ኦሪት ዘሌዋውያን Orit ZeLaeWaWiYan
Leviticus / Vayikra #8
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

 

ኦሪት ዘሌዋውያን 8

Leviticus 8

1 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው።

1 And the Lord spake unto Moses, saying,

2 አሮንን፥ ከእርሱም ጋር ልጆቹን፥ ልብሱንም፥ የቅብዓቱንም ዘይት፥ ለኃጢአት መሥዋዕትም የሆነውን ወይፈን፥ ሁለቱንም አውራ በጎች፥ የቂጣውንም እንጀራ ሌማት ውሰድ

2 Take Aaron and his sons with him, and the garments, and the anointing oil, and a bullock for the sin offering, and two rams, and a basket of unleavened bread;

3 ማኅበሩንም ሁሉ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ሰብስባቸው።

3 And gather thou all the congregation together unto the door of the tabernacle of the congregation.

4 ሙሴም እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ ማኅበሩ ሁሉ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ተሰበሰቡ።

4 And Moses did as the Lord commanded him; and the assembly was gathered together unto the door of the tabernacle of the congregation.

5 ሙሴም ማኅበሩን፦ እግዚአብሔር ይደረግ ዘንድ ያዘዘው ነገር ይህ ነው አላቸው።

5 And Moses said unto the congregation, This is the thing which the Lord commanded to be done.

6 ሙሴም አሮንንና ልጆቹን አቀረበ፥ በውኃም አጠባቸው።

6 And Moses brought Aaron and his sons, and washed them with water.

7 ሸሚዝም አለበሰው፥ በመታጠቂያም አስታጠቀው፥ ቀሚስም አለበሰው፥ ኤፉድም ደረበለት፥ በብልሃትም በተጠለፈ ቋድ አስታጠቀውና በእርሱ ላይ አሰረው።

7 And he put upon him the coat, and girded him with the girdle, and clothed him with the robe, and put the ephod upon him, and he girded him with the curious girdle of the ephod, and bound it unto him therewith.

8 የደረት ኪስ በእርሱ ላይ አደረገ በደረቱ ኪስም ውስጥ ኡሪምንና ቱሚምን አኖረበት።

8 And he put the breastplate upon him: also he put in the breastplate the Urim and the Thummim.

9 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው በራሱ ላይ መጠምጠሚያውን አደረገ በመጠምጠሚያውም ላይ በፊቱ በኩል የተቀደሰውን አክሊል፥ ቅጠል የሚመስለውን የወርቅ ምልክት፥ አደረገ።

9 And he put the mitre upon his head; also upon the mitre, even upon his forefront, did he put the golden plate, the holy crown; as the Lord commanded Moses.

10 ሙሴም የቅብዓቱን ዘይት ወሰደ፥ ማደሪያውንና በውስጡ ያለውን ሁሉ ቀብቶ ቀደሳቸው።

10 And Moses took the anointing oil, and anointed the tabernacle and all that was therein, and sanctified them.

11 ከእርሱም በመሠዊያው ላይ ሰባት ጊዜ ረጨ ይቀድሳቸውም ዘንድ መሠዊያውንና ዕቃውን ሁሉ፥ የመታጠቢያውን ሰንና መቀመጫውን ቀባ።

11 And he sprinkled thereof upon the altar seven times, and anointed the altar and all his vessels, both the laver and his foot, to sanctify them.

12 ከቅብዓቱም ዘይት በአሮን ራስ ላይ አፈሰሰ፥ ይቀድሰውም ዘንድ ቀባው።

12 And he poured of the anointing oil upon Aaron’s head, and anointed him, to sanctify him.

13 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው ሙሴ የአሮንን ልጆች አቀረበ፥ ቀሚሶችንም አለበሳቸው፥ በመታጠቂያም አስታጠቃቸው፥ ቆብም ደፋባቸው።

13 And Moses brought Aaron’s sons, and put coats upon them, and girded them with girdles, and put bonnets upon them; as the Lord commanded Moses.

14 የኃጢአትንም መሥዋዕት ወይፈን አቀረበ አሮንና ልጆቹም በኃጢአቱ መሥዋዕት ወይፈን ራስ ላይ እጆቻቸውን ጫኑ።

14 And he brought the bullock for the sin offering: and Aaron and his sons laid their hands upon the head of the bullock for the sin offering.

