ኦሪት ዘኍልቍ Orit ZeHwilQwi
Numbers / Bamidbar #21
In Amharic and English
|
ኦሪት ዘኍልቍ 21 |
Numbers 21 |
1 በደቡብም በኩል ተቀምጦ የነበረው ከነዓናዊው የዓራድ ንጉሥ በአታሪም መንገድ እስራኤል እንደ መጡ ሰማ ከእስራኤልም ጋር ሰልፍ አደረገ ከእነርሱም ምርኮ ማረከ። |
1 And when king Arad the Canaanite, which dwelt in the south, heard tell that Israel came by the way of the spies; then he fought against Israel, and took some of them prisoners. |
2 እስራኤልም ለእግዚአብሔር፦ እነዚህን አሳልፈህ በእጄ ብትሰጣቸው ከተሞቻቸውን እርም ብዬ አጠፋለሁ ብሎ ስእለት ተሳለ። |
2 And Israel vowed a vow unto the Lord, and said, If thou wilt indeed deliver this people into my hand, then I will utterly destroy their cities. |
3 እግዚአብሔርም የእስራኤልን ድምፅ ሰማ፥ ከነዓናውያንንም አሳልፎ ሰጣቸው እነርሱንም ከተሞቻቸውንም እርም ብለው አጠፉ የዚያንም ስፍራ ስም ሔርማ ብለው ጠሩት። |
3 And the Lord hearkened to the voice of Israel, and delivered up the Canaanites; and they utterly destroyed them and their cities: and he called the name of the place Hormah. |
4 ከሖርም ተራራ ከኤዶምያስ ምድር ርቀው ሊዞሩ በኤርትራ ባሕር መንገድ ተጓዙ የሕዝቡም ሰውነት ከመንገዱ የተነሣ ደከመ። |
4 And they journeyed from mount Hor by the way of the Red sea, to compass the land of Edom: and the soul of the people was much discouraged because of the way. |
5 ሕዝቡም በእግዚአብሔርና በሙሴ ላይ። በምድረ በዳ እንሞት ዘንድ ከግብፅ ለምን አወጣችሁን? እንጀራ የለም፥ ውኃ የለም ሰውነታችንም ይህን ቀላል እንጀራ ተጸየፈ ብለው ተናገሩ። |
5 And the people spake against God, and against Moses, Wherefore have ye brought us up out of Egypt to die in the wilderness? for there is no bread, neither is there any water; and our soul loatheth this light bread. |
6 እግዚአብሔርም በሕዝቡ ላይ እባቦችን ሰደደ፥ ሕዝቡንም ነደፉ ከእስራኤልም ብዙ ሰዎች ሞቱ። |
6 And the Lord sent fiery serpents among the people, and they bit the people; and much people of Israel died. |
7 ሕዝቡም ወደ ሙሴ መጥተው። በእግዚአብሔርና በአንተ ላይ ስለ ተናገርን በድለናል እባቦችን ከእኛ ያርቅልን ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸልይልን አሉት። |
7 Therefore the people came to Moses, and said, We have sinned, for we have spoken against the Lord, and against thee; pray unto the Lord, that he take away the serpents from us. And Moses prayed for the people. |
8 ሙሴም ስለ ሕዝቡ ጸለየ። እግዚአብሔርም ሙሴን፦ እባብን ሠርተህ በዓላማ ላይ ስቀል የተነደፈውም ሁሉ ሲያያት በሕይወት ይኖራል አለው። |
8 And the Lord said unto Moses, Make thee a fiery serpent, and set it upon a pole: and it shall come to pass, that every one that is bitten, when he looketh upon it, shall live. |
9 ሙሴም የናሱን እባብ ሠርቶ በዓላማ ላይ ሰቀለ እባብም የነደፈችው ሰው ሁሉ የናሱን እባብ ባየ ጊዜ ዳነ። |
9 And Moses made a serpent of brass, and put it upon a pole, and it came to pass, that if a serpent had bitten any man, when he beheld the serpent of brass, he lived. |
10 የእስራኤልም ልጆች ተጓዙ፥ በኦቦትም ሰፈሩ። |
