ኦሪት ዘሌዋውያን Orit ZeLaeWaWiYan
Leviticus / Vayikra #24
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

 

ኦሪት ዘሌዋውያን 24

Leviticus 24

1 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው።

1 And the Lord spake unto Moses, saying,

2 መብራቱን ሁልጊዜ እንድታበራበት ለመብራት ጥሩ ተወቅጦ የተጠለለ የወይራ ዘይት ያመጡልህ ዘንድ የእስራኤልን ልጆች እዘዛቸው።

2 Command the children of Israel, that they bring unto thee pure oil olive beaten for the light, to cause the lamps to burn continually.

3 በምስክሩ መጋረጃ ውጭ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ አሮን ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በእግዚአብሔር ፊት ሁልጊዜ ያሰናዳው ለዘላለም ለልጅ ልጃችሁ ሥርዓት ይሁን።

3 Without the vail of the testimony, in the tabernacle of the congregation, shall Aaron order it from the evening unto the morning before the Lord continually: it shall be a statute for ever in your generations.

4 በእግዚአብሔር ፊት በጥሩ መቅረዝ ላይ መብራቶቹን ሁልጊዜ ያሰናዳቸው።

4 He shall order the lamps upon the pure candlestick before the Lord continually.

5 መልካሙንም ዱቄት ወስደህ አሥራ ሁለት ኅብስት ጋግር በአንድ ኅብስት ውስጥ ከመስፈሪያው ከአሥር እጅ ሁለት እጅ ይሁን።

5 And thou shalt take fine flour, and bake twelve cakes thereof: two tenth deals shall be in one cake.

6 እነዚህንም ስድስት ስድስቱን በሁለት ተርታ አድርገህ በእግዚአብሔር ፊት በጥሩ ገበታ ላይ አኑራቸው።

6 And thou shalt set them in two rows, six on a row, upon the pure table before the Lord.

7 ለእግዚአብሔርም ለእሳት ቍርባን በእንጀራው ላይ ለመታሰቢያ ይሆን ዘንድ በሁለቱ ተርታ ላይ ጥሩ ዕጣን አድርግ።

7 And thou shalt put pure frankincense upon each row, that it may be on the bread for a memorial, even an offering made by fire unto the Lord.

8 በእግዚአብሔር ፊት ሁልጊዜ በሰንበት ቀን ሁሉ በተርታ ያድርገው በእስራኤል ልጆች ዘንድ የዘላለም ቃል ኪዳን ነው።

8 Every sabbath he shall set it in order before the Lord continually, being taken from the children of Israel by an everlasting covenant.

9 ለአሮንና ለልጆቹም ይሁን በእሳት ከተደረገው ከእግዚአብሔር ቍርባን በዘላለም ሥርዓት ለእርሱ ቅዱሰ ቅዱሳን ነውና በተቀደሰ ስፍራ ይብሉት።

9 And it shall be Aaron’s and his sons’; and they shall eat it in the holy place: for it is most holy unto him of the offerings of the Lord made by fire by a perpetual statute.

10 አባቱ ግብፃዊ የነበረ የእስራኤላዊት ልጅ በእስራኤል ልጆች መካከል ወጣ የእስራኤላዊቱ ልጅና አንድ እስራኤላዊ በሰፈር ውስጥ ተጣሉ

10 And the son of an Israelitish woman, whose father was an Egyptian, went out among the children of Israel: and this son of the Israelitish woman and a man of Israel strove together in the camp;

11 የእስራኤላዊቱም ልጅ የእግዚአብሔርን ስም ሰደበ፥ አቃለለውም ወደ ሙሴም አመጡት። እናቱም ከዳን ነገድ የደብራይ ልጅ ነበረች፥ ስምዋም ሰሎሚት ነበረ።

11 And the Israelitish woman’s son blasphemed the name of the Lord, and cursed. And they brought him unto Moses: (and his mother’s name was Shelomith, the daughter of Dibri, of the tribe of Dan:)

12 ከእግዚአብሔርም አፍ ስለ እርሱ ፍርድ እስኪወጣላቸው ድረስ በግዞት አኖሩት።

12 And they put him in ward, that the mind of the Lord might be shewed them.

13 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው።

13 And the Lord spake unto Moses, saying,

14 ተሳዳቢውን ከስፈሩ ወደ ውጭ አውጣው የሰሙትም ሁሉ እጃቸውን በራሱ ላይ ይጫኑበት ማኅበሩም ሁሉ ይውገረው።

14 Bring forth him that hath cursed without the camp; and let all that heard him lay their hands upon his head, and let all the congregation stone him.

15 ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ ብለህ ትነግራለህ። ማናቸውም ሰው አምላኩን ቢሰድብ ኃጢአቱን ይሸከማል።

15 And thou shalt speak unto the children of Israel, saying, Whosoever curseth his God shall bear his sin.

16 የእግዚአብሔርንም ስም የሚሰድብ ፈጽሞ ይገደል ማኅበሩም ሁሉ ይውገሩት መጻተኛ ወይም የአገር ልጅ ቢሆን፥ የእግዚአብሔርን ስም በሰደበ ጊዜ ይገደል።

16 And he that blasphemeth the name of the Lord, he shall surely be put to death, and all the congregation shall certainly stone him: as well the stranger, as he that is born in the land, when he blasphemeth the name of the Lord, shall be put to death.

17 ሰውንም እስኪሞት ድረስ የሚመታ ፈጽሞ ይገደል።

17 And he that killeth any man shall surely be put to death.

18 እንስሳንም እስኪሞት ድረስ የሚመታ ሕይወት በሕይወት ፋንታ ካሣውን ይክፈል።

18 And he that killeth a beast shall make it good; beast for beast.

19 ሰውም ባልንጀራውን ቢጐዳ፥ እርሱ እንዳደረገ እንዲሁ ይደረግበት።

19 And if a man cause a blemish in his neighbour; as he hath done, so shall it be done to him;

20 ስብራት በስብራት ፋንታ፥ ዓይን በዓይን ፋንታ፥ ጥርስ በጥርስ ፋንታ፥ ሰውን እንደ ጐዳ እንዲሁ ይደረግበት።

20 Breach for breach, eye for eye, tooth for tooth: as he hath caused a blemish in a man, so shall it be done to him again.

21 እንስሳውንም የሚገድል ካሣ ይተካ ሰውንም የሚገድል ይገደል።

21 And he that killeth a beast, he shall restore it: and he that killeth a man, he shall be put to death.

22 እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና ለመጻተኛና ለአገር ልጅ አንድ ዓይነት ሕግ ይሁንላችሁ።

22 Ye shall have one manner of law, as well for the stranger, as for one of your own country: for I am the Lord your God.

23 ሙሴም ለእስራኤል ልጆች ተናገራቸው ተሳዳቢውንም ከሰፈሩ ወደ ውጭ አወጡት፥ በድንጋይም ወገሩት። የእስራኤልም ልጆች እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ።

23 And Moses spake to the children of Israel, that they should bring forth him that had cursed out of the camp, and stone him with stones. And the children of Israel did as the Lord commanded Moses.