ኦሪት ዘሌዋውያን Orit ZeLaeWaWiYan
Leviticus / Vayikra #9
In Amharic and English
|
ኦሪት ዘሌዋውያን 9 |
Leviticus 9 |
1 በስምንተኛውም ቀን እንዲህ ሆነ ሙሴ አሮንንና ልጆቹን የእስራኤልንም ሽማግሌዎች ጠራ። |
1 And it came to pass on the eighth day, that Moses called Aaron and his sons, and the elders of Israel; |
2 አሮንንም አለው። ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ከመንጋው እምቦሳውን፥ ስለሚቃጠልም መሥዋዕት አውራውን በግ ነውር የሌለባቸውን ወስደህ በእግዚአብሔር ፊት አቅርባቸው። |
2 And he said unto Aaron, Take thee a young calf for a sin offering, and a ram for a burnt offering, without blemish, and offer them before the Lord. |
3-4 የእስራኤልንም ልጆች። ዛሬ እግዚአብሔር ይገለጥላችኋልና ለኃጢአት መሥዋዕት አውራ ፍየልን፥ ለሚቃጠልም መሥዋዕት ነውር የሌለባቸውን አንድ ዓመት የሆናቸውን እምቦሳና ጠቦትን፥ ለደኅንነትም መሥዋዕት በሬንና አውራን በግ፥ በዘይትም የተለወሰ የእህልን ቍርባን በእግዚአብሔር ፊት ይሠዉ ዘንድ ውሰዱ ብለህ ንገራቸው። |
3 And unto the children of Israel thou shalt speak, saying, Take ye a kid of the goats for a sin offering; and a calf and a lamb, both of the first year, without blemish, for a burnt offering; |
5 ሙሴም ያዘዛቸውን ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ አመጡ ማኅበሩም ሁሉ ቀርበው በእግዚአብሔር ፊት ቆሙ። |
5 And they brought that which Moses commanded before the tabernacle of the congregation: and all the congregation drew near and stood before the Lord. |
6 ሙሴም፦ ታደርጉት ዘንድ እግዚአብሔር ያዘዘው ይህ ነው የእግዚአብሔርም ክብር ይገለጥላችኋል አለ። |
6 And Moses said, This is the thing which the Lord commanded that ye should do: and the glory of the Lord shall appear unto you. |
7 ሙሴም አሮንን፦ ወደ መሠዊያው ቀርበህ የኃጢአትህን መሥዋዕትና የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን ሠዋ፥ ለራስህና ለሕዝቡም አስተስርይ እግዚአብሔርም እንዳዘዘ የሕዝቡን ቍርባን አቅርብ አስተስርይላቸውም አለው። |
7 And Moses said unto Aaron, Go unto the altar, and offer thy sin offering, and thy burnt offering, and make an atonement for thyself, and for the people: and offer the offering of the people, and make an atonement for them; as the Lord commanded. |
8 አሮንም ወደ መሠዊያው ቀርቦ ስለ ራሱ ኃጢአት መሥዋዕት የሆነውን እምቦሳ አረደ። |
8 Aaron therefore went unto the altar, and slew the calf of the sin offering, which was for himself. |
9 የአሮንም ልጆች ደሙን አቀረቡለት ጣቱንም በደሙ ውስጥ ነክሮ የመሠዊያውን ቀንዶች አስነካ፥ ደሙንም ከመሠዊያው በታች አፈሰሰው። |
9 And the sons of Aaron brought the blood unto him: and he dipped his finger in the blood, and put it upon the horns of the altar, and poured out the blood at the bottom of the altar: |
10 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው ከኃጢአቱ መሥዋዕት ስቡንና ኵላሊቶቹን፥ የጕበቱንም መረብ በመሠዊያው ላይ አቃጠለ። |
10 But the fat, and the kidneys, and the caul above the liver of the sin offering, he burnt upon the altar; as the Lord commanded Moses. |
11 ሥጋውንና ቁርበቱንም ከሰፈሩ ውጭ በእሳት አቃጠለ። |
11 And the flesh and the hide he burnt with fire without the camp. |
12 የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አረደ የአሮንም ልጆች ደሙን አመጡለት፥ እርሱም በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ረጨው። |
