ኦሪት ዘኍልቍ Orit ZeHwilQwi
Numbers / Bamidbar #29
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

 

ኦሪት ዘኍልቍ 29

Numbers 29

1 በሰባተኛውም ወር ከወሩ በመጀመሪያ ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ የተግባርን ሥራ ሁሉ አትሥሩበት መለከቶች የሚነፉበት ቀን ነው።

1 And in the seventh month, on the first day of the month, ye shall have an holy convocation; ye shall do no servile work: it is a day of blowing the trumpets unto you.

2 ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ አንድ ወይፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ ነውር የሌለባቸውን ሰባት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች፥

2 And ye shall offer a burnt offering for a sweet savour unto the Lord; one young bullock, one ram, and seven lambs of the first year without blemish:

3 ለእህል ቍርባናቸው በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፥ ለወይፈኑ ከመስፈሪያው ከአሥር እጅ ሦስት እጅ፥ ለአውራው በግ ከመስፈሪያው ከአሥር እጅ ሁለት እጅ፥

3 And their meat offering shall be of flour mingled with oil, three tenth deals for a bullock, and two tenth deals for a ram,

4 ለሰባቱ ጠቦቶች ለእያንዳንዱ ከመስፈሪያው አሥረኛ እጅ ታቀርባላችሁ።

4 And one tenth deal for one lamb, throughout the seven lambs:

5 ማስተስረያም የሚሆንላችሁን አንድ አውራ ፍየል ለኃጢአት መሥዋዕት ታቀርባላችሁ።

5 And one kid of the goats for a sin offering, to make an atonement for you:

6 በወሩ መባቻ ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቍርባን፥ በዘወትርም ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቍርባን፥ ከመጠጡም ቍርባን ሌላ፥ እንደ ሕጋቸው ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርቡ ናቸው።

6 Beside the burnt offering of the month, and his meat offering, and the daily burnt offering, and his meat offering, and their drink offerings, according unto their manner, for a sweet savour, a sacrifice made by fire unto the Lord.

7 ከዚህም ከሰባተኛው ወር በአሥረኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ ሰውነታችሁን አስጨንቁት ከሥራ ሁሉ ምንም አታድርጉ።

7 And ye shall have on the tenth day of this seventh month an holy convocation; and ye shall afflict your souls: ye shall not do any work therein:

8 ለእግዚአብሔርም ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ አንድ ወይፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ ሰባት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ታቀርባላችሁ ነውር የሌለባቸው ይሁኑ።

8 But ye shall offer a burnt offering unto the Lord for a sweet savour; one young bullock, one ram, and seven lambs of the first year; they shall be unto you without blemish:

9 ለእህል ቍርባናቸውም በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፥ ለወይፈኑ ከመስፈሪያው ከአሥር እጅ ሦስት እጅ፥ ለአውራው በግ ከመስፈሪያው ከአሥር እጅ ሁለት እጅ፥

9 And their meat offering shall be of flour mingled with oil, three tenth deals to a bullock, and two tenth deals to one ram,

10 ለሰባቱ ጠቦቶች ለእያንዳንዱ ከመስፈሪያው አሥረኛ እጅ፥

10 A several tenth deal for one lamb, throughout the seven lambs:

11 ለኃጢአት መሥዋዕት አንድ አውራ ፍየል አቅርቡ። ከሚያስተሰርየው ከኃጢአት መሥዋዕት፥ በዘወትርም ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቍርባን፥ ከመጠጥ ቍርባናቸውም ሌላ አቅርቡት።

11 One kid of the goats for a sin offering; beside the sin offering of atonement, and the continual burnt offering, and the meat offering of it, and their drink offerings.

12 ከሰባተኛውም ወር በአሥራ አምስተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ የተግባርን ሥራ ሁሉ አትሥሩበት፥ ሰባት ቀንም ለእግዚአብሔር በዓል አድርጉ።

12 And on the fifteenth day of the seventh month ye shall have an holy convocation; ye shall do no servile work, and ye shall keep a feast unto the Lord seven days:

13 ለእግዚአብሔርም ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ አሥራ ሦስት ወይፈኖች፥ ሁለት አውራ በጎች፥ አሥራ አራት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ ነውር የሌለባቸውም ይሁኑ።

13 And ye shall offer a burnt offering, a sacrifice made by fire, of a sweet savour unto the Lord; thirteen young bullocks, two rams, and fourteen lambs of the first year; they shall be without blemish:

