መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David  #62
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

መዝሙረ ዳዊት 62

Psalm 62

1 ነፍሴ ለእግዚአብሔር የምትገዛ አይደለችምን? መድኃኒቴ ከእርሱ ዘንድ ናትና።

1 Truly my soul waiteth upon God: from him cometh my salvation.

2 እርሱ አምላኬ መድኃኒቴም ነውና እርሱ መጠጊያዬ ነው፥ እጅግም አልታወክም።

2 He only is my rock and my salvation; he is my defence; I shall not be greatly moved.

3 እስከ መቼ በሰው ላይ ትቆማላችሁ? እናንተ ሁላችሁ እንዳዘነበለ ግድግዳ እንደ ፈረሰም ቅጥር ትገድላላችሁ።

3 How long will ye imagine mischief against a man? ye shall be slain all of you: as a bowing wall shall ye be, and as a tottering fence.

4 ነገር ግን ክብሬን ይሽሩ ዘንድ መከሩ፥ ሐሰትንም ይወድዳሉ በአፋቸው ይባርካሉ፥ በልባቸውም ይረግማሉ።

4 They only consult to cast him down from his excellency: they delight in lies: they bless with their mouth, but they curse inwardly. Selah.

5 ነገር ግን፥ ነፍሴ ሆይ፥ አንቺ ለእግዚአብሔር ተገዢ፥ ተስፋዬ ከእርሱ ዘንድ ናትና።

5 My soul, wait thou only upon God; for my expectation is from him.

6 እርሱ አምላኬ መድኃኒቴም ነውና እርሱ መጠጊያዬ ነው አልታወክም።

6 He only is my rock and my salvation: he is my defence; I shall not be moved.

7 መድኃኒቴና ክብሬ በእግዚአብሔር ነው የረድኤቴ አምላክ ተስፋዬም እግዚአብሔር ነው።

7 In God is my salvation and my glory: the rock of my strength, and my refuge, is in God.

8 የሕዝብ ማኅበር ሁላችሁ፥ በእርሱ ታመኑ፥ ልባችሁንም በፊቱ አፍስሱ እግዚአብሔር ረዳታችን ነው።

8 Trust in him at all times; ye people, pour out your heart before him: God is a refuge for us. Selah.

9 ነገር ግን የሰው ልጆች ከንቱ ናቸው፥ የሰው ልጆችም ሐሰተኞች ናቸው በሚዛንም ይበድላሉ፥ እነርሱስ በፍጹም ከንቱ ናቸው።

9 Surely men of low degree are vanity, and men of high degree are a lie: to be laid in the balance, they are altogether lighter than vanity.

10 ዓመፃን ተስፋ አታድርጉ፥ ቅሚያንም አትተማመኑት ባለጠግነት ቢበዛ ልባችሁ አይኵራ።

10 Trust not in oppression, and become not vain in robbery: if riches increase, set not your heart upon them.

11 እግዚአብሔር አንድ ጊዜ ተናገረ፥ እኔም ይህን ብቻ ሰማሁ ኃይል የእግዚአብሔር ነው፥

11 God hath spoken once; twice have I heard this; that power belongeth unto God.

12 አቤቱ፥ ምሕረትም ያንተ ነው አንተ ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ፍዳውን ትሰጣለህና።

12 Also unto thee, O Lord, belongeth mercy: for thou renderest to every man according to his work.