መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David #81
In Amharic and English
መዝሙረ ዳዊት 81 |
Psalm 81 |
1 በረድኤታችን በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፥ ለያዕቆብም አምላክ እልል በሉ። |
1 Sing aloud unto God our strength: make a joyful noise unto the God of Jacob. |
2 ዝማሬውን አንሡ ከበሮንም ስጡ፥ ደስ የሚያሰኘውን በገና ከመሰንቆ ጋር |
2 Take a psalm, and bring hither the timbrel, the pleasant harp with the psaltery. |
3 በመባቻ ቀን በከፍተኛው በዓላችን ቀን መለከትን ንፉ |
3 Blow up the trumpet in the new moon, in the time appointed, on our solemn feast day. |
4 ለእስራኤል ሥርዓቱ ነውና፥ የያዕቆብም አምላክ ፍርድ። |
4 For this was a statute for Israel, and a law of the God of Jacob. |
5 ከግብጽ በወጣ ጊዜ ለዮሴፍ ምስክር አቆመው። ያላወቅሁትን ቋንቋ ሰማሁ። |
5 This he ordained in Joseph for a testimony, when he went out through the land of Egypt: where I heard a language that I understood not. |
6 ጫንቃውን ከሸክም፥ እጆቹንም በቅርጫት ከመገዛት አራቅሁ። |
6 I removed his shoulder from the burden: his hands were delivered from the pots. |
7 በመከራህ ጊዜ ጠራኸኝ አዳንሁህም፥ በተሰወረ ዐውሎም መለስሁልህ፥ በክርክር ውኃ ዘንድም ፈተንሁህ። |
7 Thou calledst in trouble, and I delivered thee; I answered thee in the secret place of thunder: I proved thee at the waters of Meribah. Selah. |
8 ሕዝቤ ሆይ፥ስማኝ እነግርሃለሁም እስራኤል ሆይ፥ እመሰክርልሃለሁ። |
8 Hear, O my people, and I will testify unto thee: O Israel, if thou wilt hearken unto me; |
9 አንተስ ብትሰማኝ ሌላ አምላክ አይሆንልህም፥ ለሌላ አምላክም አትሰግድም። |
9 There shall no strange god be in thee; neither shalt thou worship any strange god. |
10 ከግብጽ ምድር ያወጣሁህ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝና አፍህን አስፋ እሞላዋለሁም። |
10 I am the Lord thy God, which brought thee out of the land of Egypt: open thy mouth wide, and I will fill it. |
11 ሕዝቤ ግን ቃሌን አልሰሙኝም፥ እስራኤልም አላዳመጠኝም። |
11 But my people would not hearken to my voice; and Israel would none of me. |
12 እንደ ልባቸው ሥራ ተውኋቸው፥ በልባቸውም አሳብ ሄዱ። |
12 So I gave them up unto their own hearts’ lust: and they walked in their own counsels. |
13 ሕዝቤስ ሰምቶኝ ቢሆን፥ እስራኤልም በመንገዴ ሄደው ቢሆን |
13 Oh that my people had hearkened unto me, and Israel had walked in my ways! |
14 ጠላቶቻቸውን ፈጥኜ ባዋረድኋቸው ነበር፥ በሚያስጨንቋቸውም ላይ እጄን በጣልሁ ነበር |
14 I should soon have subdued their enemies, and turned my hand against their adversaries. |
15 የእግዚአብሔር ጠላቶችም በተገዙለት ነበር፥ ዘመናቸውም ለዘላለም በሆነ ነበር |
15 The haters of the Lord should have submitted themselves unto him: but their time should have endured for ever. |
16 ከስንዴም ስብ ባበላቸው ነበር፥ ከዓለቱም ማር ባጠገባቸው ነበር። |
16 He should have fed them also with the finest of the wheat: and with honey out of the rock should I have satisfied thee. |