መጽሐፈ ምሳሌ | MeTsiHaFe MiSaLae
Proverbs of Solomon
| Mishlei Shlomo #21
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

መጽሐፈ ምሳሌ 21

Proverbs 21

1 የንጉሥ ልብ እንደ ውኃ ፈሳሾች በእግዚአብሔር እጅ ነው ወደ ወደደውም ያዘነብለዋል።

1 The king’s heart is in the hand of the Lord, as the rivers of water: he turneth it whithersoever he will.

2 የሰው መንገድ ሁሉ በዓይኑ ፊት የቀናች ትመስለዋለች እግዚአብሔር ግን ልብን ይመዝናል።

2 Every way of a man is right in his own eyes: but the Lord pondereth the hearts.

3 እግዚአብሔር ከመሥዋዕት ይልቅ ጽድቅንና ቅን ነገርን ማድረግ ይወድዳል።

3 To do justice and judgment is more acceptable to the Lord than sacrifice.

4 ትዕቢተኛ ዓይንና ደፋር ልብ የኀጥኣንም እርሻ ኃጢአት ነው።

4 An high look, and a proud heart, and the plowing of the wicked, is sin.

5 የትጉህ አሳብ ወደ ጥጋብ ያደርሳል ችኵል ሰው ሁሉ ግን ለመጕደል ይቸኩላል።

5 The thoughts of the diligent tend only to plenteousness; but of every one that is hasty only to want.

6 በሐሰተኛ ምላስ መዝገብ ማከማቸት የሚበንን ጉም ነው ይህን የሚፈልጉ ሞትን ይፈልጋሉ።

6 The getting of treasures by a lying tongue is a vanity tossed to and fro of them that seek death.

7 ቅን ነገርን ያደርጉ ዘንድ አይወድዱምና የኀጥኣን ንጥቂያ ራሳቸውን ያጠፋቸዋል።

7 The robbery of the wicked shall destroy them; because they refuse to do judgment.

8 የበደለኛ መንገድ የጠመመች ናት የንጹሕ ሥራ ግን የቀና ነው።

8 The way of man is froward and strange: but as for the pure, his work is right.

9 ከጠበኛ ሴት ጋር በአንድ ቤት ከመቀመጥ በውጪ በቤት ማዕዘን ላይ መቀመጥ ይሻላል።

9 It is better to dwell in a corner of the housetop, than with a brawling woman in a wide house.

10 የኀጥእ ነፍስ ክፉን ትመኛለች፥ በፊቱም ባልንጀራው ሞገስን አያገኝም።

10 The soul of the wicked desireth evil: his neighbour findeth no favour in his eyes.

11 ፌዘኛ ቅጣትን በተቀበለ ጊዜ አላዋቂ ሰው ጥበብን ያገኛል ጠቢብም ቢማር እውቀትን ይቀበላል።

11 When the scorner is punished, the simple is made wise: and when the wise is instructed, he receiveth knowledge.

12 ጻድቅ ስለ ኀጥእ ቤት ያስባል፥ ኀጥኣንም ለጥፋት እንደ ተገለበጡ።

12 The righteous man wisely considereth the house of the wicked: but God overthroweth the wicked for their wickedness.

13 የድሀውን ጩኸት እንዳይሰማ ጆሮውን የሚደፍን ሰው፥ እርሱ ራሱ ይጮኻል አይሰማለትምም።

13 Whoso stoppeth his ears at the cry of the poor, he also shall cry himself, but shall not be heard.

14 ስጦታ በስውር ቍጣን ታጠፋለች፥ የብብትም ውስጥ ጉቦ ጽኑ ቍጣን ታበርዳለች።

14 A gift in secret pacifieth anger: and a reward in the bosom strong wrath.

15 ፍርድን ማድረግ ለጻድቅ ደስታ ነው ኃጢአትን ለሚያደርጉ ግን ጥፋት ነው።

15 It is joy to the just to do judgment: but destruction shall be to the workers of iniquity.

16 ከማስተዋል መንገድ የሚሳሳት ሰው በሙታን ጉባኤ ያርፋል።

16 The man that wandereth out of the way of understanding shall remain in the congregation of the dead.

17 ተድላ የሚወድድ ድሀ ይሆናል፥ የወይን ጠጅንና ዘይትንም የሚወድድ ባለጠጋ አይሆንም።

17 He that loveth pleasure shall be a poor man: he that loveth wine and oil shall not be rich.

18 ኀጥእ የጻድቅ ቤዛ ነው በደለኛም የቅን ሰው ቤዛ ነው።

18 The wicked shall be a ransom for the righteous, and the transgressor for the upright.

19 ከጠበኛና ከቍጡ ሴት ጋር ከመቀመጥ በምድረ በዳ መቀመጥ ይሻላል።

19 It is better to dwell in the wilderness, than with a contentious and an angry woman.

20 የከበረ መዝገብና ዘይት በጠቢብ ሰው ቤት ይኖራል። አእምሮ የሌለው ሰው ግን ይውጠዋል።

20 There is treasure to be desired and oil in the dwelling of the wise; but a foolish man spendeth it up.

21 ጽድቅንና ምሕረትን የሚከተል ሕይወትንና ጽድቅን ክብርንም ያገኛል።

21 He that followeth after righteousness and mercy findeth life, righteousness, and honour.

22 ጠቢብ የኃያላንን ከተማ ይገባባታል፥ የሚታመኑበትንም ኃይል ያፈርሳል።

22 A wise man scaleth the city of the mighty, and casteth down the strength of the confidence thereof.

23 አፉንና ምላሱን የሚጠብቅ ነፍሱን ከመከራ ይጠብቃል።

23 Whoso keepeth his mouth and his tongue keepeth his soul from troubles.

24 ኵሩና ተጓዳጅ ሰው ፌዘኛ ይባላል እርሱም በትዕቢት ቍጣ ያደርጋል።

24 Proud and haughty scorner is his name, who dealeth in proud wrath.

25 ታካችን ምኞቱ ትገድለዋለች፥ እጆቹ ይሠሩ ዘንድ አይፈቅዱምና።

25 The desire of the slothful killeth him; for his hands refuse to labour.

26 ኀጥእ ቀኑን ሁሉ ምኞትን ይመኛል ጻድቅ ግን ይሰጣል፥ አይሰስትም።

26 He coveteth greedily all the day long: but the righteous giveth and spareth not.

27 የኀጥኣን መሥዋዕት አስጸያፊ ነው ይልቁንም በክፉ አሳብ ሲያቀርቡት አስጸያፊ ነው።

27 The sacrifice of the wicked is abomination: how much more, when he bringeth it with a wicked mind?

28 ሐሰተኛ ምስክር ይጠፋል የሚሰማ ሰው ግን ተጠንቅቆ ይናገራል።

28 A false witness shall perish: but the man that heareth speaketh constantly.

29 ኀጥእ ፊቱን ያጠነክራል ቅን ሰው ግን መንገዱን ያጸናል።

29 A wicked man hardeneth his face: but as for the upright, he directeth his way.

30 ጥበብ ወይም ማስተዋል ወይም ምክር በእግዚአብሔር ላይ የለም።

30 There is no wisdom nor understanding nor counsel against the Lord.

31 ፈረስ ለጦርነት ቀን ይዘጋጃል ድል ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።

31 The horse is prepared against the day of battle: but safety is of the Lord.