መጽሐፈ ምሳሌ | MeTsiHaFe MiSaLae
Proverbs of Solomon | Mishlei Shlomo #12
In Amharic and English
መጽሐፈ ምሳሌ 12 |
Proverbs 12 |
1 ተግሣጽን የሚወድድ እውቀትን ይወድዳል ዘለፋን የሚጠላ ግን ደንቆሮ ነው። |
1 Whoso loveth instruction loveth knowledge: but he that hateth reproof is brutish. |
2 ደኅና ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስን ያገኛል ተንኰለኛውን ሰው ግን ይቀሥፈዋል። |
2 A good man obtaineth favour of the Lord: but a man of wicked devices will he condemn. |
3 ሰውን ዓመፃ አያጸናውም የጻድቃን ሥር ግን አይንቀሳቀስም። |
3 A man shall not be established by wickedness: but the root of the righteous shall not be moved. |
4 ልባም ሴት ለባልዋ ዘውድ ናት አሳፋሪ ሴት ግን በአጥንቱ ውስጥ እንደ ቅንቅን ናት። |
4 A virtuous woman is a crown to her husband: but she that maketh ashamed is as rottenness in his bones. |
5 የጻድቃን አሳብ ቅን ነው የኃጥኣን ምክር ግን ተንኰል ነው። |
5 The thoughts of the righteous are right: but the counsels of the wicked are deceit. |
6 የኃጥኣን ቃል ደምን ለማፍሰስ ትሸምቃለች የቅኖች አፍ ግን ይታደጋቸዋል። |
6 The words of the wicked are to lie in wait for blood: but the mouth of the upright shall deliver them. |
7 ኀጥኣን ይገለበጣሉ፥ ደግሞም አይገኙም የጻድቃን ቤት ግን ጸንቶ ይኖራል። |
7 The wicked are overthrown, and are not: but the house of the righteous shall stand. |
8 ሰው በጥበቡ ይመሰገናል ልቡ ጠማማ የሆነ ሰው ግን ይናቃል። |
8 A man shall be commended according to his wisdom: but he that is of a perverse heart shall be despised. |
9 ለራሱ ባሪያ ሆኖ የተጠቃ ሰው እንጀራ ጐድሎት ራሱን ካከበረው ሰው ይሻላል። |
9 He that is despised, and hath a servant, is better than he that honoureth himself, and lacketh bread. |
10 ጻድቅ ሰው ለእንስሳው ነፍስ ይራራል የኀጥኣን ምሕረት ግን ጨካኝ ነው። |
10 A righteous man regardeth the life of his beast: but the tender mercies of the wicked are cruel. |
11 ምድሩን የሚሠራ ሰው እንጀራ ይጠግባል ለከንቱ ነገር የሚሮጥ ግን አእምሮ የጐደለው ነው። |
11 He that tilleth his land shall be satisfied with bread: but he that followeth vain persons is void of understanding. |
12 የኅጥኣን ፈቃድ የክፉዎች ወጥመድ ናት የጻድቃን ሥር ግን ፍሬን ያፈራል። |
12 The wicked desireth the net of evil men: but the root of the righteous yieldeth fruit. |
13 ክፉ ሰው በከንፈሩ ኃጢአት ይጠመዳል ጻድቅ ግን ከመከራ ያመልጣል። |
13 The wicked is snared by the transgression of his lips: but the just shall come out of trouble. |
14 የሰው ነፍስ ከአፉ ፍሬ መልካም ነገርን ትጠግባለች፥ ሰውም እንደ እጁ ሥራ ዋጋውን ይቀበላል። |
14 A man shall be satisfied with good by the fruit of his mouth: and the recompence of a man’s hands shall be rendered unto him. |
15 የሰነፍ መንገድ በዓይኑ የቀናች ናት ጠቢብ ግን ምክርን ይሰማል። |
15 The way of a fool is right in his own eyes: but he that hearkeneth unto counsel is wise. |
16 የሰነፍ ቍጣ ቶሎ ይታወቃል ብልህ ሰው ግን ነውርን ይሰውራል። |
16 A fool’s wrath is presently known: but a prudent man covereth shame. |
17 እውነተኛን ነገር የሚናገር ቅን ነገርን ያወራል የሐሰት ምስክር ግን ተንኰልን ያወራል። |
17 He that speaketh truth sheweth forth righteousness: but a false witness deceit. |
18 እንደሚዋጋ ሰይፍ የሚለፈልፍ ሰው አለ የጠቢባን ምላስ ግን ጤና ነው። |
18 There is that speaketh like the piercings of a sword: but the tongue of the wise is health. |
19 የእውነት ከንፈር ለዘላለም ትቆማለች ውሸተኛ ምላስ ግን ለቅጽበት ነው። |
19 The lip of truth shall be established for ever: but a lying tongue is but for a moment. |
20 ክፉን በሚያስቡ ልብ ውስጥ ተንኰል አለ በሰላም ለሚመክሩ ግን ደስታ አላቸው። |
20 Deceit is in the heart of them that imagine evil: but to the counsellors of peace is joy. |
21 ጻድቅን መከራ አያገኘውም ኀጥኣን ግን ክፋትን የተሞሉ ናቸው። |
21 There shall no evil happen to the just: but the wicked shall be filled with mischief. |
22 ውሸተኛ ከንፈር በእግዚአብሔር ዘንድ አሰጸያፊ ነው እውነትን የሚያደርጉ ግን በእርሱ ዘንድ የተወደዱ ናቸው። |
22 Lying lips are abomination to the Lord: but they that deal truly are his delight. |
23 ብልህ ሰው እውቀትን ይሸሽጋል የሰነፎች ልብ ግን ስንፍናን ያወራል። |
23 A prudent man concealeth knowledge: but the heart of fools proclaimeth foolishness. |
24 የትጉ እጅ ትገዛለች የታካች እጅ ግን ትገብራለች። |
24 The hand of the diligent shall bear rule: but the slothful shall be under tribute. |
25 ሰውን የልቡ ኀዘን ያዋርደዋል መልካም ቃል ግን ደስ ያሰኘዋል። |
25 Heaviness in the heart of man maketh it stoop: but a good word maketh it glad. |
26 ጻድቅ ለባልንጀራው መንገዱን ያሳያል የኀጥኣን መንገድ ግን ታስታቸዋለች። |
26 The righteous is more excellent than his neighbour: but the way of the wicked seduceth them. |
27 ታካች ሰው አደን ምንም አያድንም ለሰው የከበረ ሀብት ትጋት ነው። |
27 The slothful man roasteth not that which he took in hunting: but the substance of a diligent man is precious. |
28 በጽድቅ መንገድ ላይ ሕይወት አለ በጎዳናዋም ሞት የለም። |
28 In the way of righteousness is life; and in the pathway thereof there is no death. |