ኦሪት ዘኍልቍ Orit ZeHwilQwi
Numbers / Bamidbar #32
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

 

ኦሪት ዘኍልቍ 32

Numbers 32

1 የሮቤልና የጋድ ልጆችም እጅግ ብዙ እንስሶች ነበሩአቸው እነሆም፥ የኢያዜር ምድርና የገለዓድ ምድር ለእንስሶች የተመቸ ስፍራ እንደ ነበረ ባዩ ጊዜ፥

1 Now the children of Reuben and the children of Gad had a very great multitude of cattle: and when they saw the land of Jazer, and the land of Gilead, that, behold, the place was a place for cattle;

2 የጋድና የሮቤል ልጆች መጥተው ሙሴንና ካህኑን አልዓዛርን የማኅበሩንም አለቆች እንዲህ ብለው ተናገሩአቸው።

2 The children of Gad and the children of Reuben came and spake unto Moses, and to Eleazar the priest, and unto the princes of the congregation, saying,

3-4 እግዚአብሔር በእስራኤል ማኅበር ፊት የመታው ምድር፥ አጣሮት፥ ዲቦን፥ ኢያዜር፥ ነምራ፥ ሐሴቦን፥ ኤልያሊ፥ ሴባማ፥ ናባው፥ ባያን፥ ለእንስሶች የተመቸ ምድር ነው ለእኛም ለባሪያዎችህ እንስሶች አሉን።

3 Ataroth, and Dibon, and Jazer, and Nimrah, and Heshbon, and Elealeh, and Shebam, and Nebo, and Beon,
4 Even the country which the Lord smote before the congregation of Israel, is a land for cattle, and thy servants have cattle:

5 እኛስ በአንተ ዘንድ ሞገስን አግኝተን እንደ ሆነ ይህን ምድር ለባሪያዎችህ ርስት አድርገህ ስጠን ወደ ዮርዳኖስም ማዶ አታሻግረን።

5 Wherefore, said they, if we have found grace in thy sight, let this land be given unto thy servants for a possession, and bring us not over Jordan.

6 ሙሴም ለጋድና ለሮቤል ልጆች አላቸው። ወንድሞቻችሁ ወደ ጦርነት ሲሄዱ እናንተ በዚህ ትቀመጣላችሁን?

6 And Moses said unto the children of Gad and to the children of Reuben, Shall your brethren go to war, and shall ye sit here?

7 እግዚአብሔር ወደሚሰጣቸው ምድር እንዳይሻገሩ የእስራኤልን ልጆች ልብ ለምን ታደክማላችሁ?

7 And wherefore discourage ye the heart of the children of Israel from going over into the land which the Lord hath given them?

8 ምድሪቱን ይሰልሉ ዘንድ ከቃዴስ በርኔ በሰደድኋቸው ጊዜ አባቶቻችሁ እንዲህ አደረጉ።

8 Thus did your fathers, when I sent them from Kadesh–barnea to see the land.

9 ወደ ኤሽኮልም ሸለቆ በሄዱ ጊዜ፥ ምድሪቱንም ባዩ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ወደ ሰጣቸው ምድር እንዳይገቡ የእስራኤልን ልጆች ልብ አደከሙ።

9 For when they went up unto the valley of Eshcol, and saw the land, they discouraged the heart of the children of Israel, that they should not go into the land which the Lord had given them.

10 በዚያም ቀን የእግዚአብሔር ቍጣ ነደደ፥

10 And the Lord’s anger was kindled the same time, and he sware, saying,

11-12 እርሱም፦ በእውነት እግዚአብሔርን ፈጽመው ከተከተሉ ከእነዚህ ከቄኔዛዊው ከዮፎኔ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር፥ ከግብፅ የወጡት ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያሉት ሰዎች እኔን ፈጽመው አልተከተሉምና ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም እሰጥ ዘንድ የማልሁበትን ምድር አያዩም ብሎ ማለ።

11 Surely none of the men that came up out of Egypt, from twenty years old and upward, shall see the land which I sware unto Abraham, unto Isaac, and unto Jacob; because they have not wholly followed me:
12 Save Caleb the son of Jephunneh the Kenezite, and Joshua the son of Nun: for they have wholly followed the Lord.

13 የእግዚአብሔርም ቍጣ በእስራኤል ላይ ጸና፥ በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ ያደረገ ትውልድ ሁሉ እስኪጠፋ ድረስ አርባ ዓመት በምድረ በዳ ውስጥ አቅበዘበዛቸው።

13 And the Lord’s anger was kindled against Israel, and he made them wander in the wilderness forty years, until all the generation, that had done evil in the sight of the Lord, was consumed.

