መጽሐፈ ምሳሌ | MeTsiHaFe MiSaLae
Proverbs of Solomon
| Mishlei Shlomo #15
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

መጽሐፈ ምሳሌ 15

Proverbs 15

1 የለዘበች መልስ ቍጣን ትመልሳለች ሸካራ ቃል ግን ቍጣን ታስነሣለች።

1 A soft answer turneth away wrath: but grievous words stir up anger.

2 የጠቢባን ምላስ እውቀትን ያሳምራል የሰነፎች አፍ ግን ስንፍናን ያፈልቃል።

2 The tongue of the wise useth knowledge aright: but the mouth of fools poureth out foolishness.

3 የእግዚአብሔር ዓይኖች በስፍራ ሁሉ ናቸው ክፉዎችንና ደጎችን ይመለከታሉ።

3 The eyes of the Lord are in every place, beholding the evil and the good.

4 ፈዋሽ ምላስ የሕይወት ዛፍ ነው የጠማማ ምላስ ግን ነፍስን ይሰብራል።

4 A wholesome tongue is a tree of life: but perverseness therein is a breach in the spirit.

5 ሰነፍ የአባቱን ተግሣጽ ይንቃል ዘለፋን የሚቀበል ግን አእምሮው የበዛ ነው።

5 A fool despiseth his father’s instruction: but he that regardeth reproof is prudent.

6 በጻድቅ ሰው ቤት ብዙ ኃይል አለ የኃጥእ ሰው መዝገብ ግን ሁከት ነው።

6 In the house of the righteous is much treasure: but in the revenues of the wicked is trouble.

7 የጠቢባን ከንፈር እውቀትን ትዘራለች የሰነፎች ልብ ግን እንዲህ አይደለም።

7 The lips of the wise disperse knowledge: but the heart of the foolish doeth not so.

8 የኅጥኣን መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው የቅኖች ጸሎት ግን በእርሱ ዘንድ የተወደደ ነው።

8 The sacrifice of the wicked is an abomination to the Lord: but the prayer of the upright is his delight.

9 የኅጥኣን መንገድ በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው እርሱ ግን ጽድቅን የሚከተል ይወድዳል።

9 The way of the wicked is an abomination unto the Lord: but he loveth him that followeth after righteousness.

10 ክፉ መቅሠፍት መንገድን በተወ ሰው ላይ ይመጣል፥ ዘለፋንም የሚጠላ ይሞታል።

10 Correction is grievous unto him that forsaketh the way: and he that hateth reproof shall die.

11 ሲኦልና ጥፋት በእግዚአብሔር ፊት የታወቁ ናቸው ይልቁንም የሰዎች ልብ የታወቀ ነው።

11 Hell and destruction are before the Lord: how much more then the hearts of the children of men?

12 ፌዘኛ ሰው የሚዘልፈውን አይወድድም፥ ወደ ጠቢባንም አይሄድም።

12 A scorner loveth not one that reproveth him: neither will he go unto the wise.

13 ደስ ያለው ልብ ፊትን ያበራል በልብ ኀዘን ግን ነፍስ ትሰበራለች።

13 A merry heart maketh a cheerful countenance: but by sorrow of the heart the spirit is broken.

14 የአዋቂ ልብ እውቀትን ይፈልጋል የሰነፎች አፍ ግን በስንፍና ይሰማራል።

14 The heart of him that hath understanding seeketh knowledge: but the mouth of fools feedeth on foolishness.

15 ልቡ የሚያዝን ሰው ዘመኑ ሁሉ የከፋች ናት የልብ ደስታ ግን ሁልጊዜ እንደ ግብዣ ነው።

15 All the days of the afflicted are evil: but he that is of a merry heart hath a continual feast.

16 እግዚአብሔርን ከመፍራት ጋር ያለ ጥቂት ነገር ሁከት ካለበት ከብዙ መዝገብ ይሻላል።

16 Better is little with the fear of the Lord than great treasure and trouble therewith.

17 የጐመን ወጥ በፍቅር መብላት የሰባ ፍሪዳን ጥል ባለበት ዘንድ ከመብላት ይሻላል።

17 Better is a dinner of herbs where love is, than a stalled ox and hatred therewith.

18 ቍጡ ሰው ጠብን ያነሣሣል ትዕግሥተኛ ሰው ግን ጸጥ ያሰኘዋል።

18 A wrathful man stirreth up strife: but he that is slow to anger appeaseth strife.

19 የታካች መንገድ እንደ እሾህ አጥር ናት የጻድቃን መንገድ ግን የተደላደለች ናት።

19 The way of the slothful man is as an hedge of thorns: but the way of the righteous is made plain.

20 ጠቢብ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል ሰነፍ ልጅ ግን እናቱን ይንቃል።

20 A wise son maketh a glad father: but a foolish man despiseth his mother.

21 ልብ ለሌለው ሰው ስንፍና ደስታ ናት አስተዋይ ግን አካሄዱን ያቀናል።

21 Folly is joy to him that is destitute of wisdom: but a man of understanding walketh uprightly.

22 ምክር ከሌለች ዘንድ የታሰበው ሳይሳካ ይቀራል መካሮች በበዙበት ዘንድ ግን ይጸናል።

22 Without counsel purposes are disappointed: but in the multitude of counsellors they are established.

23 ሰው በአፉ መልስ ደስ ይለዋል ቃልም በጊዜው ምንኛ መልካም ነው!

23 A man hath joy by the answer of his mouth: and a word spoken in due season, how good is it!

24 በታች ካለው ከሲኦል ያመልጥ ዘንድ የሕይወት መንገድ አስተዋዩን ሰው ወደ ላይ ይወስደዋል።

24 The way of life is above to the wise, that he may depart from hell beneath.

25 እግዚአብሔር የትዕቢተኞች ቤት ይነቅላል የባልቴትን ዳርቻ ግን ያጸናል።

25 The Lord will destroy the house of the proud: but he will establish the border of the widow.

26 የበደለኛ አሳብ በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ናት ያማረ ቃል ግን ጥሩ ነው።

26 The thoughts of the wicked are an abomination to the Lord: but the words of the pure are pleasant words.

27 ትርፍ ለማግኘት የሚሳሳ ሰው የራሱን ቤት ያውካል መማለጃን የሚጠላ ግን በሕይወት ይኖራል።

27 He that is greedy of gain troubleth his own house; but he that hateth gifts shall live.

28 የጻድቅ ልብ መልሱን ያስባል የኅጥኣን አፍ ግን ክፋትን ያፈልቃል።

28 The heart of the righteous studieth to answer: but the mouth of the wicked poureth out evil things.

29 እግዚአብሔር ከኅጥኣን ይርቃል የጻድቃንን ጸሎት ግን ይሰማል።

29 The Lord is far from the wicked: but he heareth the prayer of the righteous.

30 የዓይን ብርሃን ልብን ደስ ያሰኛል፥ መልካም ወሬም አጥንትን ያለመልማል።

30 The light of the eyes rejoiceth the heart: and a good report maketh the bones fat.

31 የሕይወትን ተግሣጽ የሚሰማ ጆሮ በጠቢባን መካከል ይኖራል።

31 The ear that heareth the reproof of life abideth among the wise.

32 ተግሣጽን ቸል የሚል የራሱን ነፍስ ይንቃል ዘለፋን የሚሰማ ግን አእምሮ ያገኛል።

32 He that refuseth instruction despiseth his own soul: but he that heareth reproof getteth understanding.

33 እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ ትምህርት ነው ትሕትናም ክብረትን ትቀድማለች።

33 The fear of the Lord is the instruction of wisdom; and before honour is humility.