መጽሐፈ ምሳሌ | MeTsiHaFe MiSaLae
Proverbs of Solomon
| Mishlei Shlomo #29
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

መጽሐፈ ምሳሌ 29

Proverbs 29

1 ብዙ ጊዜ ተዘልፎ አንገቱን ያደነደነ ድንገት ይሰበራል፥ ፈውስም የለውም።

1 He, that being often reproved hardeneth his neck, shall suddenly be destroyed, and that without remedy.

2 ጻድቃን በበዙ ጊዜ ሕዝብ ደስ ይለዋል ኀጥኣን በሠለጠኑ ጊዜ ግን ሕዝብ ያለቅሳል።

2 When the righteous are in authority, the people rejoice: but when the wicked beareth rule, the people mourn.

3 ጥበብን የወደደ ሰው አባቱን ደስ ያሰኛል ጋለሞቶችን የሚከተል ግን ሀብቱን ያጠፋል።

3 Whoso loveth wisdom rejoiceth his father: but he that keepeth company with harlots spendeth his substance.

4 ንጉሥ በፍርድ አገሩን ያጸናል መማለጃ የሚወድድ ግን ያፈርሰዋል።

4 The king by judgment establisheth the land: but he that receiveth gifts overthroweth it.

5 ወዳጁን በለዘበ ቃል የሚናገር ሰው ለእግሩ መርበብን ይዘረጋል።

5 A man that flattereth his neighbour spreadeth a net for his feet.

6 በክፉ ሰው ዓመፃ ወጥመድ ይገኛል ጻድቅ ግን ደስ ይለዋል፥ እልልም ይላል።

6 In the transgression of an evil man there is a snare: but the righteous doth sing and rejoice.

7 ጻድቅ የድሆችን ፍርድ ይመለከታል ኀጥእ ግን እውቀትን አያስተውልም።

7 The righteous considereth the cause of the poor: but the wicked regardeth not to know it.

8 ፌዘኞች ከተማቸውን ያቃጥላሉ ጠቢባን ግን ቍጣን ይመልሳሉ።

8 Scornful men bring a city into a snare: but wise men turn away wrath.

9 ጠቢብ ከሰነፍ ጋር ቢጣላ፥ ሰነፍ ወይም ይቈጣል ወይም ይስቃል፥ ዕረፍትም የለም።

9 If a wise man contendeth with a foolish man, whether he rage or laugh, there is no rest.

10 ደምን ለማፍሰስ የሚሹ ሰዎች ፍጹሙን ሰው ይጠላሉ፥ ደግሞም የቅኑን ሰው ነፍስ ይሻሉ።

10 The bloodthirsty hate the upright: but the just seek his soul.

11 ሰነፍ ሰው ቍጣውን ሁሉ ያወጣል ጠቢብ ግን በውስጡ ያስቀረዋል።

11 A fool uttereth all his mind: but a wise man keepeth it in till afterwards.

12 መኰንን ሐሰተኛ ነገርን ቢያደምጥ፥ ከእርሱ በታች ያሉት ሁሉ ዓመፅኞች ይሆናሉ።

12 If a ruler hearken to lies, all his servants are wicked.

13 ድሀና ግፈኛ ተገናኙ እግዚአብሔር የሁለቱንም ዓይን ያበራል።

13 The poor and the deceitful man meet together: the Lord lighteneth both their eyes.

14 ለድሀ በእውነት የሚፈርድ ንጉሥ፥ ዙፋኑ ለዘላለም ይጸናል።

14 The king that faithfully judgeth the poor, his throne shall be established for ever.

15 በትርና ተግሣጽ ጥበብን ይሰጣሉ ያልተቀጣ ብላቴና ግን እናቱን ያሳፍራል።

15 The rod and reproof give wisdom: but a child left to himself bringeth his mother to shame.

16 ኀጥኣን ሲበዙ ኃጢአት ትበዛለች ጻድቃን ግን ውደቀታቸውን ያያሉ።

16 When the wicked are multiplied, transgression increaseth: but the righteous shall see their fall.

17 ልጅህን ቅጣ ዕረፍትንም ይሰጥሃል ለነፍስህም ተድላን ይሰጣታል።

17 Correct thy son, and he shall give thee rest; yea, he shall give delight unto thy soul.

18 ራእይ ባይኖር ሕዝብ መረን ይሆናል ሕግን የሚጠብቅ ግን የተመሰገነ ነው።

18 Where there is no vision, the people perish: but he that keepeth the law, happy is he.

19 ባሪያ በቃል አይገሠጽም ቢያስተውል እንኳ አይመልስምና።

19 A servant will not be corrected by words: for though he understand he will not answer.

20 በቃሉ የሚቸኵለውን ሰው ብታይ፥ ከእርሱ ይልቅ ለሰነፍ ተስፋ አለው።

20 Seest thou a man that is hasty in his words? there is more hope of a fool than of him.

21 ባሪያውን ከሕፃንነቱ ጀምሮ በማቀማጠል የሚያሳድግ የኋላ ኋላ እንደ ጌታ ያደርገዋል።

21 He that delicately bringeth up his servant from a child shall have him become his son at the length.

22 ቍጡ ሰው ክርክርን ያነሣሣል። ወፈፍተኛ ሰውም ኃጢአትን ያበዛል።

22 An angry man stirreth up strife, and a furious man aboundeth in transgression.

23 ሰውን ትዕቢቱ ያዋርደዋል መንፈሱን የሚያዋርድ ግን ክብርን ይቀበላል።

23 A man’s pride shall bring him low: but honour shall uphold the humble in spirit.

24 ከሌባ ጋር የሚካፈል ነፍሱን ይጠላል መርገምን ይሰማል፥ ነገር ግን ምንም አይገልጥም።

24 Whoso is partner with a thief hateth his own soul: he heareth cursing, and bewrayeth it not.

25 ሰውን መፍራት ወጥመድ ያመጣል በእግዚአብሔር የሚታመን ግን እርሱ ይጠበቃል።

25 The fear of man bringeth a snare: but whoso putteth his trust in the Lord shall be safe.

26 ብዙ ሰዎች የሹምን ፊት ይሻሉ የሰው ፍርድ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።

26 Many seek the ruler’s favour; but every man’s judgment cometh from the Lord.

27 ኃጢአተኛ በጻድቃን ዘንድ አስጸያፊ ነው በቀና መንገድ የሚሄደውም በኀጥኣን ዘንድ አስጸያፊ ነው።

27 An unjust man is an abomination to the just: and he that is upright in the way is abomination to the wicked.