ኦሪት ዘዳግም Orit ZeDaGim
Deuteronomy / Devarim #14
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

ኦሪት ዘዳግም 14

Deuteronomy 14

1-2 እናንተ የአምላካችሁ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ ለአምላክህ ለእግዚአብሔ አንተ ቅዱስ ሕዝብ ነህና፥ በምድርም ላይ ከሚኖሩ አሕዛብ ሁሉ ይልቅ ለእርሱ ለራሱ ሕዝብ ትሆንለት ዘንድ እግዚአብሔር አንተን መርጦአልና ስለ ሞተው ሰው አካላችሁን አትንጩ፥ በዓይኖቻችሁም መካከል ራሳችሁን አትላጩ።

1 Ye are the children of the Lord your God: ye shall not cut yourselves, nor make any baldness between your eyes for the dead.
2 For thou art an holy people unto the Lord thy God, and the Lord hath chosen thee to be a peculiar people unto himself, above all the nations that are upon the earth.

3-4 ርኩስን ነገር ሁሉ አትብላ። የምትበሉአቸው እንስሶች እነዚህ ናቸው በሬ፥

3 Thou shalt not eat any abominable thing.
4 These are the beasts which ye shall eat: the ox, the sheep, and the goat,

5 በግ፥ ፍየል፥ ዋላ፥ ሚዳቋ፥ የበረሃ ፍየል፥ አጋዘን፥ አጭ፥ በራይሌ፥ ድኵላ።

5 The hart, and the roebuck, and the fallow deer, and the wild goat, and the pygarg, and the wild ox, and the chamois.

6 ከእንስሶች ሰኮናው የተሰነጠቀውን፥ ጥፍሩም ከሁለት የተከፈለውን፥ የሚያመሰኳውንም እንስሳ ሁሉ ትበላለህ።

6 And every beast that parteth the hoof, and cleaveth the cleft into two claws, and cheweth the cud among the beasts, that ye shall eat.

7 ነገር ግን ከሚያመሰኩ ወይም ሰኮናቸው ከተሰነጠቀ እነዚህን አትበሉም ግመልን፥ ጥንቸልን፥ ሽኮኮን አትበሉም። ያመሰኳሉና፥ ነገር ግን ሰኮናቸው አልተሰነጠቀምና እነዚህ ለእናንተ ርኩሶች ናቸው።

7 Nevertheless these ye shall not eat of them that chew the cud, or of them that divide the cloven hoof; as the camel, and the hare, and the coney: for they chew the cud, but divide not the hoof; therefore they are unclean unto you.

8 እርያም፥ ሰኮናው ስለ ተሰነጠቀ ነገር ግን ስላላመሰኳ እርሱ ለእናንተ ርኩስ ነው ሥጋውን አትብሉ፥ በድኑንም አትንኩ።

8 And the swine, because it divideth the hoof, yet cheweth not the cud, it is unclean unto you: ye shall not eat of their flesh, nor touch their dead carcase.