14 እነሆም፥ የእግዚአብሔርን መዓት በእስራኤል ላይ አብዝታችሁ ትጨምሩ ዘንድ እናንተ የኃጢአተኞች ትውልድ በአባቶቻችሁ ፋንታ ቆማችኋል።

14 And, behold, ye are risen up in your fathers’ stead, an increase of sinful men, to augment yet the fierce anger of the Lord toward Israel.

15 እርሱን ከመከተል ብትመለሱ እርሱ ሕዝቡን በምድረ በዳ ደግሞ ይተዋል ይህንንም ሕዝብ ሁሉ ታጠፋላችሁ።

15 For if ye turn away from after him, he will yet again leave them in the wilderness; and ye shall destroy all this people.

16 ወደ እርሱም ቀርበው አሉት። በዚህ ለእንስሶቻችን በረቶች ለልጆቻችንም ከተሞች እንሠራለን

16 And they came near unto him, and said, We will build sheepfolds here for our cattle, and cities for our little ones:

17 እኛ ግን ለጦርነት ተዘጋጅተን ወደ ስፍራቸው እስክናገባቸው ድረስ በእስራኤል ልጆች ፊት እንሄዳለን በዚህም ምድር ስላሉ ሰዎች ልጆቻችን በተመሸጉ ከተሞች ይቀመጣሉ።

17 But we ourselves will go ready armed before the children of Israel, until we have brought them unto their place: and our little ones shall dwell in the fenced cities because of the inhabitants of the land.

18 የእስራኤል ልጆች ሁሉ ርስታቸውን እስኪወርሱ ድረስ ወደ ቤቶቻችን አንመለስም

18 We will not return unto our houses, until the children of Israel have inherited every man his inheritance.

19 ከዮርዳኖስ ወዲህ ወደ ምሥራቅ ርስታችን ደርሶናልና እኛ ከዮርዳኖስ ማዶ ወደዚያ ከእነርሱ ጋር ርስት አንወርስም።

19 For we will not inherit with them on yonder side Jordan, or forward; because our inheritance is fallen to us on this side Jordan eastward.

20 ሙሴም አላቸው። ይህንስ ነገር ብታደርጉ፥ ተዘጋጅታችሁም በእግዚአብሔር ፊት ወደ ሰልፍ ብትሄዱ፥

20 And Moses said unto them, If ye will do this thing, if ye will go armed before the Lord to war,

21 እርሱም ጠላቶቹን ከፊቱ እስኪያሳድድ ድረስ ምድሪቱም በእግዚአብሔር ፊት ድል እስክትሆን ድረስ ከእናንተ ሰው ሁሉ ጋሻ ጦሩን ይዞ በእግዚአብሔር ፊት ዮርዳኖስን ቢሻገር፥

21 And will go all of you armed over Jordan before the Lord, until he hath driven out his enemies from before him,

22 ከዚያ በኋላ ትመለሳላችሁ፥ በእግዚአብሔርም ፊት በእስራኤል ዘንድ ንጹሐን ትሆናላችሁ ይህች ምድርም በእግዚአብሔር ፊት ርስት ትሆንላችኋለች።

22 And the land be subdued before the Lord: then afterward ye shall return, and be guiltless before the Lord, and before Israel; and this land shall be your possession before the Lord.

23 እናንተ ግን እንዲህ ባታደርጉ፥ እነሆ፥ እግዚአብሔርን ትበድላላችሁ ኃጢአታችሁም እንዲያገኛችሁ እወቁ።

23 But if ye will not do so, behold, ye have sinned against the Lord: and be sure your sin will find you out.

24 ለልጆቻችሁ ከተሞች፥ ለበጎቻችሁም በረቶች ሥሩ ከአፋችሁም የወጣውን ነገር አድርጉ።

24 Build you cities for your little ones, and folds for your sheep; and do that which hath proceeded out of your mouth.

25 የጋድና የሮቤልም ልጆች ሙሴን እንዲህ ብለው ተናገሩት። እኛ ባሪያዎችህ ጌታችን እንዳዘዘ እናደርጋለን።

25 And the children of Gad and the children of Reuben spake unto Moses, saying, Thy servants will do as my lord commandeth.