14 ለእህል ቍርባናቸውም በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፥ ለአሥራ ሦስት ወይፈኖች ለእያንዳንዱ ከመስፈሪያው ከአሥር እጅ ሦስት እጅ፥ ለሁለቱ አውራ በጎች ለእያንዳንዱ ከመስፈሪያው ከአሥር እጅ ሁለት እጅ፥

14 And their meat offering shall be of flour mingled with oil, three tenth deals unto every bullock of the thirteen bullocks, two tenth deals to each ram of the two rams,

15 ለአሥራ አራቱ ጠቦቶች ለእያንዳንዱ ከመስፈሪያው አሥረኛ እጅ፥

15 And a several tenth deal to each lamb of the fourteen lambs:

16 ለኃጢአትም መሥዋዕት አንድ አውራ ፍየል ታቀርባላችሁ በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቍርባን ከመጠጡም ቍርባን ሌላ የሚቀርቡ ናቸው።

16 And one kid of the goats for a sin offering; beside the continual burnt offering, his meat offering, and his drink offering.

17 በሁለተኛውም ቀን አሥራ ሁለት ወይፈኖችን፥ ሁለት አውራ በጎችን፥ ነውር የሌለባቸው አሥራ አራት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶችን፥

17 And on the second day ye shall offer twelve young bullocks, two rams, fourteen lambs of the first year without spot:

18 ለወይፈኖቹና ለአውራ በጎቹ ለጠቦቶቹም የእህል ቍርባናቸውንና የመጠጥ ቍርባናቸውን እንደ ቍጥራቸው መጠን እንደ ሕጉ፥

18 And their meat offering and their drink offerings for the bullocks, for the rams, and for the lambs, shall be according to their number, after the manner:

19 ለኃጢአትም መሥዋዕት አንድ አውራ ፍየልን ታቀርባላችሁ በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቍርባን ከመጠጡም ቍርባናቸው ሌላ የሚቀርቡ ናቸው።

19 And one kid of the goats for a sin offering; beside the continual burnt offering, and the meat offering thereof, and their drink offerings.

20 በሦስተኛውም ቀን አሥራ አንድ ወይፈኖች፥ ሁለት አውራ በጎች፥ ነውር የሌለባቸውን አሥራ አራት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች፥

20 And on the third day eleven bullocks, two rams, fourteen lambs of the first year without blemish;

21 ለወይፈኖቹና ለአውራ በጎቹ ለጠቦቶቹም የእህል ቍርባናቸውንና የመጠጥ ቍርባናቸውን እንደ ቍጥራቸው መጠን እንደ ሕጉ፥

21 And their meat offering and their drink offerings for the bullocks, for the rams, and for the lambs, shall be according to their number, after the manner:

22 ለኃጢአትም መሥዋዕት አንድ አውራ ፍየል፥ በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቍርባን ከመጠጡም ቍርባን ሌላ ታቀርባላችሁ።

22 And one goat for a sin offering; beside the continual burnt offering, and his meat offering, and his drink offering.

23 በአራተኛውም ቀን አሥር ወይፈኖች፥ ሁለት አውራ በጎች፥ ነውር የሌለባቸውን አሥራ አራት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች፥

23 And on the fourth day ten bullocks, two rams, and fourteen lambs of the first year without blemish:

24 ለወይፈኖቹና ለአውራ በጎቹ ለጠቦቶቹም የእህል ቍርባናቸውንና የመጠጥ ቍርባናቸውን እንደ ቍጥራቸውም መጠን እንደ ሕጉ፥

24 Their meat offering and their drink offerings for the bullocks, for the rams, and for the lambs, shall be according to their number, after the manner:

25 ለኃጢአትም መሥዋዕት አንድ አውራ ፍየል፥ በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቍርባን ከመጠጡም ቍርባን ሌላ ታቀርባላችሁ።

25 And one kid of the goats for a sin offering; beside the continual burnt offering, his meat offering, and his drink offering.

