ኦሪት ዘዳግም Orit ZeDaGim
Deuteronomy / Devarim #10
In Amharic and English
|
ኦሪት ዘዳግም 10 |
Deuteronomy 10 |
1 በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር፦ እንደ ፊተኞች ያሉትን ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ጠርበህ ወደ እኔ ወደ ተራራው ውጣ፥ ለአንተም የእንጨት ታቦት ሥራ |
1 At that time the Lord said unto me, Hew thee two tables of stone like unto the first, and come up unto me into the mount, and make thee an ark of wood. |
2 በሰበርሃቸውም በፊተኞቹ ጽላቶች የነበሩትን ቃሎች በእነዚህ ጽላቶች እጽፋለሁ፥ በታቦቱም ውስጥ ታደርጋቸዋለህ አለኝ። |
2 And I will write on the tables the words that were in the first tables which thou brakest, and thou shalt put them in the ark. |
3 ከግራርም እንጨት ታቦትን ሠራሁ፥ እንደ ፊተኞችም ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ጠረብሁ ሁለቱንም ጽላቶች በእጄ ይዤ ወደ ተራራው ወጣሁ። |
3 And I made an ark of shittim wood, and hewed two tables of stone like unto the first, and went up into the mount, having the two tables in mine hand. |
4 ስብሰባ ተደርጎ በነበረበትም ቀን እግዚአብሔር በተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ የተናገራችሁን አሠርቱን ቃላት ቀድሞ ተጽፈው እንደ ነበረ በጽላቶቹ ላይ ጻፈ እግዚአብሔርም እነርሱን ለእኔ ሰጠኝ። |
4 And he wrote on the tables, according to the first writing, the ten commandments, which the Lord spake unto you in the mount out of the midst of the fire in the day of the assembly: and the Lord gave them unto me. |
5 ተመልሼም ከተራራው ወረድሁ፥ ጽላቶችንም በሠራሁት ታቦት ውስጥ አደረግኋቸው እግዚአብሔርም እንዳዘዘኝ በዚያ ኖሩ። |
5 And I turned myself and came down from the mount, and put the tables in the ark which I had made; and there they be, as the Lord commanded me. |
6 የእስራኤልም ልጆች ከብኤሮት ብኔያዕቃን ወደ ሞሴራ ተጓዙ በዚያም አሮን ሞተ በዚያም ተቀበረ በእርሱም ፋንታ ልጁ አልዓዛር ካህን ሆነ። |
6 And the children of Israel took their journey from Beeroth of the children of Jaakan to Mosera: there Aaron died, and there he was buried; and Eleazar his son ministered in the priest’s office in his stead. |
7 ከዚያም ወደ ጉድጎዳ ተጓዙ ከጉድጎዳም ወደ ውኃ ፈሳሾች ምድር ወደ ዮጥባታ ተጓዙ። |
7 From thence they journeyed unto Gudgodah; and from Gudgodah to Jotbath, a land of rivers of waters. |
8 በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ይሸከም ዘንድ፥ እርሱንም ለማገልገል በእግዚአብሔር ፊት ይቆም ዘንድ፥ በስሙም ይባርክ ዘንድ እግዚአብሔር እስከ ዛሬ ድረስ የሌዊን ነገድ ለየ። |
8 At that time the Lord separated the tribe of Levi, to bear the ark of the covenant of the Lord, to stand before the Lord to minister unto him, and to bless in his name, unto this day. |
9 ስለዚህ ለሌዊ ከወንድሞቹ ጋር ክፍልና ርስት የለውም አምላክህ እግዚአብሔር እንደ ተናገረው እግዚአብሔር ርስቱ ነው። |
9 Wherefore Levi hath no part nor inheritance with his brethren; the Lord is his inheritance, according as the Lord thy God promised him. |
10 እኔም እንደ ፊተኛው ጊዜ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በተራራው ላይ ተቀመጥሁ እግዚአብሔርም በዚህ ጊዜ ደግሞ ሰማኝ እግዚአብሔር ሊያጠፋህ አልወደደም። |
