መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David #63
In Amharic and English
መዝሙረ ዳዊት 63 |
Psalm 63 |
1 አምላኬ፥ አምላኬ፥ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ ነፍሴ አንተን ተጠማች፥ ሥጋዬ አንተን እንዴት ናፈቀች እንጨትና ውኃ በሌለበት በምድረ በዳ። |
1 O God, thou art my God; early will I seek thee: my soul thirsteth for thee, my flesh longeth for thee in a dry and thirsty land, where no water is; |
2 ኃይልህንና ክብርህን አይ ዘንድ እንዲሁ በመቅደስ ውስጥ ተመለከትሁህ። |
2 To see thy power and thy glory, so as I have seen thee in the sanctuary. |
3 ምሕረትህ ከሕይወት ይሻላልና ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል። |
3 Because thy lovingkindness is better than life, my lips shall praise thee. |
4 እንዲህ በሕይወቴ ዘመን አመሰግንሃለሁ፥ በአንተም ስም እጆቼን አነሣለሁ። |
4 Thus will I bless thee while I live: I will lift up my hands in thy name. |
5 ነፍሴ በቅቤና በስብ እንደሚጠግቡ ትጠግባለች፥ ከንፈሮቼም ስምህን በደስታ ያመሰግናሉ። |
5 My soul shall be satisfied as with marrow and fatness; and my mouth shall praise thee with joyful lips: |
6 በመኝታዬም አስብሃለሁ፥ በማለዳም እናገርልሃለሁ |
6 When I remember thee upon my bed, and meditate on thee in the night watches. |
7 ረዳቴ ሆነኸኛልና፥ በክንፎችህም ጥላ ደስ ይለኛልና። |
7 Because thou hast been my help, therefore in the shadow of thy wings will I rejoice. |
8 ነፍሴ በኋላህ ተከታተለች፥ እኔንም ቀኝህ ተቀበለችኝ። |
8 My soul followeth hard after thee: thy right hand upholdeth me. |
9 እነርሱ ግን ነፍሴን ለከንቱ ፈለጓት ወደ ምድር ጥልቅ ይገባሉ። |
9 But those that seek my soul, to destroy it, shall go into the lower parts of the earth. |
10 ለሰይፍ እጅ አልፈው ይሰጣሉ፥ የቀበሮም እድል ፈንታ ይሆናሉ። |
10 They shall fall by the sword: they shall be a portion for foxes. |
11 ንጉሥ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል በእርሱ የሚምል ሁሉ ይከብራል፥ ሐሰትን የሚናገር አፍ ይዘጋልና። |
11 But the king shall rejoice in God; every one that sweareth by him shall glory: but the mouth of them that speak lies shall be stopped. |