10 And the children of Israel set forward, and pitched in Oboth. |
11 ከኦቦትም ተጕዘው በሞዓብ ፊት ለፊት ባለችው ምድረ በዳ፥ በፀሐይ መውጫ በኩል፥ በዒዬዓባሪም ሰፈሩ። |
11 And they journeyed from Oboth, and pitched at Ije–abarim, in the wilderness which is before Moab, toward the sunrising. |
12 ከዚያም ተጕዘው በዘሬድ ሸለቆ ሰፈሩ። |
12 From thence they removed, and pitched in the valley of Zared. |
13 ከዚያም ተጕዘው ከአሞራውያን ዳርቻ በሚወጣው ምድረ በዳ ውስጥ በአሮኖን ማዶ ሰፈሩ አሮኖን በሞዓብና በአሞራውያን መካከል ያለ የሞዓብ ዳርቻ ነውና። |
13 From thence they removed, and pitched on the other side of Arnon, which is in the wilderness that cometh out of the coasts of the Amorites: for Arnon is the border of Moab, between Moab and the Amorites. |
14 ስለዚህ በእግዚአብሔር የጦርነት መጽሐፍ እንዲህ ተባለ። ዋሄብ በሱፋ፥ የአርኖንም ሸለቆች፥ |
14 Wherefore it is said in the book of the wars of the Lord, What he did in the Red sea, and in the brooks of Arnon, |
15 ወደ ዔር ማደሪያ የሚወርድ በሞዓብም ዳርቻ የሚጠጋ የሸለቆች ፈሳሽ። |
15 And at the stream of the brooks that goeth down to the dwelling of Ar, and lieth upon the border of Moab. |
16 ከዚያም ወደ ብኤር ተጓዙ ይኸውም እግዚአብሔር ሙሴን፦ ሕዝቡን ሰብስብ ውኃንም እሰጣቸዋለሁ ብሎ የተናገረለት ጕድጓድ ነው። |
16 And from thence they went to Beer: that is the well whereof the Lord spake unto Moses, Gather the people together, and I will give them water. |
17 በዚያም ጊዜ እስራኤል ይህን መዝሙር ዘመረ። አንተ ምንጭ ሆይ፥ ፍለቅ፤ እናንተ ዘምሩለት፤ |
17 Then Israel sang this song, Spring up, O well; sing ye unto it: |
18 በበትረ መንግሥት በበትራቸውም የሕዝብ አዛውንቶች ያጐደጐዱት፥ አለቆችም የቈፈሩት ጕድጓድ። |
18 The princes digged the well, the nobles of the people digged it, by the direction of the lawgiver, with their staves. And from the wilderness they went to Mattanah: |
19 ከምድረ በዳም ወደ መቴና ተጓዙ ከመቴናም ወደ ነሃሊኤል፥ ከነሃሊኤልም ወደ ባሞት፥ |
19 And from Mattanah to Nahaliel: and from Nahaliel to Bamoth: |
20 ከባሞትም ምድረ በዳውን ከላይ ወደሚመለከተው ወደ ፈስጋ ተራራ ራስ በሞዓብ በረሀ ወዳለው ሸለቆ ተጓዙ። |
20 And from Bamoth in the valley, that is in the country of Moab, to the top of Pisgah, which looketh toward Jeshimon. |
21-22 እስራኤልም። በምድርህ ላይ እንለፍ ወደ እርሻና ወደ ወይን ቦታ አንገባም ከጕድጓድም ውኃን አንጠጣም ከምድርህ ዳርቻ እስክንወጣ ድረስ በንጉሥ ጐዳና እንሄዳለን ብለው ወደ አሞራውያን ንጉሥ ወደ ሴዎን መልእክተኞችን ላኩ። |
21 And Israel sent messengers unto Sihon king of the Amorites, saying, |
23 ሴዎንም እስራኤል በምድሩ ላይ ያልፍ ዘንድ እንቢ አለ ሴዎንም ሕዝቡን ሁሉ ሰበሰበ፥ እስራኤልንም ለመውጋት ወደ ምድረ በዳ ወጣ፥ ወደ ያሀጽም መጣ፥ ከእስራኤልም ጋር ተዋጋ። |
23 And Sihon would not suffer Israel to pass through his border: but Sihon gathered all his people together, and went out against Israel into the wilderness: and he came to Jahaz, and fought against Israel. |
24 እስራኤልም በሰይፍ መታው፥ ምድሩንም ከአርኖን ጀምሮ እስከ አሞን ልጆች እስከ ያቦቅ ድረስ ወረሰ የአሞንም ልጆች ዳርቻ የጸና ነበረ። |
