መጽሐፈ ምሳሌ | MeTsiHaFe MiSaLae
Proverbs of Solomon | Mishlei Shlomo #3
In Amharic and English
መጽሐፈ ምሳሌ 3 |
Proverbs 3 |
1 ልጄ ሆይ፥ ሕጌን አትርሳ፥ ልብህም ትእዛዛቴን ይጠብቅ። |
1 My son, forget not my law; but let thine heart keep my commandments: |
2 ብዙ ዘመናትና ረጅም ዕድሜ ሰላምም ይጨምሩልሃልና። |
2 For length of days, and long life, and peace, shall they add to thee. |
3 ምሕረትና እውነት ከአንተ አይራቁ በአንገትህ እሰራቸው በልብህ ጽላት ጻፋቸው። |
3 Let not mercy and truth forsake thee: bind them about thy neck; write them upon the table of thine heart: |
4 በእግዚአብሔርና በሰው ፊትም ሞገስንና መልካም ዝናን ታገኛለህ። |
4 So shalt thou find favour and good understanding in the sight of God and man. |
5 በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ |
5 Trust in the Lord with all thine heart; and lean not unto thine own understanding. |
6 በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል። |
6 In all thy ways acknowledge him, and he shall direct thy paths. |
7 በራስህ አስተያየት ጠቢብ አትሁን እግዚአብሔርን ፍራ፥ ከክፋትም ራቅ |
7 Be not wise in thine own eyes: fear the Lord, and depart from evil. |
8 ይህም ለሥጋህ ፈውስ ይሆንልሃል፥ ለአጥንትህም ጠገን። |
8 It shall be health to thy navel, and marrow to thy bones. |
9 እግዚአብሔርን ከሀብትህ አክብር፥ ከፍሬህም ሁሉ በኵራት |
9 Honour the Lord with thy substance, and with the firstfruits of all thine increase: |
10 ጐተራህም እህልን ይሞላል፥ መጥመቂያህም በወይን ጠጅ ሞልታ ትትረፈረፋለች። |
10 So shall thy barns be filled with plenty, and thy presses shall burst out with new wine. |
11 ልጄ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ተግሣጽ አትናቅ፥ በገሠጸህም ጊዜ አትመረር። |
11 My son, despise not the chastening of the Lord; neither be weary of his correction: |
12 እግዚአብሔር የወደደውን ይገሥጻልና፥ አባት የሚወድደውን ልጁን እንደሚገሥጽ። |
12 For whom the Lord loveth he correcteth; even as a father the son in whom he delighteth. |
13 ጥበብን የሚያገኝ ሰው ምስጉን ነው፥ ማስተዋልንም ገንዘቡ የሚያደርግ |
13 Happy is the man that findeth wisdom, and the man that getteth understanding. |
14 በወርቅና በብር ከመነገድ ይልቅ በእርስዋ መነገድ ይሻላልና። |
14 For the merchandise of it is better than the merchandise of silver, and the gain thereof than fine gold. |
15 ከቀይ ዕንቍም ትከብራለች፥ የተከበረም ነገር ሁሉ አይተካከላትም። |
15 She is more precious than rubies: and all the things thou canst desire are not to be compared unto her. |
16 በቀኝዋ ረጅም ዘመን ነው፥ በግራዋም ባለጠግነትና ክብር። |
16 Length of days is in her right hand; and in her left hand riches and honour. |
17 መንገድዋ የደስታ መንገድ ነው፥ ጎዳናዋም ሁሉ ሰላም ነው። |
17 Her ways are ways of pleasantness, and all her paths are peace. |
18 እርስዋ ለሚይዙአት የሕይወት ዛፍ ናት፥ የተመረኰዘባትም ሁሉ ምስጉን ነው። |
18 She is a tree of life to them that lay hold upon her: and happy is every one that retaineth her. |
19 እግዚአብሔር በጥበብ ምድርን መሠረተ፥ በማስተዋልም ሰማያትን አጸና። |
19 The Lord by wisdom hath founded the earth; by understanding hath he established the heavens. |
20 በእውቀቱ ቀላያት ተቀደዱ፥ ደመናትም ጠልን ያንጠባጥባሉ። |
20 By his knowledge the depths are broken up, and the clouds drop down the dew. |
21 ልጄ ሆይ፥ እነዚህ ከዓይኖችህ አይራቁ መልካም ጥበብንና ጥንቃቄን ጠብቅ። |
21 My son, let not them depart from thine eyes: keep sound wisdom and discretion: |
22 ለነፍስህም ሕይወት ይሆናሉ፥ ለአንገትህም ሞገስ። |
22 So shall they be life unto thy soul, and grace to thy neck. |
23 የዚያን ጊዜ መንገድህን ተማምነህ ትሄዳለህ፥ እግርህም አይሰነካከልም። |
23 Then shalt thou walk in thy way safely, and thy foot shall not stumble. |
24 በተኛህ ጊዜ አትፈራም ትተኛለህ፥ እንቅልፍህም የጣፈጠ ይሆንልሃል። |
24 When thou liest down, thou shalt not be afraid: yea, thou shalt lie down, and thy sleep shall be sweet. |
25 ድንገት ከሚያስፈራ ነገር፥ ከሚመጣውም ከኃጥኣን ጥፋት አትፈራም |
25 Be not afraid of sudden fear, neither of the desolation of the wicked, when it cometh. |
26 እግዚአብሔር መታመኛህ ይሆናልና፥ እግርህም እንዳይጠመድ ይጠብቅሃልና። |
26 For the Lord shall be thy confidence, and shall keep thy foot from being taken. |
27 ለተቸገረው ሰው በጎ ነገርን ማድረግ አትከልክል፥ ልታደርግለት የሚቻልህ ሲሆን። |
27 Withhold not good from them to whom it is due, when it is in the power of thine hand to do it. |
28 ወዳጅህን፦ ሂድና ተመለስ ነገ እሰጥሃለሁ አትበለው። በጎ ነገርን ማድረግ ሲቻልህ። |
28 Say not unto thy neighbour, Go, and come again, and to morrow I will give; when thou hast it by thee. |
29 በወዳጅህ ላይ ክፉ አትሥራ፥ እርሱ ተማምኖ ከአንተ ጋር ተቀምጦ ሳለ። |
29 Devise not evil against thy neighbour, seeing he dwelleth securely by thee. |
30 ከሰው ጋር በከንቱ አትጣላ፥ እርሱ ክፉ ካልሠራብህ። |
30 Strive not with a man without cause, if he have done thee no harm. |
31 በግፈኛ ሰው አትቅና፥ መንገዱንም ሁሉ አትምረጥ። |
31 Envy thou not the oppressor, and choose none of his ways. |
32 ጠማማ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ርኩስ ነውና ወዳጅነቱ ግን ከቅኖች ጋር ነው። |
32 For the froward is abomination to the Lord: but his secret is with the righteous. |
33 የእግዚአብሔር መርገም በኃጥእ ቤት ነው፥ የጻድቃን ቤት ግን ይባረካል። |
33 The curse of the Lord is in the house of the wicked: but he blesseth the habitation of the just. |
34 በፌዘኞች እርሱ ያፌዛል፥ ለትሑታን ግን ሞገስን ይሰጣል። |
34 Surely he scorneth the scorners: but he giveth grace unto the lowly. |
35 ጠቢባን ክብርን ይወርሳሉ የሰነፎች ከፍታቸው ግን መዋረድ ነው። |
35 The wise shall inherit glory: but shame shall be the promotion of fools. |