ኦሪት ዘፍጥረት Orit ZeFiTret
Genesis / Bereisheit #36
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

ኦሪት ዘፍጥረት 36

Genesis 36

1 የዔሳው ትውልድ ይህ ነው እርሱም ኤዶም ነው።

1 Now these are the generations of Esau, who is Edom.

2 ዔሳው ከከነዓን ልጆች ሚስቶችን አገባ የኬጢያዊውን የዔሎንን ልጅ ዓዳን፥ የኤዊያዊው የፅብዖን ልጅ ዓና የወለዳትን አህሊባማን፥

2 Esau took his wives of the daughters of Canaan; Adah the daughter of Elon the Hittite, and Aholibamah the daughter of Anah the daughter of Zibeon the Hivite;

3 የእስማኤልን ልጅ የነባዮትን እኅት ቤሴሞትን።

3 And Bashemath Ishmael’s daughter, sister of Nebajoth.

4 ዓዳ ለዔሳው ኤልፋዝን ወለደች ቤሴሞትም ራጉኤልን ወለደች

4 And Adah bare to Esau Eliphaz; and Bashemath bare Reuel;

5 አህሊባማም የዑስን፥ የዕላምን፥ ቆሬን ወለደች በከነዓን ምድር የተወለዱለት የዔሳው ልጆች እነዚህ ናቸው።

5 And Aholibamah bare Jeush, and Jaalam, and Korah: these are the sons of Esau, which were born unto him in the land of Canaan.

6 ዔሳውም ሚስቶቹን ወንዶች ልጆቹንና ሴቶች ልጆቹን ቤተሰቡንም ሁሉ ከብቱንም ሁሉ እንስሶቹንም ሁሉ በከነዓንም አገር ያገኘውን ሁሉ ይዞ ከወንድሙ ከያዕቆብ ፊት ወደ ሌላ አገር ሄደ።

6 And Esau took his wives, and his sons, and his daughters, and all the persons of his house, and his cattle, and all his beasts, and all his substance, which he had got in the land of Canaan; and went into the country from the face of his brother Jacob.

7 ከብታቸው ስለ በዛ በአንድነት ይቀመጡ ዘንድ አልቻሉም በእንግድነት የተቀመጡባትም ምድር ከከብታቸው ብዛት የተነሣ ልትበቃቸው አልቻለችም።

7 For their riches were more than that they might dwell together; and the land wherein they were strangers could not bear them because of their cattle.

8 ዔሳውም በሴይር ተራራ ተቀመጠ ዔሳውም ኤዶም ነው።

8 Thus dwelt Esau in mount Seir: Esau is Edom.

9 በሴይር ተራራ የሚኖሩ የኤዶማውያን አባት የዔሳው ትውልድም ይህ ነው።

9 And these are the generations of Esau the father of the Edomites in mount Seir:

10 የዔሳው ልጆች ስም ይህ ነው የዔሳው ሚስት የዓዳ ልጅ ኤልፋዝ የዔሳው ሚስት የቤሴሞት ልጅ ራጉኤል።

10 These are the names of Esau’s sons; Eliphaz the son of Adah the wife of Esau, Reuel the son of Bashemath the wife of Esau.

11 የኤልፋዝም ልጆች እነዚህ ናቸው ቴማን፥ ኦማር፥ ስፎ፥ ጎቶም፥ ቄኔዝ።

11 And the sons of Eliphaz were Teman, Omar, Zepho, and Gatam, and Kenaz.

12 ቲምናዕም ለዔሳው ልጅ ለኤልፋዝ የጭን ገረድ ነበረች፥ አማሌቅንም ለኤልፋዝ ወለደችለት የዔሳው ሚስት የዓዳ ልጆች እነዚህ ናቸው።

12 And Timna was concubine to Eliphaz Esau’s son; and she bare to Eliphaz Amalek: these were the sons of Adah Esau’s wife.

13 የራጉኤልም ልጆች እነዚህ ናቸው ናሖት፥ ዛራ፥ ሣማ፥ ሚዛህ እነዚህም የዔሳው ሚስት የቤሴሞት ልጆች ናቸው።

13 And these are the sons of Reuel; Nahath, and Zerah, Shammah, and Mizzah: these were the sons of Bashemath Esau’s wife.

