መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David #29
In Amharic and English
መዝሙረ ዳዊት 29 |
Psalm 29 |
1 የአምላክ ልጆች ሆይ፥ ለእግዚአብሔር አምጡ። ክብርንና ምስጋናን ለእግዚአብሔር አምጡ። |
1 Give unto the Lord, O ye mighty, give unto the Lord glory and strength. |
2 የስሙን ክብር ለእግዚአብሔር አምጡ፥ በቅድስናው ስፍራ ለእግዚአብሔር ስገዱ። |
2 Give unto the Lord the glory due unto his name; worship the Lord in the beauty of holiness. |
3 የእግዚአብሔር ድምፅ በውኆች ላይ፥ የክብር አምላክ አንጐደጐደ፥ እግዚአብሔር በብዙ ውኆች ላይ። |
3 The voice of the Lord is upon the waters: the God of glory thundereth: the Lord is upon many waters. |
4 የእግዚአብሔር ድምፅ በኃይል ነው የእግዚአብሔር ድምፅ በታላቅ ክብር ነው። |
4 The voice of the Lord is powerful; the voice of the Lord is full of majesty. |
5 የእግዚአብር ድምፅ ዝግባን ይሰብራል እግዚአብሔር የሊባኖስን ዝግባ ይቀጠቅጣል። |
5 The voice of the Lord breaketh the cedars; yea, the Lord breaketh the cedars of Lebanon. |
6 እንደ ጥጃ ሊባኖስን፥ አንድ ቀን እንዳለው አውሬ ልጅ ስርዮንን ያዘልላቸዋል። |
6 He maketh them also to skip like a calf; Lebanon and Sirion like a young unicorn. |
7 የእግዚአብሔር ድምፅ የእሳቱን ነበልባል ይቈርጣል። |
7 The voice of the Lord divideth the flames of fire. |
8 የእግዚአብሔር ድምፅ ምድረ በዳውን ያናውጣል፥ እግዚአብሔር የቃዴስን ምድረ በዳ ያናውጣል። |
8 The voice of the Lord shaketh the wilderness; the Lord shaketh the wilderness of Kadesh. |
9 የእግዚአብሔር ድምፅ ዋላዎችን ያጠነክራቸዋል፥ ጫካዎቹንም ይገልጣል ሁሉም በመቅደሱ። ምስጋና ይላል። |
9 The voice of the Lord maketh the hinds to calve, and discovereth the forests: and in his temple doth every one speak of his glory. |
10 እግዚአብሔር የጥፋት ውኃን ሰብስቦአል እግዚአብሔር ለዘላለም ንጉሥ ሆኖ ይቀመጣል። |
10 The Lord sitteth upon the flood; yea, the Lord sitteth King for ever. |
11 እግዚአብሔር ለሕዝቡ ኃይልን ይሰጣል እግዚአብሔር ሕዝቡን በሰላም ይባርካል። |
11 The Lord will give strength unto his people; the Lord will bless his people with peace. |