15 አረደውም ሙሴም ደሙን ወስዶ በጣቱ የመሠዊያውን ቀንዶች ዙሪያ ቀባ፥ መሠዊያውንም አነጻው ደሙንም ከመሠዊያው በታች አፈሰሰው፥ ያስተሰርይለትም ዘንድ ቀደሰው።

15 And he slew it; and Moses took the blood, and put it upon the horns of the altar round about with his finger, and purified the altar, and poured the blood at the bottom of the altar, and sanctified it, to make reconciliation upon it.

16 በሆድ ዕቃውም ላይ ያለውን ስብ ሁሉ፥ የጕበቱንም መረብ፥ ሁለቱንም ኵላሊቶች ስባቸውንም ወሰደ ሙሴም በመሠዊያው ላይ አቃጠለው።

16 And he took all the fat that was upon the inwards, and the caul above the liver, and the two kidneys, and their fat, and Moses burned it upon the altar.

17 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው ወይፈኑን፥ ቁርበቱንም፥ ሥጋውንም፥ ፈርሱንም ከሰፈሩ ውጭ በእሳት አቃጠለ።

17 But the bullock, and his hide, his flesh, and his dung, he burnt with fire without the camp; as the Lord commanded Moses.

18 ለሚቃጠል መሥዋዕትም የሚሆን አውራ በግ አቀረበ አሮንና ልጆቹም በአውራው በግ ራስ ላይ እጆቻቸውን ጫኑ።

18 And he brought the ram for the burnt offering: and Aaron and his sons laid their hands upon the head of the ram.

19 አረደውም ሙሴም ደሙን በመሠዊያው ዙሪያ ረጨው።

19 And he killed it; and Moses sprinkled the blood upon the altar round about.

20 አውራውንም በግ በየብልቱ ቈረጠ ሙሴም ጭንቅላቱን ብልቶቹንም ስቡንም አቃጠለ።

20 And he cut the ram into pieces; and Moses burnt the head, and the pieces, and the fat.

21 የሆድ ዕቃውንና እግሮቹንም በውኃ አጠበ ሙሴም አውራውን በግ ሁሉ በመሠዊያው ላይ አቃጠለው ይህ ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን የሚቃጠል መሥዋዕት ነበረ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባን ነበረ።

21 And he washed the inwards and the legs in water; and Moses burnt the whole ram upon the altar: it was a burnt sacrifice for a sweet savour, and an offering made by fire unto the Lord; as the Lord commanded Moses.

22 ለቅድስናም የሚሆነውን ሁለተኛውን አውራ በግ አቀረበ አሮንና ልጆቹም በአውራው በግ ራስ ላይ እጆቻቸውን ጫኑ።

22 And he brought the other ram, the ram of consecration: and Aaron and his sons laid their hands upon the head of the ram.

23 አረደውም ሙሴን ከደሙ ወስዶ የአሮንን የቀኝ ጆሮውን ጫፍ፥ የቀኝ እጁንም አውራ ጣት የቀኝ እግሩንም አውራ ጣት አስነካው።

23 And he slew it; and Moses took of the blood of it, and put it upon the tip of Aaron’s right ear, and upon the thumb of his right hand, and upon the great toe of his right foot.

24 የአሮንንም ልጆች አቀረበ ሙሴም የቀኝ ጆሮአቸውን ጫፍ፥ የቀን እጃቸውንም አውራ ጣት፥ የቀኝ እግራቸውንም አውራ ጣት ከደሙ አስነካ ሙሴም ደሙን በመሠዊያው ዙሪያ ረጨ።

24 And he brought Aaron’s sons, and Moses put of the blood upon the tip of their right ear, and upon the thumbs of their right hands, and upon the great toes of their right feet: and Moses sprinkled the blood upon the altar round about.

