መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David #49
In Amharic and English
መዝሙረ ዳዊት 49 |
Psalm 49 |
1 አሕዛብ ሁላችሁ፥ ይህን ስሙ በዓለም የምትኖሩትም ሁላችሁ፥ አድምጡ |
1 Hear this, all ye people; give ear, all ye inhabitants of the world: |
2 ዝቅተኞችና ከፍተኞች፥ ባለጠጎችና ድሆች በአንድነት። |
2 Both low and high, rich and poor, together. |
3 አፌ ጥበብን ይናገራል፥ የልቤም አሳብ ማስተዋልን። |
3 My mouth shall speak of wisdom; and the meditation of my heart shall be of understanding. |
4 ጆሮዬን ወደ ምሳሌ አዘነብላለሁ፥ በበገናም ምሥጢሬን እገልጣለሁ። |
4 I will incline mine ear to a parable: I will open my dark saying upon the harp. |
5 ኃጢአት ተረከዜን በከበበኝ ጊዜ በክፉ ቀን ለምን እፈራለሁ? |
5 Wherefore should I fear in the days of evil, when the iniquity of my heels shall compass me about? |
6 በኃይላቸው የሚታመኑ፥ በባለጠግነታቸውም ብዛት የሚመኩ |
6 They that trust in their wealth, and boast themselves in the multitude of their riches; |
7 ወንድም ወንድሙን አያድንም፥ ሰውም አያድንም ቤዛውን ለእግዚአብሔር አይሰጥም፥ |
7 None of them can by any means redeem his brother, nor give to God a ransom for him: |
8-9 ለዘላለም እንዲኖር፥ ጥፋትንም እንዳያይ የነፍሳቸው ለውጥ ከብሮአልና፥ ለዘላለምም ቀርቶአልና። |
8 (For the redemption of their soul is precious, and it ceaseth for ever:) |
10 ብልሃተኞች እንዲሞቱ፥ ሰነፎችችና ደንቆሮች በአንድነት እንዲጠፉ፥ ገንዘባቸውንም ለሌሎች እንዲተዉ አይቶአል። |
10 For he seeth that wise men die, likewise the fool and the brutish person perish, and leave their wealth to others. |
11 በልባቸውም ቤታቸው ለዘላለም የሚኖር፥ ማደሪያቸውም ለልጆች ልጅ የሚሆን ይመስላቸዋል በየአገራቸውም ስማቸው ይጠራል። |
11 Their inward thought is, that their houses shall continue for ever, and their dwelling places to all generations; they call their lands after their own names. |
12 ሰው ግን ክቡር ሆኖ ሳለ አያውቅም እንደሚጠፉ እንስሶች መሰለ። |
12 Nevertheless man being in honour abideth not: he is like the beasts that perish. |
13 ይህች መንገዳቸው መሰናክላቸው ናት፥ ከእነርሱም በኋላ የሚመጡ በአፋቸው እሺ ይላሉ። |
13 This their way is their folly: yet their posterity approve their sayings. Selah. |
14 እንደ በጎች ወደ ሲኦል የሚሄዱ ናቸው፥ እረኛቸውም ሞት ነው ቅኖችንም በማለዳ ይገዙአቸዋል፥ ውበታቸውም ከመኖሪያቸው ተለይታ በሲኦል ታረጃለች። |
14 Like sheep they are laid in the grave; death shall feed on them; and the upright shall have dominion over them in the morning; and their beauty shall consume in the grave from their dwelling. |
15 ነገር ግን እግዚአብሔር ይቀበለኛልና ነፍሴን ከሲኦል እጅ ይቤዣታል። |
15 But God will redeem my soul from the power of the grave: for he shall receive me. Selah. |
16 የሰው ባለጠግነት የቤቱም ክብር በበዛ ጊዜ አትፍራ፥ |
16 Be not thou afraid when one is made rich, when the glory of his house is increased; |
17 በሞተ ጊዜ ከእርሱ ጋር ምንም አይወስድምና፥ ክብሩም ከእርሱ በኋላ አይወርድምና። |
17 For when he dieth he shall carry nothing away: his glory shall not descend after him. |
18 በሕይወቱ ሳለ ነፍሱን ባርኮአልና ለሰውነቱ መልካም ብታደርግለት ያመሰግንሃል። |
18 Though while he lived he blessed his soul: and men will praise thee, when thou doest well to thyself. |
19 ሆኖም ወደ አባቶቹ ትውልድ ይወርዳል ለዘላለም ብርሃንን አያይም። |
19 He shall go to the generation of his fathers; they shall never see light. |
20 አእምሮ የሌለው ክቡር ሰው እንደሚጠፋ እንስሶች መሰለ። |
20 Man that is in honour, and understandeth not, is like the beasts that perish. |