26 በአምስተኛውም ቀን ዘጠኝ ወይፈኖች፥ ሁለት አውራ በጎች፥ ነውር የሌለባቸውን አሥራ አራት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች፥

26 And on the fifth day nine bullocks, two rams, and fourteen lambs of the first year without spot:

27 ለወይፈኖቹና ለአውራ በጎቹ ለጠቦቶቹም የእህል ቍርባናቸውንና የመጠጥ ቍርባናቸውን እንደ ቍጥራቸው መጠን እንደ ሕጉ፥

27 And their meat offering and their drink offerings for the bullocks, for the rams, and for the lambs, shall be according to their number, after the manner:

28 ለኃጢአትም መሥዋዕት አንድ አውራ ፍየል፥ በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቍርባን ከመጠጡም ቍርባን ሌላ ታቀርባላችሁ።

28 And one goat for a sin offering; beside the continual burnt offering, and his meat offering, and his drink offering.

29 በስድስተኛውም ቀን ስምንት ወይፈኖች፥ ሁለት አውራ በጎች፥ ነውር የሌለባቸውን አሥራ አራት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች፥

29 And on the sixth day eight bullocks, two rams, and fourteen lambs of the first year without blemish:

30 ለወይፈኖቹና ለአውራ በጎቹ ለጠቦቶቹም የእህል ቍርባናቸውንና የመጠጥ ቍርባናቸውን እንደ ቍጥራቸው መጠን እንደ ሕጉ፥

30 And their meat offering and their drink offerings for the bullocks, for the rams, and for the lambs, shall be according to their number, after the manner:

31 ለኃጢአትም መሥዋዕት አንድ አውራ ፍየል፥ በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቍርባን ከመጠጡም ቍርባን ሌላ ታቀርባላችሁ።

31 And one goat for a sin offering; beside the continual burnt offering, his meat offering, and his drink offering.

32 በሰባተኛውም ቀን ሰባት ወይፈኖች፥ ሁለት አውራ በጎች፥ ነውር የሌለባቸውን አሥራ አራት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች፥

32 And on the seventh day seven bullocks, two rams, and fourteen lambs of the first year without blemish:

33 ለወይፈኖቹና ለአውራ በጎቹ ለጠቦቶቹም የእህል ቍርባናቸውንና የመጠጥ ቍርባናቸውን እንደ ቍጥራቸው መጠን እንደ ሕጉ፥

33 And their meat offering and their drink offerings for the bullocks, for the rams, and for the lambs, shall be according to their number, after the manner:

34 ለኃጢአትም መሥዋዕት አንድ አውራ ፍየል፥ በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቍርባን ከመጠጡም ቍርባን ሌላ ታቀርባላችሁ።

34 And one goat for a sin offering; beside the continual burnt offering, his meat offering, and his drink offering.

35 በስምንተኛውም ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ የተግባርን ሥራ ሁሉ አትሥሩበት።

35 On the eighth day ye shall have a solemn assembly: ye shall do no servile work therein:

36 ለእግዚአብሔርም ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ አንድ ወይፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ ነውር የሌለባቸውን ሰባት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ታቀርባላችሁ።

36 But ye shall offer a burnt offering, a sacrifice made by fire, of a sweet savour unto the Lord: one bullock, one ram, seven lambs of the first year without blemish:

37 የእህል ቍርባናቸውና የመጠጥ ቍርባናቸው ለወይፈኑ ለአውራውም በግ ለጠቦቶቹም እንደ ቍጥራቸው መጠን እንደ ሕጉ ይሆናሉ።

37 Their meat offering and their drink offerings for the bullock, for the ram, and for the lambs, shall be according to their number, after the manner:

38 ለኃጢአትም መሥዋዕት አንድ አውራ ፍየል ታቀርባላችሁ በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቍርባን ከመጠጡም ቍርባን ሌላ የሚቀርቡ ናቸው።

38 And one goat for a sin offering; beside the continual burnt offering, and his meat offering, and his drink offering.

39 እነዚህንም፥ ከስእለታችሁና በፈቃዳችሁ ከምታመጡት ሌላ፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ለእህልም ለመጠጥም ቍርባን፥ ለደኅንነትም መሥዋዕታችሁ በበዓላችሁ ጊዜ ለእግዚአብሔር አቅርቡ።

39 These things ye shall do unto the Lord in your set feasts, beside your vows, and your freewill offerings, for your burnt offerings, and for your meat offerings, and for your drink offerings, and for your peace offerings.

40 ሙሴም ለእስራኤል ልጆች እግዚአብሔር ሙሴን ያዘዘውን ሁሉ ነገራቸው።

40 And Moses told the children of Israel according to all that the Lord commanded Moses.