ኦሪት ዘኍልቍ Orit ZeHwilQwi
Numbers / Bamidbar #9
In Amharic and English
|
ኦሪት ዘኍልቍ 9 |
Numbers 9 |
1 ከግብፅ ምድር በወጡ በሁለተኛው ዓመት በመጀመሪያው ወር በሲና ምድረ በዳ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው። |
1 And the Lord spake unto Moses in the wilderness of Sinai, in the first month of the second year after they were come out of the land of Egypt, saying, |
2 የእስራኤል ልጆች በጊዜው ፋሲካውን ያድርጉ |
2 Let the children of Israel also keep the passover at his appointed season. |
3 በዚህ ወር በአሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በጊዜው አድርጉት እንደ ሥርዓቱ ሁሉ እንደ ፍርዱም ሁሉ አድርጉት። |
3 In the fourteenth day of this month, at even, ye shall keep it in his appointed season: according to all the rites of it, and according to all the ceremonies thereof, shall ye keep it. |
4 ሙሴም ፋሲካን ያደርጉ ዘንድ የእስራኤልን ልጆች ተናገራቸው። |
4 And Moses spake unto the children of Israel, that they should keep the passover. |
5 በመጀመሪያውም ወር በአሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በሲና ምድረ በዳ ፋሲካን አደረጉ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ የእስራኤል ልጆች አደረጉ። |
5 And they kept the passover on the fourteenth day of the first month at even in the wilderness of Sinai: according to all that the Lord commanded Moses, so did the children of Israel. |
6 በሞተ ሰው ሬሳ የረከሱ ሰዎችም ነበሩ፥ ስለዚህም በዚያ ቀን ፋሲካን ያደርጉ ዘንድ አልቻሉም። በዚያም ቀን ወደ ሙሴና ወደ አሮን ቀረቡ። |
6 And there were certain men, who were defiled by the dead body of a man, that they could not keep the passover on that day: and they came before Moses and before Aaron on that day: |
7 እነዚያም ሰዎች። በሞተ ሰው ሬሳ ረክሰናል በእስራኤል ልጆች መካከል በጊዜው ቍርባን ለእግዚአብሔር እንዳናቀርብ ስለ ምን እንከለከላለን? አሉት። |
7 And those men said unto him, We are defiled by the dead body of a man: wherefore are we kept back, that we may not offer an offering of the Lord in his appointed season among the children of Israel? |
8 ሙሴም፦ እግዚአብሔር ስለ እናንተ የሚያዝዘውን እስክሰማ ድረስ ቈዩ አላቸው። |
8 And Moses said unto them, Stand still, and I will hear what the Lord will command concerning you. |
9 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው። |
9 And the Lord spake unto Moses, saying, |
10 ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው። ከእናንተ ወይም ከትውልዶቻችሁ ዘንድ ሰው በሬሳ ቢረክስ፥ ወይም ሩቅ መንገድ ቢሄድ፥ እርሱ ደግሞ ለእግዚአብሔር ፋሲካን ያድርግ። |
10 Speak unto the children of Israel, saying, If any man of you or of your posterity shall be unclean by reason of a dead body, or be in a journey afar off, yet he shall keep the passover unto the Lord. |
11 በሁለተኛው ወር በአሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ ያድርጉት ከቂጣ እንጀራና ከመራራ ቅጠል ጋር ይብሉት። |
11 The fourteenth day of the second month at even they shall keep it, and eat it with unleavened bread and bitter herbs. |
12 ከእርሱም እስከ ነገ ምንም አያስቀሩ፥ ከእርሱም አጥንትን አይስበሩ እንደ ፋሲካ ሥርዓት ሁሉ ያድርጉት። |
12 They shall leave none of it unto the morning, nor break any bone of it: according to all the ordinances of the passover they shall keep it. |
13 ነገር ግን ንጹሕ የሆነ ሰው በመንገድም ላይ ያልሆነ ፋሲካን ባያደርግ፥ ያ ሰው ከሕዝቡ ዘንድ ተለይቶ ይጠፋል የእግዚአብሔርን ቍርባን በጊዜው አላቀረበምና ያ ሰው ኃጢአቱን ይሸከማል። |
13 But the man that is clean, and is not in a journey, and forbeareth to keep the passover, even the same soul shall be cut off from among his people: because he brought not the offering of the Lord in his appointed season, that man shall bear his sin. |