9 በውኆች ውስጥ ከሚኖሩት ሁሉ የምትበሉአቸው እነዚህ ናቸው ክንፍና ቅርፊት ያላቸውን ትበላላችሁ።

9 These ye shall eat of all that are in the waters: all that have fins and scales shall ye eat:

10 ክንፍና ቅርፊትም የሌላቸውን አትበሉም ለእናንተ ርኩስ ናቸው።

10 And whatsoever hath not fins and scales ye may not eat; it is unclean unto you.

11 ንጹሕ የሆኑትን ወፎች ሁሉ ብሉ።

11 Of all clean birds ye shall eat.

12 ሊበሉ የማይገባቸው ግን እነዚህ ናቸው

12 But these are they of which ye shall not eat: the eagle, and the ossifrage, and the ospray,

13 ንስር፥ ገዴ፥ ዓሣ አውጭ፥ ጭልፊት፥ ጭላት በየወገኑ፥

13 And the glede, and the kite, and the vulture after his kind,

14-15 ቍራም ሁሉ በየወገኑ፥ ሰጎን፥

14 And every raven after his kind,
15 And the owl, and the night hawk, and the cuckow, and the hawk after his kind,

16 ጠላቋ፥ ዝዪ፥ በቋል በየወገኑ፥ ጕጕት፥

16 The little owl, and the great owl, and the swan,

17 ጋጋኖ፥ የውኃ ዶሮ፥ ይብራ፥ ጥምብ አንሣ አሞራ፥

17 And the pelican, and the gier eagle, and the cormorant,

18 እርኩም፥ ሽመላ፥ ሳቢሳ በየወገኑ፥ ጅንጅላቴ ወፍ፥ የሌሊት ወፍ።

18 And the stork, and the heron after her kind, and the lapwing, and the bat.

19 የሚበርርም ተንቀሳቃሽ ሁሉ ለእናንተ ርኩስ ነው አይበላም።

19 And every creeping thing that flieth is unclean unto you: they shall not be eaten.

20 ንጹሕ የሆኑትን ወፎች ሁሉ ብሉ።

20 But of all clean fowls ye may eat.

21 አንተ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ሕዝብ ነህና የበከተውን ሁሉ አትብላ ይበላው ዘንድ በአገርህ ደጅ ለተቀመጠ መጻተኛ ትሰጠዋለህ፥ ወይም ለእንግዳ ትሸጠዋለህ። የፍየሉን ጠቦት በእናቱ ወተት አትቀቅል።

21 Ye shall not eat of any thing that dieth of itself: thou shalt give it unto the stranger that is in thy gates, that he may eat it; or thou mayest sell it unto an alien: for thou art an holy people unto the Lord thy God. Thou shalt not seethe a kid in his mother’s milk.

22 ከእርሻህ በየዓመቱ ከምታገኘው ከዘርህ ፍሬ ሁሉ አሥራት ታወጣለህ።

22 Thou shalt truly tithe all the increase of thy seed, that the field bringeth forth year by year.

23 ሁልጊዜ አምላክህን እግዚአብሔርን መፍራት ትማር ዘንድ፥ ስሙ እንዲጠራበት በመረጠው ስፍራ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት የእህልህን የወይን ጠጅህንም የዘይትህንም አሥራት የላምህንና የበግህንም በኵራት ብላ።

23 And thou shalt eat before the Lord thy God, in the place which he shall choose to place his name there, the tithe of thy corn, of thy wine, and of thine oil, and the firstlings of thy herds and of thy flocks; that thou mayest learn to fear the Lord thy God always.

24 አምላክህ እግዚአብሔር በባረከህ ጊዜ፥ መንገዱ ሩቅ ቢሆን፥ አምላክህም እግዚአብሔር ስሙን ያኖርበት ዘንድ የመረጠው ስፍራ ቢርቅብህ፥ ይህን ወደዚያ ለመሸከም ባትችል፥ ትሸጠዋለህ፥

24 And if the way be too long for thee, so that thou art not able to carry it; or if the place be too far from thee, which the Lord thy God shall choose to set his name there, when the Lord thy God hath blessed thee:

25 የዋጋውንም ገንዘብ በእጅህ ይዘህ አምላክህ እግዚአብሔር ወደ መረጠው ስፍራ ትሄዳለህ።

25 Then shalt thou turn it into money, and bind up the money in thine hand, and shalt go unto the place which the Lord thy God shall choose:

26 በዚያም በገንዘቡ ሰውነትህ የፈለገውን፥ በሬ ወይም በግ ወይም የወይን ጠጅ ወይም ብርቱ መጠጥ ሰውነትህም የሚሻውን ሁሉ ትገዛለህ በዚያም በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ትበላዋለህ፥ አንተና ቤተ ሰብህም ደስ ይላችኋል።

26 And thou shalt bestow that money for whatsoever thy soul lusteth after, for oxen, or for sheep, or for wine, or for strong drink, or for whatsoever thy soul desireth: and thou shalt eat there before the Lord thy God, and thou shalt rejoice, thou, and thine household,

27 ድርሻና ርስት ከአንተ ጋር ስለሌለው በአገርህ ደጅ ውስጥ ያለውን ሌዋዊ ቸል አትበል።

27 And the Levite that is within thy gates; thou shalt not forsake him; for he hath no part nor inheritance with thee.

28 በየሦስተኛው ዓመት መጨረሻ በዚያ ዓመት የፍሬህን አሥራት ሁሉ አምጥተህ በአገርህ ደጅ ውስጥ ታኖረዋለህ

28 At the end of three years thou shalt bring forth all the tithe of thine increase the same year, and shalt lay it up within thy gates:

29 ሌዋዊውም፥ ከአንተ ጋር ክፍልና ርስት የለውምና፥ በአገርህም ደጅ ያለ መጻተኛ ድሀ አደግም መበለትም መጥተው ይበላሉ ይጠግባሉም ይኸውም አምላክህ እግዚአብሔር በምታደርገው በእጅህ ሥራ ሁሉ ይባርክህ ዘንድ ነው።

29 And the Levite, (because he hath no part nor inheritance with thee,) and the stranger, and the fatherless, and the widow, which are within thy gates, shall come, and shall eat and be satisfied; that the Lord thy God may bless thee in all the work of thine hand which thou doest.