መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David  #50
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

መዝሙረ ዳዊት 50

Psalm 50

1 የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ተናገረ፥ ከፀሓይም መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ምድርን ጠራት።

1 The mighty God, even the Lord, hath spoken, and called the earth from the rising of the sun unto the going down thereof.

2 ከክብሩ ውበት ከጽዮን እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል።

2 Out of Zion, the perfection of beauty, God hath shined.

3 አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም እሳት በፊት ይቃጠላል፥ በዙሪያውም ብዙ ዐውሎ አለ።

3 Our God shall come, and shall not keep silence: a fire shall devour before him, and it shall be very tempestuous round about him.

4 በላይ ያለውን ሰማይን ምድርንም በሕዝቡ ለመፍረድ ይጠራል

4 He shall call to the heavens from above, and to the earth, that he may judge his people.

5 ከእርሱ ጋር ለመሥዋዕት ኪዳን የቆሙትን ቅዱሳኑን ሰብስቡለት።

5 Gather my saints together unto me; those that have made a covenant with me by sacrifice.

6 ሰማያት ጽድቁን ይናገራሉ፥ እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና።

6 And the heavens shall declare his righteousness: for God is judge himself. Selah.

7 ሕዝቤ፥ ስማኝ፥ ልንገርህ እስራኤልም፥ ስማኝ፥ ልመስክርብህ አምላክስ እኔ አምላክህ ነኝ።

7 Hear, O my people, and I will speak; O Israel, and I will testify against thee: I am God, even thy God.

8 ስለ ቍርባንህ የምዘልፍህ አይደለሁም የሚቃጠል መሥዋዕትህ ሁልጊዜ በፊቴ ነው።

8 I will not reprove thee for thy sacrifices or thy burnt offerings, to have been continually before me.

9 ከቤትህ ፍሪዳን ከመንጋህም አውራ ፍየልን አልወስድም

9 I will take no bullock out of thy house, nor he goats out of thy folds.

10 የምድረ በዳ አራዊት ሁሉ በሺህ ተራራዎች ያሉ እንስሶችም የእኔ ናቸውና።

10 For every beast of the forest is mine, and the cattle upon a thousand hills.

11 የሰማይን አዕዋፍ ሁሉ አውቃለሁ፥ የምድረ በዳ አራዊትም በእኔ ዘንድ ናቸው።

11 I know all the fowls of the mountains: and the wild beasts of the field are mine.

12 ብራብም ለአንተ አልነግርህም፥ ዓለምና ሞላው የእኔ ነውና።

12 If I were hungry, I would not tell thee: for the world is mine, and the fulness thereof.

13 የፍሪዳውን ሥጋ እበላለሁን? የፍየሉንስ ደም እጠጣለሁን?

13 Will I eat the flesh of bulls, or drink the blood of goats?

14 ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ሠዋ፥ ለልዑልም ስእለትህን ስጥ

14 Offer unto God thanksgiving; and pay thy vows unto the most High:

15 በመከራ ቀን ጥራኝ፥ አድንህማለሁ አንተም ታከብረኛለህ።

15 And call upon me in the day of trouble: I will deliver thee, and thou shalt glorify me.

16 ኃጢአተኛውን ግን እግዚአብሔር አለው። ለምን አንተ ሕጌን ትናገራለህ? ኪዳኔንም በአፍህ ለምን ትወስዳለህ?

16 But unto the wicked God saith, What hast thou to do to declare my statutes, or that thou shouldest take my covenant in thy mouth?

17 አንተስ ተግሣጼን ጠላህ፥ ቃሎቼንም ወደ ኋላህ ጣልህ።

17 Seeing thou hatest instruction, and castest my words behind thee.

18 ሌባውን ባየህ ጊዜ ከእርሱ ጋር ትሮጥ ነበር እድል ፈንታህንም ከአመንዝሮች ጋር አደረግህ።

18 When thou sawest a thief, then thou consentedst with him, and hast been partaker with adulterers.

19 አፍህ ክፋትን አበዛ፥ አንደበትህም ሽንገላን ተበተበ።

19 Thou givest thy mouth to evil, and thy tongue frameth deceit.

20 ተቀምጠህ ወንድምህን አማኸው፥ ለእናትህም ልጅ ዕንቅፋት አኖርህ።

20 Thou sittest and speakest against thy brother; thou slanderest thine own mother’s son.

21 ይህን አድርገህ ዝም አልሁህ እኔ እንደ አንተ እሆን ዘንድ ጠረጠርህ እዘልፍሃለሁ በፊትህም እቆማለሁ።

21 These things hast thou done, and I kept silence; thou thoughtest that I was altogether such an one as thyself: but I will reprove thee, and set them in order before thine eyes.

22 እግዚአብሔርን የምትረሱ እናንተ፥ ይህን አስተውሉ አለዚያ ግን ይነጥቃል የሚያድንም የለም።

22 Now consider this, ye that forget God, lest I tear you in pieces, and there be none to deliver.

23 ምስጋና የሚሠዋ ያከብረኛል የእግዚአብሔርን ማዳን ለእርሱ የማሳይበት መንገድ ከዚያ አለ።

23 Whoso offereth praise glorifieth me: and to him that ordereth his conversation aright will I shew the salvation of God.