ኦሪት ዘጸአት Orit ZeTseAt
Exodus / Shemot #5
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

ኦሪት ዘጸአት 5

Exodus 5

1 ከዚህም በኋላ ሙሴና አሮን መጥተው ፈርዖንን እንዲህ አሉት። የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። በምድረ በዳ በዓል ያደርግልኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ።

1 And afterward Moses and Aaron went in, and told Pharaoh, Thus saith the Lord God of Israel, Let my people go, that they may hold a feast unto me in the wilderness.

2 ፈርዖንም። ቃሉን እሰማ ዘንድ እስራኤልንስ እለቅቅ ዘንድ እግዚአብሔር ማን ነው? እግዚአብሔርን አላውቅም፥ እስራኤልንም ደግሞ አልለቅቅም አለ።

2 And Pharaoh said, Who is the Lord, that I should obey his voice to let Israel go? I know not the Lord, neither will I let Israel go.

3 እርሱም፦ የዕብራውያን አምላክ ተገናኘን ቸነፈር ወይም ሰይፍ እንዳይጥልብን የሦስት ቀን መንገድ በምድረ በዳ እንድንሄድ፥ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር እንድንሠዋ እንለምንሃለን አሉት።

3 And they said, The God of the Hebrews hath met with us: let us go, we pray thee, three days’ journey into the desert, and sacrifice unto the Lord our God; lest he fall upon us with pestilence, or with the sword.

4 የግብፅ ንጉሥም። አንተ ሙሴ አንተም አሮን፥ ሕዝቡን ለምን ሥራቸውን ታስተዋላችሁ? ወደ ተግባራችሁ ሂዱ አላቸው።

4 And the king of Egypt said unto them, Wherefore do ye, Moses and Aaron, let the people from their works? get you unto your burdens.

5 ፈርዖንም። እነሆ የምድሩ ሕዝብ አሁን በዝቶአል፥ እናንተም ሥራቸውን ታስፈቱአቸዋላችሁ አለ።

5 And Pharaoh said, Behold, the people of the land now are many, and ye make them rest from their burdens.

6 ፈርዖንም በዚያን ቀን የሕዝቡን አስገባሪዎች ሹማምቶቹንም እንዲህ ሲል አዘዘ፦

6 And Pharaoh commanded the same day the taskmasters of the people, and their officers, saying,

7 እንደ ወትሮው ለጡብ ሥራ ደግሞ ገለባ ለሕዝቡ አትስጡ ነገር ግን እነርሱ ሄደው ገለባ ይሰብስቡ።

7 Ye shall no more give the people straw to make brick, as heretofore: let them go and gather straw for themselves.

8 ቀድሞ ያደርጉት የነበረውን የጡብ ቍጥር በእነርሱ ላይ አድርጉት ምንም ከእርሱ አታጕድሉ ሥራ ሰልችተዋልና ስለዚህ፦ ለአምላካችን እንድንሰዋ እንሂድ እያሉ ይጮኻሉ።

8 And the tale of the bricks, which they did make heretofore, ye shall lay upon them; ye shall not diminish ought thereof: for they be idle; therefore they cry, saying, Let us go and sacrifice to our God.

9 እርሱንም ያደርጉ ዘንድ በሰዎች ላይ ሥራው ይክበድባቸው ከንቱ ቃልም አያስቡ።

9 Let there more work be laid upon the men, that they may labour therein; and let them not regard vain words.

10 የሕዝቡም አስገባሪዎች ሹማምቶቹም ወጡ፥ ሕዝቡንም። ፈርዖን እንዲህ ይላል። ገለባ አልሰጣችሁም።

10 And the taskmasters of the people went out, and their officers, and they spake to the people, saying, Thus saith Pharaoh, I will not give you straw.