14 በመካከላችሁም መጻተኛ ቢኖር፥ ለእግዚአብሔር ፋሲካን ያደርግ ዘንድ ቢወድድ፥ እንደ ፋሲካ ሥርዓት እንደ ፍርዱም እንዲሁ ያድርግ ለመጻተኛና ለአገር ልጅ አንድ ሥርዓት ይሁንላችሁ። |
14 And if a stranger shall sojourn among you, and will keep the passover unto the Lord; according to the ordinance of the passover, and according to the manner thereof, so shall he do: ye shall have one ordinance, both for the stranger, and for him that was born in the land. |
15 ማደሪያውም በተተከለ ቀን ደመናው የምስክሩን ድንኳን ሸፈነው ከማታም ጀምሮ እስከ ጥዋት ድረስ በማደሪያው ላይ እንደ እሳት ይመስል ነበር። |
15 And on the day that the tabernacle was reared up the cloud covered the tabernacle, namely, the tent of the testimony: and at even there was upon the tabernacle as it were the appearance of fire, until the morning. |
16 እንዲሁ ሁልጊዜ ነበረ በቀን ደመና በሌሊትም የእሳት አምሳል ይሸፍነው ነበር። |
16 So it was alway: the cloud covered it by day, and the appearance of fire by night. |
17 ደመናውም ከድንኳኑ ላይ በተነሣ ጊዜ በዚያን ጊዜ የእስራኤል ልጆች ይጓዙ ነበር ደመናውም በቆመበት ስፍራ በዚያ የእስራኤል ልጆች ይሰፍሩ ነበር። |
17 And when the cloud was taken up from the tabernacle, then after that the children of Israel journeyed: and in the place where the cloud abode, there the children of Israel pitched their tents. |
18 በእግዚአብሔር ትእዛዝ የእስራኤል ልጆች ይጓዙ ነበር፥ በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ይሰፍሩ ነበር። ደመናው በማደሪያው ላይ በተቀመጠበት ዘመን ሁሉ በሰፈራቸው ይቀመጡ ነበር። |
18 At the commandment of the Lord the children of Israel journeyed, and at the commandment of the Lord they pitched: as long as the cloud abode upon the tabernacle they rested in their tents. |
19 ደመናውም በማደሪያው ላይ ብዙ ቀን በተቀመጠ ጊዜ የእስራኤል ልጆች የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይጠብቁ ነበር፥ አይጓዙምም ነበር። |
19 And when the cloud tarried long upon the tabernacle many days, then the children of Israel kept the charge of the Lord, and journeyed not. |
20 አንዳንድ ጊዜ ደመናው ጥቂት ቀን በማደሪያው ላይ ይሆን ነበር በዚያን ጊዜ እንደ እግዚአብሔር ትእዛዝ በሰፈራቸው ይቀመጡ ነበር እንደ እግዚአብሔርም ትእዛዝ ይጓዙ ነበር። |
20 And so it was, when the cloud was a few days upon the tabernacle; according to the commandment of the Lord they abode in their tents, and according to the commandment of the Lord they journeyed. |
21 አንዳንድ ጊዜም ደመናው ከማታ ጀምሮ እስከ ጥዋት ድረስ ይቀመጥ ነበር በጥዋትም ደመናው በተነሣ ጊዜ ይጓዙ ነበር በቀንም በሌሊትም ቢሆን፥ ደመናው በተነሣ ጊዜ ይጓዙ ነበር። |
21 And so it was, when the cloud abode from even unto the morning, and that the cloud was taken up in the morning, then they journeyed: whether it was by day or by night that the cloud was taken up, they journeyed. |
22 ደመናውም ሁለት ቀን ወይም አንድ ወር ወይም አንድ ዓመት ቆይቶ በማደሪያው ላይ ቢቀመጥ የእስራኤል ልጆች በሰፈራቸው ይቀመጡ ነበር፥ አይጓዙምም ነበር ነገር ግን በተነሣ ጊዜ ይጓዙ ነበር። |
22 Or whether it were two days, or a month, or a year, that the cloud tarried upon the tabernacle, remaining thereon, the children of Israel abode in their tents, and journeyed not: but when it was taken up, they journeyed. |
23 በእግዚአብሔር ትእዛዝ ይሰፍሩ ነበር፥ በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ይጓዙ ነበር፥ እግዚአብሔር በሙሴ እጅ እንዳዘዘ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይጠብቁ ነበር። |
23 At the commandment of the Lord they rested in the tents, and at the commandment of the Lord they journeyed: they kept the charge of the Lord, at the commandment of the Lord by the hand of Moses. |