መጽሐፈ ምሳሌ | MeTsiHaFe MiSaLae
Proverbs of Solomon | Mishlei Shlomo #4
In Amharic and English
መጽሐፈ ምሳሌ 4 |
Proverbs 4 |
1 እናንተ ልጆች፥ የአባትን ተግሣጽ ስሙ፥ ማስተዋልንም ታውቁ ዘንድ አድምጡ |
1 Hear, ye children, the instruction of a father, and attend to know understanding. |
2 መልካም ትምህርትን እሰጣችኋለሁና ሕጌን አትተዉ። |
2 For I give you good doctrine, forsake ye not my law. |
3 እኔም አባቴን የምሰማ ልጅ ነበርሁና፥ በእናቴም ዘንድ እወደድ ነበር። |
3 For I was my father’s son, tender and only beloved in the sight of my mother. |
4 ያስተምረኝም ነበር እንዲህም ይለኝ ነበር። ልብህ ቃሌን ይቀበል ትእዛዜን ጠብቅ በሕይወትም ትኖራለህ። |
4 He taught me also, and said unto me, Let thine heart retain my words: keep my commandments, and live. |
5 ጥበብን አግኝ ማስተዋልን አግኝ አትርሳም፥ ከአፌም ቃል ፈቀቅ አትበል። |
5 Get wisdom, get understanding: forget it not; neither decline from the words of my mouth. |
6 አትተዋት፥ ትደግፍህማለች ውደዳት፥ ትጠብቅህማለች። |
6 Forsake her not, and she shall preserve thee: love her, and she shall keep thee. |
7 ጥበብ ዓይነተኛ ነገር ናትና ጥበብን አግኝ ከሀብትህም ሁሉ ማስተዋልን አትርፍ። |
7 Wisdom is the principal thing; therefore get wisdom: and with all thy getting get understanding. |
8 ከፍ ከፍ አድርጋት፥ እርስዋም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች ብታቅፋትም ታከብርሃለች። |
8 Exalt her, and she shall promote thee: she shall bring thee to honour, when thou dost embrace her. |
9 ለራስህ የሞገስ አክሊልን ትሰጥሃለች፥ የተዋበ ዘውድንም ታበረክትሃለች። |
9 She shall give to thine head an ornament of grace: a crown of glory shall she deliver to thee. |
10 ልጄ ሆይ፥ ስማ፥ ንግግሬንም ተቀበል የሕይወትህም ዘመን ትበዛልሃለች። |
10 Hear, O my son, and receive my sayings; and the years of thy life shall be many. |
11 የጥበብን መንገድ አስተማርሁህ በቀናች ጎዳና መራሁህ። |
11 I have taught thee in the way of wisdom; I have led thee in right paths. |
12 በሄድህ ጊዜ እርምጃህ አይጠብብም በሮጥህም ጊዜ አትሰናከልም። |
12 When thou goest, thy steps shall not be straitened; and when thou runnest, thou shalt not stumble. |
13 ተግሣጽን ያዝ፥ አትተውም ጠብቀው፥ እርሱ ሕይወትህ ነውና። |
13 Take fast hold of instruction; let her not go: keep her; for she is thy life. |
14 በኃጥኣን መንገድ አትግባ፥ በክፉ ሰዎችም ጎዳና አትሂድ። |
14 Enter not into the path of the wicked, and go not in the way of evil men. |
15 ከእርስዋ ራቅ፥ አትሂድባትም ፈቀቅ በል ተዋትም። |
15 Avoid it, pass not by it, turn from it, and pass away. |
16 ክፉ ካላደረጉ አይተኙምና፥ ካላሰናከሉም እንቅልፋቸው ይወገዳልና። |
16 For they sleep not, except they have done mischief; and their sleep is taken away, unless they cause some to fall. |
17 የኃጢአትን እንጀራ ይበላሉና፥ የግፍንም ወይን ጠጅ ይጠጣሉና። |
17 For they eat the bread of wickedness, and drink the wine of violence. |
18 የጻድቃን መንገድ ግን እንደ ንጋት ብርሃን ነው፥ ሙሉ ቀን እስኪሆንም ድረስ እየተጨመረ ይበራል። |
18 But the path of the just is as the shining light, that shineth more and more unto the perfect day. |
19 የኃጥኣን መንገድ እንደ ጨለማ ነው፥ እንዴት እንደሚሰናከሉም አያውቁም። |
19 The way of the wicked is as darkness: they know not at what they stumble. |
20 ልጄ ሆይ፥ ንግግሬን አድምጥ ወደ ቃሌም ጆሮህን አዘንብል። |
20 My son, attend to my words; incline thine ear unto my sayings. |
21 ከዓይንህ አታርቃት፥ በልብህም ውስጥ ጠብቃት። |
21 Let them not depart from thine eyes; keep them in the midst of thine heart. |
22 ለሚያገኙአት ሕይወት፥ ለሥጋቸውም ሁሉ ፈውስ ነውና። |
22 For they are life unto those that find them, and health to all their flesh. |
23 አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና። |
23 Keep thy heart with all diligence; for out of it are the issues of life. |
24 የአፍህን ጠማማነት ከአንተ አውጣ፥ ሐሰተኞቹን ከንፈሮችም ከአንተ አርቅ። |
24 Put away from thee a froward mouth, and perverse lips put far from thee. |
25 ዓይኖችህ አቅንተው ይዩ፥ ሽፋሽፍቶችህም በቀጥታ ይመልከቱ። |
25 Let thine eyes look right on, and let thine eyelids look straight before thee. |
26 የእግርህን መንገድ አቅና፥ አካሄድህም ሁሉ ይጽና። |
26 Ponder the path of thy feet, and let all thy ways be established. |
27 ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል እግርህንም ከክፉ መልስ። |
27 Turn not to the right hand nor to the left: remove thy foot from evil. |