12 And he slew the burnt offering; and Aaron’s sons presented unto him the blood, which he sprinkled round about upon the altar. |
13 የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በየብልቱ፥ ራሱንም አመጡለት እርሱም በመሠዊያው ላይ አቃጠለው። |
13 And they presented the burnt offering unto him, with the pieces thereof, and the head: and he burnt them upon the altar. |
14 የሆድ ዕቃውንና እግሮቹንም አጠበ በመሠዊያውም በሚቃጠለው መሥዋዕት ላይ አቃጠለው። |
14 And he did wash the inwards and the legs, and burnt them upon the burnt offering on the altar. |
15 የሕዝቡንም ቍርባን አቀረበ ስለ ሕዝቡ ለኃጢአት መሥዋዕት የሆነውን ፍየል ወስዶ አረደው፥ ስለ ኃጢአትም እንደ ፊተኛው ሠዋው። |
15 And he brought the people’s offering, and took the goat, which was the sin offering for the people, and slew it, and offered it for sin, as the first. |
16 የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አቀረበ፥ እንደ ሥርዓቱም አደረገው። |
16 And he brought the burnt offering, and offered it according to the manner. |
17 የእህሉንም ቍርባን አቀረበ፥ ከእርሱም እፍኝ ሙሉ ወስዶ በጥዋት ከሚቃጠለው መሥዋዕት ሌላ በመሰዊያው ላይ አቃጠለው። |
17 And he brought the meat offering, and took an handful thereof, and burnt it upon the altar, beside the burnt sacrifice of the morning. |
18 ስለ ሕዝቡ የሆነውን የደኅንነት መሥዋዕት በሬውንና አውራውን በግ አረደ የአሮንም ልጆች ደሙን አመጡለት፥ |
18 He slew also the bullock and the ram for a sacrifice of peace offerings, which was for the people: and Aaron’s sons presented unto him the blood, which he sprinkled upon the altar round about, |
19 በመሠዊያውም ላይ በዙሪያው ረጨው የበሬውንና የአራውንም በግ ስብ፥ ላቱንም፥ የሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ፥ ኩላሊቶቹንም፥ የጉበቱንም መረብ አመጡለት። |
19 And the fat of the bullock and of the ram, the rump, and that which covereth the inwards, and the kidneys, and the caul above the liver: |
20 ስቡንም በፍርምባዎቹ ላይ አደረጉ፥ ስቡንም በመሠዊያው ላይ አቃጠለ |
20 And they put the fat upon the breasts, and he burnt the fat upon the altar: |
21 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው አሮን ፍርምባዎቹንና ቀኝ ወርቹን በእግዚአብሔር ፊት ለመወዝወዝ ቁርባን ወዘወዘው። |
21 And the breasts and the right shoulder Aaron waved for a wave offering before the Lord; as Moses commanded. |
22 አሮንም እጆቹን ወደ ሕዝቡ ዘረጋ ባረካቸውም የኃጢያቱን የሚቃጠለውንም የደኅንነቱንም መሥዋዕት ከሠዋ በኋላ ወረደ። |
22 And Aaron lifted up his hand toward the people, and blessed them, and came down from offering of the sin offering, and the burnt offering, and peace offerings. |
23 ሙሴና አሮንም ወደ መገናኛው ድንኳን ገቡ ወጡም፥ ሕዝቡንም ባረኩ የእግዚአብሔርም ክብር ለሕዝቡ ሁሉ ተገለጠ። |
23 And Moses and Aaron went into the tabernacle of the congregation, and came out, and blessed the people: and the glory of the Lord appeared unto all the people. |
24 እሳትም ከእግዚአብሔር ዘንድ ወጣ፥ በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ስቡንም በላ ሕዝቡም ሁሉ አይተው እልል አሉ፥ በግምባራቸውም ወደቁ። |
24 And there came a fire out from before the Lord, and consumed upon the altar the burnt offering and the fat: which when all the people saw, they shouted, and fell on their faces. |