መጽሐፈ ምሳሌ | MeTsiHaFe MiSaLae
Proverbs of Solomon | Mishlei Shlomo #18
In Amharic and English
መጽሐፈ ምሳሌ 18 |
Proverbs 18 |
1 መለየት የሚወድድ ምኞቱን ይከተላል፥ መልካሙንም ጥበብ ሁሉ ይቃወማል። |
1 Through desire a man, having separated himself, seeketh and intermeddleth with all wisdom. |
2 ሰነፍ የጥበብን ነገር አይወድድም በልቡ ያለውን ሁሉ መግለጥ ብቻ ይወድዳል እንጂ። |
2 A fool hath no delight in understanding, but that his heart may discover itself. |
3 ኀጥእ በመጣ ጊዜ ንቀት ደግሞ ይመጣል፥ ነውርም ከስድብ ጋር። |
3 When the wicked cometh, then cometh also contempt, and with ignominy reproach. |
4 የሰው አፍ ቃል የጠለቀ ውኃ ነው፥ የጥበብም ምንጭ ፈሳሽ ወንዝ ነው። |
4 The words of a man’s mouth are as deep waters, and the wellspring of wisdom as a flowing brook. |
5 የጻድቅ ፍርድ ይጠምም ዘንድ፥ ለኀጥእም ማድላት መልካም አይደለም። |
5 It is not good to accept the person of the wicked, to overthrow the righteous in judgment. |
6 የሰነፍ ከንፈር በጥል ውስጥ ትገባለች፥ አፉም በትርን ትጠራለች። |
6 A fool’s lips enter into contention, and his mouth calleth for strokes. |
7 የሰነፍ አፍ ለራሱ ጥፋት ነው፥ ከንፈሩም ለነፍሱ ወጥመድ ነው። |
7 A fool’s mouth is his destruction, and his lips are the snare of his soul. |
8 የጆሮ ጠቢ ቃል እንደ ጣፋጭ መብል ነው፥ እርሱም እስከ ሆድ ጕርጆች ድረስ ይወርዳል። |
8 The words of a talebearer are as wounds, and they go down into the innermost parts of the belly. |
9 በሥራው ታካች የሚሆን የሀብት አጥፊ ወንድም ነው። |
9 He also that is slothful in his work is brother to him that is a great waster. |
10 የእግዚአብሔር ስም የጸና ግምብ ነው ጻድቅ ወደ እርሱ ሮጦ ከፍ ከፍ ይላል። |
10 The name of the Lord is a strong tower: the righteous runneth into it, and is safe. |
11 ለባለጠጋ ሰው ሀብቱ እንደ ጸናች ከተማ ናት፥ በአሳቡም እንደ ረጅም ቅጥር። |
11 The rich man’s wealth is his strong city, and as an high wall in his own conceit. |
12 ሰው ሳይወድቅ በፊት ልቡ ከፍ ከፍ ይላል፥ ትሕትናም ክብረትን ትቀድማለች። |
12 Before destruction the heart of man is haughty, and before honour is humility. |
13 ሳይሰማ ነገርን በሚመልስ ስንፍናና እፍረት ይሆንበታል። |
13 He that answereth a matter before he heareth it, it is folly and shame unto him. |
14 የሰው ነፍስ ሕመሙን ይታገሣል የተቀጠቀጠን መንፈስ ግን ማን ያጠንክረዋል? |
14 The spirit of a man will sustain his infirmity; but a wounded spirit who can bear? |
15 የአስተዋይ ልብ እውቀትን ያገኛል፥ የጠቢባንም ጆሮ እውቀትን ትፈልጋለች። |
15 The heart of the prudent getteth knowledge; and the ear of the wise seeketh knowledge. |
16 የሰው ስጦታ መንገዱን ታሰፋለታለች፥ በታላላቆችም ፊት ታገባዋለች። |
16 A man’s gift maketh room for him, and bringeth him before great men. |
17 ወደ ፍርድ አስቀድሞ የገባ ጻድቅ ይመስላል ባልንጀራው ግን መጥቶ ይመረምረዋል። |
17 He that is first in his own cause seemeth just; but his neighbour cometh and searcheth him. |
18 ዕጣ ክርክርን ትከለክላለች፥ በኃያላንም መካከል ትበይናለች። |
18 The lot causeth contentions to cease, and parteth between the mighty. |
19 የተበደለ ወንድም እንደ ጸናች ከተማ ጽኑ ነው ክርክራቸውም እንደ ግንብ ብረት ነው። |
19 A brother offended is harder to be won than a strong city: and their contentions are like the bars of a castle. |
20 የሰው ሆድ ከአፉ ፍሬ ይሞላል ከንፈሩም ከሚያፈራው ይጠግባል። |
20 A man’s belly shall be satisfied with the fruit of his mouth; and with the increase of his lips shall he be filled. |
21 ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ ናቸው የሚወድዱአትም ፍሬዋን ይበላሉ። |
21 Death and life are in the power of the tongue: and they that love it shall eat the fruit thereof. |
22 ሚስት ያገኘ በረከትን አገኘ፥ ከእግዚአብሔርም ሞገስን ይቀበላል። |
22 Whoso findeth a wife findeth a good thing, and obtaineth favour of the Lord. |
23 ድሀ በትሕትና እየለመነ ይናገራል ባለጠጋ ግን በድፍረት ይመልሳል። |
23 The poor useth intreaties; but the rich answereth roughly. |
24 ብዙ ወዳጆች ያሉት ሰው ይጠፋል ነገር ግን ከወንድም አብልጦ የሚጠጋጋ ወዳጅ አለ። |
24 A man that hath friends must shew himself friendly: and there is a friend that sticketh closer than a brother. |