11 እናንተ ሂዱ፥ ከምታገኙበትም ስፍራ ገለባ ሰብስቡ ከሥራችሁ ግን ምንም አይጐድልም አሉአቸው።

11 Go ye, get you straw where ye can find it: yet not ought of your work shall be diminished.

12 ሕዝቡም ስለ ገለባ እብቅ ሊሰበስቡ በግብፅ ምድር ሁሉ ተበተኑ።

12 So the people were scattered abroad throughout all the land of Egypt to gather stubble instead of straw.

13 አስገባሪዎቹም። ገለባ ትቀበሉበት እንደ ነበረ ጊዜ የቀን ሥራችሁን ጨርሱ እያሉ አስቸኰሉአቸው።

13 And the taskmasters hasted them, saying, Fulfil your works, your daily tasks, as when there was straw.

14 የፈርዖንም አስገባሪዎች። ቀድሞ ታደርጉ እንደ ነበራችሁ ትናንትናና ዛሬ የተቈጠረውን ጡብ ስለ ምን አትጨርሱም? እያሉ በእስራኤል ልጆች ላይ የተሾሙትን አለቆቹን ገረፉ።

14 And the officers of the children of Israel, which Pharaoh’s taskmasters had set over them, were beaten, and demanded, Wherefore have ye not fulfilled your task in making brick both yesterday and to day, as heretofore?

15 የእስራኤል ልጆች አለቆችም ወደ ፈርዖን መጡ። ለምን በባሪያዎችህ እንዲህ ታደርጋለህ?

15 Then the officers of the children of Israel came and cried unto Pharaoh, saying, Wherefore dealest thou thus with thy servants?

16 ገለባ አይሰጡንም፥ የጡቡንም ሥራ እንድንሠራ ያዝዙናል እነሆም ባሪያዎችህን ይገርፉናል ግድፈቱ ግን በአንተ ሕዝብ ላይ ነው ብለው ጮኹ።

16 There is no straw given unto thy servants, and they say to us, Make brick: and, behold, thy servants are beaten; but the fault is in thine own people.

17 እርሱ ግን፦ ሰልችታችኋል፥ ሰልችታችኋል ስለዚህም። እንሂድ ለእግዚአብሔርም እንሠዋ ትላላችሁ።

17 But he said, Ye are idle, ye are idle: therefore ye say, Let us go and do sacrifice to the Lord.

18 አሁንም ሂዱ፥ ሥሩ ገለባ አይሰጡአችሁም፥ የጡቡን ቍጥር ግን ታመጣላችሁ አላቸው።

18 Go therefore now, and work; for there shall no straw be given you, yet shall ye deliver the tale of bricks.

19 የእስራኤልም ልጆች አለቆች። ዕለት ዕለት ከምትሰሩት ከጡቡ ቍጥር ምንም አታጕድሉ ባሉአቸው ጊዜ ነገሩ እንደ ከፋባቸው አዩ።

19 And the officers of the children of Israel did see that they were in evil case, after it was said, Ye shall not minish ought from your bricks of your daily task.

20 ከፈርዖንም ዘንድ ሲወጡ ሙሴንና አሮንን በፊታቸው ቆመው ተገናኙአቸው።

20 And they met Moses and Aaron, who stood in the way, as they came forth from Pharaoh:

21 እርሱም፦ በፈርዖንና በባሪያዎቹ ፊት ሽታችንን አግምታችሁታልና፥ ይገድሉንም ዘንድ ሰይፍን በእጃቸው ሰጥታችኋቸዋልና እግዚአብሔር ይመልከታችሁ ይፍረድባችሁም አሉአቸው።

21 And they said unto them, The Lord look upon you, and judge; because ye have made our savour to be abhorred in the eyes of Pharaoh, and in the eyes of his servants, to put a sword in their hand to slay us.

22 ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ተመለሰና። ጌታ ሆይ፥ ስለ ምን ይህን ሕዝብ አስከፋህ? ስለ ምንስ ላክኸኝ?

22 And Moses returned unto the Lord, and said, Lord, wherefore hast thou so evil entreated this people? why is it that thou hast sent me?

23 በስምህ እናገር ዘንድ ወደ ፈርዖን ከገባሁ ወዲህ፥ ይህን ሕዝብ አስከፍቶታልና አንተም ሕዝብህን ከቶ አላዳንኸውም አለ።

23 For since I came to Pharaoh to speak in thy name, he hath done evil to this people; neither hast thou delivered thy people at all.