10 And I stayed in the mount, according to the first time, forty days and forty nights; and the Lord hearkened unto me at that time also, and the Lord would not destroy thee. |
11 እግዚአብሔርም፦ ተነሥተህ በሕዝቡ ፊት ተጓዝ ለአባቶቻቸውም ልሰጣቸው ወደ ማልሁላቸው ምድር ይግቡ ይውረሱአትም አለኝ። |
11 And the Lord said unto me, Arise, take thy journey before the people, that they may go in and possess the land, which I sware unto their fathers to give unto them. |
12-13 እስራኤል ሆይ፥ አሁንስ አምላክህን እግዚአብሔርን ትፈራ ዘንድ፥ በመንገዱም ሁሉ ትሄድ ዘንድ፥ አምላክህንም እግዚአብሔርን ትወድድ ዘንድ፥ በፍጹምም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ ታመልከው ዘንድ፥ መልካምም እንዲሆንልህ ዛሬ ለአንተ የማዝዘውን የእግዚአብሔርን ትእዛዝና ሥርዓት ትጠብቅ ዘንድ ነው እንጂ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ የሚፈልገው ምንድር ነው? |
12 And now, Israel, what doth the Lord thy God require of thee, but to fear the Lord thy God, to walk in all his ways, and to love him, and to serve the Lord thy God with all thy heart and with all thy soul, |
14 እነሆ፥ ሰማይ ሰማየ ሰማያትም፥ ምድርም በእርስዋም ያለው ሁሉ የአምላክህ የእግዚአብሔር ነው። |
14 Behold, the heaven and the heaven of heavens is the Lord’s thy God, the earth also, with all that therein is. |
15 ብቻ እግዚአብሔር ስለ አባቶችህ ደስ ብሎታል፥ እነርሱንም ወድዶአል ከእነርሱም በኋላ እናንተን ዘራቸውን እንደ ዛሬው ሁሉ ከአሕዛብ ሁሉ መካከል መረጠ። |
15 Only the Lord had a delight in thy fathers to love them, and he chose their seed after them, even you above all people, as it is this day. |
16-17 እንግዲህ አምላካችሁ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ የጌቶችም ጌታ፥ ታላቅ አምላክ ኃያልም የሚያስፈራም፥ በፍርድ የማያደላ፥ መማለጃም የማይቀበል ነውና እናንተ የልባችሁን ሸለፈት ግረዙ፥ ክእንግዲህ ወዲህም አንገተ ደንዳና አትሁኑ። |
16 Circumcise therefore the foreskin of your heart, and be no more stiffnecked. |
18 ለድሃ አደጉና ለመበለቲቱ ይፈርዳል፥ መብልና ልብስም ይሰጠው ዘንድ ስደተኛውን ይወድዳል። |
18 He doth execute the judgment of the fatherless and widow, and loveth the stranger, in giving him food and raiment. |
19 እናንተ በግብፅ አገር ስደተኞች ነበራችሁና ስለዚህ ስደተኛውን ውደዱ። |
19 Love ye therefore the stranger: for ye were strangers in the land of Egypt. |
20 አምላክህን እግዚአብሔርን ፍራ፥ እርሱንም አምልክ ከእርሱም ተጣበቅ፥ በስሙም ማል። |
20 Thou shalt fear the Lord thy God; him shalt thou serve, and to him shalt thou cleave, and swear by his name. |
21 ዓይኖችህ ያዩትን እነዚህን ታላላቆች የሚያስፈሩትንም ነገሮች ያደረገልህ እርሱ ክብርህ ነው፥ እርሱም አምላክህ ነው። |
21 He is thy praise, and he is thy God, that hath done for thee these great and terrible things, which thine eyes have seen. |
22 አባቶችህ ሰባ ነፍስ ሆነው ወደ ግብፅ ወረዱ አሁንም አምላክህ እግዚአብሔር ብዛትህን እንደ ሰማይ ከዋክብት አደረገ። |
22 Thy fathers went down into Egypt with threescore and ten persons; and now the Lord thy God hath made thee as the stars of heaven for multitude. |