14 የፅብዖን ልጅ የዓና ልጅ የዔሳው ሚስት የአህሊባማ ልጆች እነዚህ ናቸው ለዔሳውም የዑስን፥ የዕላማን፥ ቆሬን ወለደች።

14 And these were the sons of Aholibamah, the daughter of Anah the daughter of Zibeon, Esau’s wife: and she bare to Esau Jeush, and Jaalam, and Korah.

15 የዔሳው ልጆች አለቆች እነዚህ ናቸው ለዔሳው የበኵር ለኤልፋዝ ልጆች ቴማን አለቃ፥ ኦማር አለቃ፥ ስፎ አለቃ፥ ቄኔዝ አለቃ፥

15 These were dukes of the sons of Esau: the sons of Eliphaz the firstborn son of Esau; duke Teman, duke Omar, duke Zepho, duke Kenaz,

16 ቆሬ አለቃ፥ ጎቶም አለቃ፥ አማሌቅ አለቃ በኤዶም ምድር የኤልፋዝ አለቆች እነዚህ ናቸው እነዚህ የዓዳ ልጆች ናቸው።

16 Duke Korah, duke Gatam, and duke Amalek: these are the dukes that came of Eliphaz in the land of Edom; these were the sons of Adah.

17 የዔሳው ልጅ የራጉኤል ልጆች እነዚህ ናቸው ናሖት አለቃ፥ ዛራ አለቃ፥ ሣማ አለቃ፥ ሚዛህ አለቃ በኤዶም ምድር የራጉኤል ልጆች አለቆች እነዚህ ናቸው እነዚህም የዔሳው ሚስት የቤሴሞት ልጆች ናቸው።

17 And these are the sons of Reuel Esau’s son; duke Nahath, duke Zerah, duke Shammah, duke Mizzah: these are the dukes that came of Reuel in the land of Edom; these are the sons of Bashemath Esau’s wife.

18 የዔሳው ሚስት የአህሊባማ ልጆች እነዚህ ናቸው የዑስ አለቃ፥ የዕላማ አለቃ፥ ቆሬ አለቃ የዔሳው ሚስት የዓና ልጅ የአህሊባማ አለቆች እነዚህ ናቸው።

18 And these are the sons of Aholibamah Esau’s wife; duke Jeush, duke Jaalam, duke Korah: these were the dukes that came of Aholibamah the daughter of Anah, Esau’s wife.

19 የዔሳው ልጆችና አለቆቻቸው እነዚህ ናቸው እርሱም ኤዶም ነው።

19 These are the sons of Esau, who is Edom, and these are their dukes.

20 በዚያች አገር የተቀመጡ የሖሪው የሴይር ልጆች እነዚህ ናቸው ሎጣን፥ ሦባል፥ ፅብዖን፥ ዓና፥ ዲሶን፥ ኤጽር፥ ዲሳን

20 These are the sons of Seir the Horite, who inhabited the land; Lotan, and Shobal, and Zibeon, and Anah,

21 እነዚህ በኤዶም ምድር የሖሪው የሴይር ልጆች አለቆች ናቸው።

21 And Dishon, and Ezer, and Dishan: these are the dukes of the Horites, the children of Seir in the land of Edom.

22 የሎጣን ልጆችም ሖሪ፥ ሄማም ናቸው የሎጣንም እኅት ቲምናዕ ናት።

22 And the children of Lotan were Hori and Hemam; and Lotan’s sister was Timna.

23 የሦባል ልጆችም እነዚህ ናቸው ዓልዋን፥ ማኔሐት፥ ዔባል፥ ስፎ፥ አውናም።

23 And the children of Shobal were these; Alvan, and Manahath, and Ebal, Shepho, and Onam.

24 የፅብዖን ልጆችም እነዚህ ናቸው አያ፥ ዓና ይህም ዓና በምድረ በዳ የአባቱን የፅብዖንን አህዮች ሲጠብቅ ፍልውኆችን ያገኘ ነው።

24 And these are the children of Zibeon; both Ajah, and Anah: this was that Anah that found the mules in the wilderness, as he fed the asses of Zibeon his father.