25 ስቡንና ላቱን፥ በሆድ ዕቃውም ላይ ያለውን ስብ ሁሉ፥ የጕበቱንም መረብ፥ ሁለቱንም ኵላሊቶች ስባቸውንም፥ ቀኝ ወርቹንም ወሰደ

25 And he took the fat, and the rump, and all the fat that was upon the inwards, and the caul above the liver, and the two kidneys, and their fat, and the right shoulder:

26 በእግዚአብሔር ፊት ካለው ከቂጣው እንጀራ ሌማት አንድ የቂጣ እንጐቻ፥ አንድም የዘይት እንጀራ፥ አንድም ስስ ቂጣ ወስዶ በስቡና በቀኝ ወርቹ ላይ አኖራቸው።

26 And out of the basket of unleavened bread, that was before the Lord, he took one unleavened cake, and a cake of oiled bread, and one wafer, and put them on the fat, and upon the right shoulder:

27 ሁሉንም በአሮንና በልጆቹ እጆች ላይ አደረገ፥ በእግዚአብሔርም ፊት ለመወዝወዝ ቍርባን ወዘወዛቸው።

27 And he put all upon Aaron’s hands, and upon his sons’ hands, and waved them for a wave offering before the Lord.

28 ሙሴም ከእጃቸው ተቀብሎ በመሠዊያው በሚቃጠለው መሥዋዕት ላይ አቃጠለው የጣፋጭ ሽታ መቀደሻ ነበረ። እርሱም ለእግዚአብሔር የእሳት ቁርባን ነበረ።

28 And Moses took them from off their hands, and burnt them on the altar upon the burnt offering: they were consecrations for a sweet savour: it is an offering made by fire unto the Lord.

29 ሙሴም ፍርምባውን ወስዶ በእግዚአብሔር ፊት ለመወዝወዝ ቍርባን ወዘወዘው እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ይህ ለቅድስና ከታረደው አውራ በግ የሙሴ እድል ፈንታ ሆነ።

29 And Moses took the breast, and waved it for a wave offering before the Lord: for of the ram of consecration it was Moses’ part; as the Lord commanded Moses.

30 ሙሴም ከቅብዓቱ ዘይትና በመሠዊያው ላይ ካለው ከደሙ ወስዶ በአሮንና በልብሱ ላይ፥ በልጆቹና በልጆቹ ልብስ ላይ ረጨው አሮንንና ልብሱንም፥ ልጆቹንም የልጆቹንም ልብስ ቀደሰ።

30 And Moses took of the anointing oil, and of the blood which was upon the altar, and sprinkled it upon Aaron, and upon his garments, and upon his sons, and upon his sons’ garments with him; and sanctified Aaron, and his garments, and his sons, and his sons’ garments with him.

31 ሙሴም አሮንንና ልጆቹን አላቸው። ሥጋውን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ቀቅሉ አሮንና ልጆቹ ይበሉታል ብዬ እንዳዘዝሁ በዚያ እርሱንና በሌማቱ ያለውን የቅድስናውን እንጀራ ብሉ።

31 And Moses said unto Aaron and to his sons, Boil the flesh at the door of the tabernacle of the congregation: and there eat it with the bread that is in the basket of consecrations, as I commanded, saying, Aaron and his sons shall eat it.

32 ከሥጋውና ከእንጀራውም የተረፈውን በእሳት ታቃጥሉታላችሁ።

32 And that which remaineth of the flesh and of the bread shall ye burn with fire.

33 ሰባት ቀን ይክናችኋልና የክህነታችሁ ቀን እስኪፈጸም ድረስ ሰባት ቀን ከማኅበሩ ድንኳን ደጃፍ አትውጡ።

33 And ye shall not go out of the door of the tabernacle of the congregation in seven days, until the days of your consecration be at an end: for seven days shall he consecrate you.

34 በዚህ ቀን እንደ ተደረገ ለእናንተ ለማስተስረያ ይደረግ ዘንድ እንዲሁ እግዚአብሔር አዘዘ።

34 As he hath done this day, so the Lord hath commanded to do, to make an atonement for you.

35 እግዚአብሔር እንዲሁ አዝዞኛልና እንዳትሞቱ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ሌሊቱንና ቀኑን ሰባት ቀን ተቀመጡ፥ የእግዚአብሔርንም ሥርዓት ጠብቁ።

35 Therefore shall ye abide at the door of the tabernacle of the congregation day and night seven days, and keep the charge of the Lord, that ye die not: for so I am commanded.

36 አሮንና ልጆቹም እግዚአብሔር በሙሴ እጅ ያዘዘውን ሁሉ አደረጉ።

36 So Aaron and his sons did all things which the Lord commanded by the hand of Moses.