መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David #64
In Amharic and English
መዝሙረ ዳዊት 64 |
Psalm 64 |
1 አቤቱ፥ ወደ አንተ በለመንሁ ጊዜ ጸሎቴን ስማኝ፥ ከጠላትም ፍርሃት ነፍሴን አድን። |
1 Hear my voice, O God, in my prayer: preserve my life from fear of the enemy. |
2 ከክፉዎች ሸንጎ ከዓመፀኞችም ብዛት ሰውረኝ። |
2 Hide me from the secret counsel of the wicked; from the insurrection of the workers of iniquity: |
3 እንደ ሰይፍ ምላሳቸውን አሰሉ መራራ ነገርን ለማድረግ፥ |
3 Who whet their tongue like a sword, and bend their bows to shoot their arrows, even bitter words: |
4 ንጹሕንም በስውር ለመንደፍ ቀስትን ገተሩ ድንገት ይነድፉታል አይፈሩምም። |
4 That they may shoot in secret at the perfect: suddenly do they shoot at him, and fear not. |
5 ለእነርሱ ለራሳቸው ክፉ ነገርን አጸኑ ወጥመድን ይሰውሩ ዘንድ ተማከሩ ማንስ ያየናል? ይላሉ። |
5 They encourage themselves in an evil matter: they commune of laying snares privily; they say, Who shall see them? |
6 ዓመፃን ፈልጓት፥ ሲፈትኑም አለቁ የሰው የውስጥ አሳቡና ልቡ የጠለቀ ነው፥ |
6 They search out iniquities; they accomplish a diligent search: both the inward thought of every one of them, and the heart, is deep. |
7 እግዚአብሔርም ከፍ ከፍ ይላል። የድንገትም ፍላጻ ያቈስላቸዋል |
7 But God shall shoot at them with an arrow; suddenly shall they be wounded. |
8 አንደበታቸው ያሰናክላቸዋል፥ የሚያዩአቸውም ሁሉ ይደነግጣሉ። |
8 So they shall make their own tongue to fall upon themselves: all that see them shall flee away. |
9 ሰዎች ሁሉ ፈሩ፥ የእግዚአብሔርንም ሥራ ተናገሩ፥ ሥራውንም አስተዋሉ። |
9 And all men shall fear, and shall declare the work of God; for they shall wisely consider of his doing. |
10 ጻድቅ በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል፥ በእርሱም ይታመናል ልባቸውም የቀና ሁሉ እልል ይላሉ። |
10 The righteous shall be glad in the Lord, and shall trust in him; and all the upright in heart shall glory. |