መጽሐፈ ምሳሌ | MeTsiHaFe MiSaLae
Proverbs of Solomon | Mishlei Shlomo #25
In Amharic and English
መጽሐፈ ምሳሌ 25 |
Proverbs 25 |
1 እነዚህም ደግሞ የይሁዳ ንጉሥ የሕዝቅያስ ሰዎች የቀዱአቸው የሰሎሞን ምሳሌዎች ናቸው። |
1 These are also proverbs of Solomon, which the men of Hezekiah king of Judah copied out. |
2 የእግዚአብሔር ክብር ነገርን መሰወር ነው የነገሥታት ክብር ግን ነገርን መመርመር ነው። |
2 It is the glory of God to conceal a thing: but the honour of kings is to search out a matter. |
3 እንደ ሰማይ ከፍታ እንደ ምድርም ጥልቀት የነገሥታት ልብ አይመረመርም። |
3 The heaven for height, and the earth for depth, and the heart of kings is unsearchable. |
4 ከብር ዝገትን አስወግድ፥ ፈጽሞም ይጠራል። |
4 Take away the dross from the silver, and there shall come forth a vessel for the finer. |
5 ከንጉሥ ፊት ኀጥኣንን አርቅ፥ ዙፋኑም በጽድቅ ትጸናለች። |
5 Take away the wicked from before the king, and his throne shall be established in righteousness. |
6 በንጉሥ ፊት አትመካ፥ በታላልቆችም ስፍራ አትቁም |
6 Put not forth thyself in the presence of the king, and stand not in the place of great men: |
7 ዓይኖችህ ባዩት በመኰንን ፊት ከምትዋረድ። ወደዚህ ከፍ በል ብትባል ይሻልሃልና። |
7 For better it is that it be said unto thee, Come up hither; than that thou shouldest be put lower in the presence of the prince whom thine eyes have seen. |
8 ባልንጀራህ ባሳፈረህ ጊዜ ኋላ እንዳትጸጸት ለክርክር ፈጥነህ አትውጣ |
8 Go not forth hastily to strive, lest thou know not what to do in the end thereof, when thy neighbour hath put thee to shame. |
9 ክርክርህን ከባልንጀራህ ጋር ተከራከር የሌላ ሰው ምሥጢር ግን አትግለጥ፥ |
9 Debate thy cause with thy neighbour himself; and discover not a secret to another: |
10 የሚሰማ እንዳይነቅፍህ፥ አንተንም ከማነወር ዝም እንዳይል። |
10 Lest he that heareth it put thee to shame, and thine infamy turn not away. |
11 የወርቅ እንኮይ በብር ፃሕል ላይ የጊዜው ቃል እንዲሁ ነው። |
11 A word fitly spoken is like apples of gold in pictures of silver. |
12 የምትሰማን ጆሮ የሚዘልፍ ጠቢብ ሰው እንደ ወርቅ ጉትቻ እንደሚያንጸባርቅም ዕንቍ እንዲሁ ነው። |
12 As an earring of gold, and an ornament of fine gold, so is a wise reprover upon an obedient ear. |
13 በመከር ወራት የውርጭ ጠል ደስ እንደሚያሰኝ፥ እንዲሁ የታመነ መልእክተኛ ለላኩት ነው የጌቶቹን ነፍስ ያሳርፋልና። |
13 As the cold of snow in the time of harvest, so is a faithful messenger to them that send him: for he refresheth the soul of his masters. |
14 ስለ ስጦታው በሐሰት የሚመካ ሰው ዝናብ እንደማይከተለው ደመና ነፋስም ነው። |
14 Whoso boasteth himself of a false gift is like clouds and wind without rain. |
15 በትዕግሥት አለቃ ይለዝባል፥ የገራም ምላስ አጥንትን ይሰብራል። |
15 By long forbearing is a prince persuaded, and a soft tongue breaketh the bone. |
16 አጥብቀህ እንዳትጠግብ እንዳትተፋውም ማር ባገኘህ ጊዜ የሚበቃህን ብላ። |
16 Hast thou found honey? eat so much as is sufficient for thee, lest thou be filled therewith, and vomit it. |
17 እንዳይሰለችህ እንዳይጠላህም እግርህን ወደ ባልንጀራህ ቤት አታዘውትር። |
17 Withdraw thy foot from thy neighbour’s house; lest he be weary of thee, and so hate thee. |
18 በባልንጀራው በሐሰት የሚመሰክር እንደ መዶሻና እንደ ሰይፍ እንደ ተሳለም ፍላጻ ነው። |
18 A man that beareth false witness against his neighbour is a maul, and a sword, and a sharp arrow. |
19 ወስላታውን ሰው በመከራ ጊዜ መተማመን እንደ ተሰበረ ጥርስና እንደ ሰለለ እግር ነው። |
19 Confidence in an unfaithful man in time of trouble is like a broken tooth, and a foot out of joint. |
20 ለሚያዝን ልብ ዝማሬ የሚዘምር፥ ለብርድ ቀን መጐናጸፊያውን እንደሚያስወግድ በቍስልም ላይ እንደ መጻጻ እንዲሁ ነው። |
20 As he that taketh away a garment in cold weather, and as vinegar upon nitre, so is he that singeth songs to an heavy heart. |
21 ጠላትህ ቢራብ እንጀራ አብላው፥ ቢጠማም ውኃ አጠጣው |
21 If thine enemy be hungry, give him bread to eat; and if he be thirsty, give him water to drink: |
22 ፍም በራሱ ላይ ትሰበስባለህና፥ እግዚአብሔርም ዋጋህን ይመልስልሃልና። |
22 For thou shalt heap coals of fire upon his head, and the Lord shall reward thee. |
23 የሰሜን ነፋስ ወጀብ ያመጣል ሐሜተኛ ምላስም የሰውን ፊት ያስቈጣል። |
23 The north wind driveth away rain: so doth an angry countenance a backbiting tongue. |
24 ከጠበኛ ሴት ጋር በአንድ ቤት ከመቀመጥ በሰገነት ማዕዘን መቀመጥ ይሻላል። |
24 It is better to dwell in the corner of the housetop, than with a brawling woman and in a wide house. |
25 የቀዘቀዘ ውኃ ለተጠማች ነፍስ ደስ እንደሚያሰኝ፥ ከሩቅ አገር የመጣ መልካም ምስራች እንዲሁ ነው። |
25 As cold waters to a thirsty soul, so is good news from a far country. |
26 በኀጥእ ፊት የሚወድቅ ጻድቅ እንደደፈረሰ ፈሳሽና እንደ ረከሰ ምንጭ ነው። |
26 A righteous man falling down before the wicked is as a troubled fountain, and a corrupt spring. |
27 ብዙ ማር መብላት መልካም አይደለም እንዲሁም የራስን ክብር መፈላለግ አያስከብርም። |
27 It is not good to eat much honey: so for men to search their own glory is not glory. |
28 ቅጥር እንደሌላት እንደ ፈረሰች ከተማ፥ መንፈሱን የማይከለክል ሰው እንዲሁ ነው። |
28 He that hath no rule over his own spirit is like a city that is broken down, and without walls. |