጕድጓድ ነው እግዚአብሔር የተቈጣው በእርስዋ ይወድቃል። |
14 The mouth of strange women is a deep pit: he that is abhorred of the Lord shall fall therein. |
15 ስንፍና በሕፃን ልብ ታስሮአል የተግሣጽ በትር ግን ከእርሱ ያርቃታል። |
15 Foolishness is bound in the heart of a child; but the rod of correction shall drive it far from him. |
16 ለራሱ ጥቅም ለመጨመር ሲል ድሀን የሚጐዳ፥ ለባለጠጋም የሚሰጥ፥ እርሱ ወደ ድህነት ይወድቃል። |
16 He that oppresseth the poor to increase his riches, and he that giveth to the rich, shall surely come to want. |
17 ጆሮህን አዘንብለህ የጠቢባንን ቃላት ስማ፥ ልብህንም ወደ እውቀቴ አድርግ |
17 Bow down thine ear, and hear the words of the wise, and apply thine heart unto my knowledge. |
18 እነርሱን በውስጥህ ብትጠብቅ፥ በከንፈሮችህም ላይ የተዘጋጁ ቢሆኑ፥ የተወደደ ነገር ይሆንልሃልና። |
18 For it is a pleasant thing if thou keep them within thee; they shall withal be fitted in thy lips. |
19 እምነትህ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ ለአንተ ዛሬ እነሆ አስታወቅሁህ። |
19 That thy trust may be in the Lord, I have made known to thee this day, even to thee. |
20-21 የእውነትን ቃል እርግጥነት አስታውቅህ ዘንድ፥ ለሚጠይቅህም እውነትን ቃል መመለስ ይቻልህ ዘንድ፥ በምክርና በእውቀት የከበረን ነገር አልጻፍሁልህምን? |
20 Have not I written to thee excellent things in counsels and knowledge, |
22 ድሀን በግድ አትበለው ድሀ ነውና ችግረኛውንም በበር አትግፋው |
22 Rob not the poor, because he is poor: neither oppress the afflicted in the gate: |
23 እግዚአብሔር የእነርሱን ፍርድ ይፋረድላቸዋልና፥ የቀሙአቸውንም ሰዎች ሕይወት ይቀማልና። |
23 For the Lord will plead their cause, and spoil the soul of those that spoiled them. |
24 ከቍጡ ሰው ጋር ባልንጀራ አትሁን፥ ከወፈፍተኛም ጋት አትሂድ፥ |
24 Make no friendship with an angry man; and with a furious man thou shalt not go: |
25 መንገዱን እንዳትማር ለነፍስህም ወጥመድ እንዳታገኝህ። |
25 Lest thou learn his ways, and get a snare to thy soul. |
26 እጃቸውን አጋና እንደሚማቱ፥ ለባለ ዕዳዎች እንደሚዋሱ አትሁን |
26 Be not thou one of them that strike hands, or of them that are sureties for debts. |
27 የምትከፍለው ባይኖርህ፥ ምንጣፍህን ከበታችህ ስለ ምን ይወስዳል? |
27 If thou hast nothing to pay, why should he take away thy bed from under thee? |
28 አባቶችህ የሠሩትን የቀድሞውን የድንበር ምልክት አታፍልስ። |
28 Remove not the ancient landmark, which thy fathers have set. |
29 በሥራው የቀጠፈ ሰውን አይተሃልን? በነገሥታት ፊት ይቆማል በተዋረዱም ሰዎች ፊት አይቆምም። |
29 Seest thou a man diligent in his business? he shall stand before kings; he shall not stand before mean men. |