24 And Israel smote him with the edge of the sword, and possessed his land from Arnon unto Jabbok, even unto the children of Ammon: for the border of the children of Ammon was strong. |
25 እስራኤልም እነዚህን ከተሞች ሁሉ ወሰደ እስራኤልም በአሞራውያን ከተሞች ሁሉ በሐሴቦንና በመንደሮቹ ሁሉ ተቀመጠ። |
25 And Israel took all these cities: and Israel dwelt in all the cities of the Amorites, in Heshbon, and in all the villages thereof. |
26 ሐሴቦንም የአሞራውያን ንጉሥ የሴዎን ከተማ ነበረ እርሱም የፊተኛውን የሞዓብን ንጉሥ ወግቶ እስከ አርኖን ድረስ ምድሩን ሁሉ ከእጁ ወስዶ ነበር። |
26 For Heshbon was the city of Sihon the king of the Amorites, who had fought against the former king of Moab, and taken all his land out of his hand, even unto Arnon. |
27 ስለዚህ በምሳሌ እንዲህ ተብሎ ተነገረ። ወደ ሐሴቦን ኑ፤ የሴዎን ከተማ ይሠራ፥ ይመሥረት፤ |
27 Wherefore they that speak in proverbs say, Come into Heshbon, let the city of Sihon be built and prepared: |
28 እሳት ከሐሴቦን፥ ነበልባልም ከሴዎን ከተማ ወጣ የሞዓብን ዔር፥ የአርኖንን ተራራ አለቆች በላ፤ |
28 For there is a fire gone out of Heshbon, a flame from the city of Sihon: it hath consumed Ar of Moab, and the lords of the high places of Arnon. |
29 ሞዓብ ሆይ፥ ወዮልህ! የከሞስ ሕዝብ ሆይ፥ ጠፋህ፤ ወንዶች ልጆቹን ለሽሽት፥ ሴቶች ልጆቹንም ለምርኮ፥ ለአሞራውያን ንጉሥ ለሴዎን ሰጠ። |
29 Woe to thee, Moab! thou art undone, O people of Chemosh: he hath given his sons that escaped, and his daughters, into captivity unto Sihon king of the Amorites. |
30 ገተርናቸው ከሐሴቦን እስከ ዴቦን ድረስ ጠፉ ኖፋም እስኪደርሱ እስከ ሜድባ አፈረስናቸው። |
30 We have shot at them; Heshbon is perished even unto Dibon, and we have laid them waste even unto Nophah, which reacheth unto Medeba. |
31 እስራኤልም እንደዚህ በአሞራውያን ምድር ተቀመጡ። |
31 Thus Israel dwelt in the land of the Amorites. |
32 ሙሴም ሰላዮችን ወደ ኢያዜር ሰደደ መንደሮችዋንም ወሰዱ፥ በዚያም የነበሩትን አሞራውያን አባረሩ። |
32 And Moses sent to spy out Jaazer, and they took the villages thereof, and drove out the Amorites that were there. |
33 ተመልሰውም በበሳን መንገድ ወጡ የባሳንም ንጉሥ ዐግ ከሕዝቡ ሁሉ ጋር በኤድራይ ይወጋቸው ዘንድ ወጣ። |
33 And they turned and went up by the way of Bashan: and Og the king of Bashan went out against them, he, and all his people, to the battle at Edrei. |
34 እግዚአብሔርም ሙሴን፦ እርሱንና ሕዝቡን ሁሉ ምድሪቱንም አሳልፌ በእጅህ ሰጥቼአለሁና አትፍራው በሐሴቦንም በተቀመጠው በአሞራውያን ንጉሥ በሴዎን እንዳደረግህ እንዲሁ ታደርግበታለህ አለው። |
34 And the Lord said unto Moses, Fear him not: for I have delivered him into thy hand, and all his people, and his land; and thou shalt do to him as thou didst unto Sihon king of the Amorites, which dwelt at Heshbon. |
35 እርሱንና ልጆቹን ሕዝቡንም ሁሉ መቱ ሰውም አልቀረለትም ምድሩንም ወረሱ። |
35 So they smote him, and his sons, and all his people, until there was none left him alive: and they possessed his land. |