26 ልጆቻችን፥ ሚስቶቻችንም፥ መንጎቻችንም፥ እንስሶቻችንም ሁሉ በዚያ በገለዓድ ከተሞች ይሆናሉ

26 Our little ones, our wives, our flocks, and all our cattle, shall be there in the cities of Gilead:

27 እኛ ባሪያዎችህ ግን ሁላችን ጋሻ ጦራችንን ይዘን በእግዚአብሔር ፊት ጌታችን እንደ ተናገረ ወደ ጦርነት እንሄዳለን።

27 But thy servants will pass over, every man armed for war, before the Lord to battle, as my lord saith.

28 ሙሴም ካህኑን አልዓዛርን የነዌንም ልጅ ኢያሱን የእስራኤልንም ልጆች ነገድ አለቆች ስለ እነርሱ አዘዘ።

28 So concerning them Moses commanded Eleazar the priest, and Joshua the son of Nun, and the chief fathers of the tribes of the children of Israel:

29 ሙሴም፦ የጋድና የሮቤል ልጆች ሁላቸው ጋሻ ጦራቸውን ይዘው ከእናንተ ጋር በእግዚአብሔር ፊት ዮርዳኖስን ቢሻገሩ፥ ምድሪቱንም ድል ብትነሡ፥ የገለዓድን ምድር ርስት አድርጋችሁ ትሰጡአቸዋላችሁ።

29 And Moses said unto them, If the children of Gad and the children of Reuben will pass with you over Jordan, every man armed to battle, before the Lord, and the land shall be subdued before you; then ye shall give them the land of Gilead for a possession:

30 ጋሻ ጦራቸውን ይዘው ከእናንተ ጋር ባይሻገሩ ግን በከነዓን ምድር በእናንተ መካከል ርስታቸውን ይወርሳሉ አላቸው።

30 But if they will not pass over with you armed, they shall have possessions among you in the land of Canaan.

31 የጋድና የሮቤልም ልጆች መልሰው። እግዚአብሔር ለእኛ ለባሪያዎችህ እንደ ተናገረ እንዲሁ እናደርጋለን።

31 And the children of Gad and the children of Reuben answered, saying, As the Lord hath said unto thy servants, so will we do.

32 ጋሻ ጦራችንን ይዘን በእግዚአብሔር ፊት ወደ ከነዓን ምድር እንሻገራለን፥ ከዮርዳኖስም ማዶ ከወዲሁ የወረስነው ርስት ይሆንልናል አሉት።

32 We will pass over armed before the Lord into the land of Canaan, that the possession of our inheritance on this side Jordan may be ours.

33 ሙሴም ለጋድና ለሮቤል ልጆች ለዮሴፍም ልጅ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ፥ የአሞራውያንን ንጉሥ የሴዎንን ግዛት የባሳንንም ንጉሥ የዐግን ግዛት፥ ምድሪቱንና በዙሪያዋ ያሉትን ከተሞች ሰጣቸው።

33 And Moses gave unto them, even to the children of Gad, and to the children of Reuben, and unto half the tribe of Manasseh the son of Joseph, the kingdom of Sihon king of the Amorites, and the kingdom of Og king of Bashan, the land, with the cities thereof in the coasts, even the cities of the country round about.

34 የጋድም ልጆች ዲቦንን፥ አጣሮትን፥ አሮዔርን፥

34 And the children of Gad built Dibon, and Ataroth, and Aroer,

35 ዓጥሮትሽፋንን፥ ኢያዜርን፥ ዮግብሃን፥

35 And Atroth, Shophan, and Jaazer, and Jogbehah,

36 ቤትነምራን፥ ቤትሃራንን የተመሸጉ ከተሞች አድርገው ሠሩ የበጎች በረቶችንም ሠሩ።

36 And Beth–nimrah, and Beth–haran, fenced cities: and folds for sheep.

37 የሮቤልም ልጆች ሐሴቦንን፥ ኤልያሊን፥

37 And the children of Reuben built Heshbon, and Elealeh, and Kirjathaim,

38 ቂርያታይምን፥ ስማቸውም የተለወጠውን ናባውን፥ በኣልሜዎንን፥ ሴባማን ሠሩ እነዚህንም የሠሩአቸውን ከተሞች በሌላ ስም ጠሩአቸው።

38 And Nebo, and Baal–meon, (their names being changed,) and Shibmah: and gave other names unto the cities which they builded.

39 የምናሴም ልጅ የማኪር ልጆች ወደ ገለዓድ ሄዱ፥ ወሰዱአትም፥ በእርስዋም የነበሩትን አሞራውያንን አሳደዱ።

39 And the children of Machir the son of Manasseh went to Gilead, and took it, and dispossessed the Amorite which was in it.

40 ሙሴም ለምናሴ ልጅ ለማኪር ገለዓድን ሰጠ በእርስዋም ተቀመጠ።

40 And Moses gave Gilead unto Machir the son of Manasseh; and he dwelt therein.

41 የምናሴም ልጅ ኢያዕር ሄዶ መንደሮችዋን ወሰደ፥ የኢያዕርም መንደሮች ብሎ ጠራቸው።

41 And Jair the son of Manasseh went and took the small towns thereof, and called them Havoth–jair.

42 ኖባህም ሄደ ቄናትንም መንደሮችዋንም ወሰደ፥ በስሙም ኖባህ ብሎ ጠራቸው።

42 And Nobah went and took Kenath, and the villages thereof, and called it Nobah, after his own name.