መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David #51
In Amharic and English
መዝሙረ ዳዊት 51 |
Psalm 51 |
1 አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ እንደ ምሕረትህም ብዛት መተላለፌን ደምስስ። |
1 Have mercy upon me, O God, according to thy lovingkindness: according unto the multitude of thy tender mercies blot out my transgressions. |
2 ከበደሌ ፈጽሞ እጠበኝ፥ ከኃጢአቴም አንጻኝ |
2 Wash me throughly from mine iniquity, and cleanse me from my sin. |
3 እኔ መተላለፌን አውቃለሁና፥ ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ ነውና። 4 አንተን ብቻ በደልሁ፥ በፊትህም ክፋትን አደረግሁ፥ በነገርህም ትጸድቅ ዘንድ በፍርድህም ንጹሕ ትሆን ዘንድ። |
3 For I acknowledge my transgressions: and my sin is ever before me. |
5 እነሆ፥ በዓመፃ ተፀነስሁ፥ እናቴም በኃጢአት ወለደችኝ። |
5 Behold, I was shapen in iniquity; and in sin did my mother conceive me. |
6 እነሆ፥ እውነትን ወደድህ የማይታይ ስውር ጥበብን አስታወቅኸኝ። |
6 Behold, thou desirest truth in the inward parts: and in the hidden part thou shalt make me to know wisdom. |
7 በሂሶጵ እርጨኝ፥ እነጻማለሁ እጠበኝ፥ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ። |
7 Purge me with hyssop, and I shall be clean: wash me, and I shall be whiter than snow. |
8 ሐሤትንና ደስታን አሰማኝ፥ የሰበርሃቸውም አጥንቶቼ ደስ ይላቸዋል። |
8 Make me to hear joy and gladness; that the bones which thou hast broken may rejoice. |
9 ከኃጢአቴ ፊትህን መልስ፥ በደሌንም ሁሉ ደምስስልኝ። |
9 Hide thy face from my sins, and blot out all mine iniquities. |
10 አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ። |
10 Create in me a clean heart, O God; and renew a right spirit within me. |
11 ከፊትህ አትጣለኝ፥ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ። |
11 Cast me not away from thy presence; and take not thy holy spirit from me. |
12 የማዳንህን ደስታ ስጠኝ፥ በእሽታ መንፈስም ደግፈኝ። |
12 Restore unto me the joy of thy salvation; and uphold me with thy free spirit. |
13 ለሕግ ተላላፎች መንገድህን አስተምራለሁ፥ ኃጢአተኞችም ወደ አንተ ይመለሳሉ። |
13 Then will I teach transgressors thy ways; and sinners shall be converted unto thee. |
14 የመድኃኒቴ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ ከደም አድነኝ፥ አንደበቴም በአንተ ጽድቅ ትደሰታለች። |
14 Deliver me from bloodguiltiness, O God, thou God of my salvation: and my tongue shall sing aloud of thy righteousness. |
15 አቤቱ፥ ከንፈሮቼን ክፈት፥ አፌም ምስጋናህን ያወራል። |
15 O Lord, open thou my lips; and my mouth shall shew forth thy praise. |
16 መሥዋዕትን ብትወድድስ በሰጠሁህ ነበር የሚቃጠለውም መሥዋዕት ደስ አያሰኝህም። |
16 For thou desirest not sacrifice; else would I give it: thou delightest not in burnt offering. |
17 የእግዚአብሔር መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፥ የተሰበርውንና የተዋረደውን ልብ እግዚአብሔር አይንቅም። |
17 The sacrifices of God are a broken spirit: a broken and a contrite heart, O God, thou wilt not despise. |
18 አቤቱ፥ በውዴታህ ጽዮንን አሰማምራት የኢየሩሳሌምንም ቅጽሮች ሥራ። |
18 Do good in thy good pleasure unto Zion: build thou the walls of Jerusalem. |
19 የጽድቁን መሥዋዕት መባውንም የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በወደድህ ጊዜ፥ ያን ጊዜ በመሠዊያህ ላይ ፍሪዳዎችን ይሠዋሉ። |
19 Then shalt thou be pleased with the sacrifices of righteousness, with burnt offering and whole burnt offering: then shall they offer bullocks upon thine altar. |