25 የዓና ልጆችም እነዚህ ናቸው

25 And the children of Anah were these; Dishon, and Aholibamah the daughter of Anah.

26 ዲሶን፥ አህሊባማም የዓና ሴት ልጅ። የዲሶንም ልጆች እነዚህ ናቸው ሔምዳን፥ ኤስባን፥ ይትራን፥ ክራን።

26 And these are the children of Dishon; Hemdan, and Eshban, and Ithran, and Cheran.

27 የኤጽር ልጆችም እነዚህ ናቸው ቢልሐን፥ ዛዕዋን፥ ዓቃን።

27 The children of Ezer are these; Bilhan, and Zaavan, and Akan.

28 የዲሳን ልጆችም እነዚህ ናቸው ዑፅ፥ አራን።

28 The children of Dishan are these; Uz, and Aran.

29 የሖሪ አለቆች እነዚህ ናቸው ሎጣን አለቃ፥ ሦባል አለቃ፥ ፅብዖን አለቃ፥

29 These are the dukes that came of the Horites; duke Lotan, duke Shobal, duke Zibeon, duke Anah,

30 ዓና አለቃ፥ ዲሶን አለቃ፥ ኤጽር አለቃ፥ ዲሳን አለቃ በሴይር ምድር አለቆች የሆኑ የሖሪ አለቆቹ እነዚህ ናቸው።

30 Duke Dishon, duke Ezer, duke Dishan: these are the dukes that came of Hori, among their dukes in the land of Seir.

31 በእስራኤል ልጆች ላይ ንጉሥ ከመኖሩ በፊት በኤዶም አገር የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ናቸው።

31 And these are the kings that reigned in the land of Edom, before there reigned any king over the children of Israel.

32 በኤዶምም የቢዖር ልጅ ባላቅ ነገሠ የከተማውም ስም ዲንሃባ ናት።

32 And Bela the son of Beor reigned in Edom: and the name of his city was Dinhabah.

33 ባላቅም ሞተ፥ በስፍራውም የባሶራው የዛራ ልጅ ኢዮባብ ነገሠ።

33 And Bela died, and Jobab the son of Zerah of Bozrah reigned in his stead.

34 ኢዮባብም ሞተ፥ በስፍራውም የቴማኒው አገር ሑሳም ነገሠ።

34 And Jobab died, and Husham of the land of Temani reigned in his stead.

35 ሑሳምም ሞተ፥ በስፍራውም የምድያምን ሰዎች በሞዓብ ሜዳ የመታ የባዳድ ልጅ ሃዳድ ነገሠ የከተማውም ስም ዓዊት ተባለ።

35 And Husham died, and Hadad the son of Bedad, who smote Midian in the field of Moab, reigned in his stead: and the name of his city was Avith.

36 ሃዳድም ሞተ፥ በስፍራውም የመሥሬቃው ሠምላ ነገሠ።

36 And Hadad died, and Samlah of Masrekah reigned in his stead.

37 ሠምላም ሞተ፥ በስፍራውም በወንዝ አጠገብ ካለችው ከርሆቦት ሳኦል ነገሠ።

37 And Samlah died, and Saul of Rehoboth by the river reigned in his stead.

38 ሳኦልም ሞተ፥ በስፍራውም የዓክቦር ልጅ በኣልሐናን ነገሠ።

38 And Saul died, and Baal–hanan the son of Achbor reigned in his stead.

39 የዓክቦር ልጅ በኣልሐናንም ሞተ፥ በስፍራውም ሃዳር ነገሠ የከተማውም ስም ፋዑ ነው ሚስቱም የሜዛሃብ ልጅ መጥሬድ የወለደቻት መሄጣብኤል ትባላለች።

39 And Baal–hanan the son of Achbor died, and Hadar reigned in his stead: and the name of his city was Pau; and his wife’s name was Mehetabel, the daughter of Matred, the daughter of Mezahab.

40 የዔሳውም የአለቆቹ ስም በወገናቸው በስፍራቸው በስማቸውም ይህ ነው ቲምናዕ አለቃ፥ ዓልዋ አለቃ፥ የቴት አለቃ፥

40 And these are the names of the dukes that came of Esau, according to their families, after their places, by their names; duke Timnah, duke Alvah, duke Jetheth,

41 አህሊባማ አለቃ፥ ኤላ አለቃ፥ ፊኖን አለቃ፥

41 Duke Aholibamah, duke Elah, duke Pinon,

42 ቄኔዝ አለቃ፥ ቴማን አለቃ፥ ሚብሳር አለቃ፥

42 Duke Kenaz, duke Teman, duke Mibzar,

43 መግዲኤል አለቃ፥ ዒራም አለቃ፥ እነዚህ በግዛታቸው ምድር በየመኖሪያቸው የኤዶም አለቆች ናቸው። የኤዶማውያን አባት ይህ ዔሳው ነው።

43 Duke Magdiel, duke Iram: these be the dukes of Edom, according to their habitations in the land of their possession: he is Esau the father of the Edomites.