ኦሪት ዘፍጥረት Orit ZeFiTret
Genesis / Bereisheit #10
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

ኦሪት ዘፍጥረት 10

Genesis 10

1 የኖኅ ልጆች የሴም የካም የያፌት ትውልድ ይህ ነው ከጥፋት ውኃም በኋላ ልጆች ተወለዱላቸው።

1 Now these are the generations of the sons of Noah, Shem, Ham, and Japheth: and unto them were sons born after the flood.

2 የያፌት ልጆች ጋሜር፥ ማጎግ፥ ማዴ፥ ያዋን፥ ይልሳ፥ ቶቤል፥ ሞሳሕ፥ ቴራስ ናቸው።

2 The sons of Japheth; Gomer, and Magog, and Madai, and Javan, and Tubal, and Meshech, and Tiras.

3 የጋሜርም ልጆች አስከናዝ፥ ሪፋት፥ ቴርጋማ ናቸው።

3 And the sons of Gomer; Ashkenaz, and Riphath, and Togarmah.

4 የያዋንም ልጆች ኤሊሳ፥ ተርሴስ፥ ኪቲም፥ ሮድኢ ናቸው።

4 And the sons of Javan; Elishah, and Tarshish, Kittim, and Dodanim.

5 ከእነዚህም የአሕዛብ ደሴቶች ሁሉ በየምድራቸው በየቋንቋቸው በየነገዳቸው በየሕዝባቸው ተከፋፈሉ።

5 By these were the isles of the Gentiles divided in their lands; every one after his tongue, after their families, in their nations.

6 የካምም ልጆች ኩሽ፥ ምጽራይም፥ ፉጥ፥ ከነዓን ናቸው።

6 And the sons of Ham; Cush, and Mizraim, and Phut, and Canaan.

7 የኩሽም ልጆች ሳባ፥ ኤውላጥ፥ ሰብታ፥ ራዕማ፥ ሰበቃታ ናቸው። የራዕማ ልጆችም ሳባ፥ ድዳን ናቸው።

7 And the sons of Cush; Seba, and Havilah, and Sabtah, and Raamah, and Sabtecha: and the sons of Raamah; Sheba, and Dedan.

8 ኩሽም ናምሩድን ወለደ እርሱም በምድር ላይ ኃያል መሆንን ጀመረ።

8 And Cush begat Nimrod: he began to be a mighty one in the earth.

9 እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ኃያል አዳኝ ነበረ ስለዚህም፦ በእግዚአብሔር ፊት ኃያል አዳኝ እንደ ናምሩድ ተባለ።

9 He was a mighty hunter before the Lord: wherefore it is said, Even as Nimrod the mighty hunter before the Lord.

10 የግዛቱም መጀመሪያ በሰናዖር አገር ባቢሎን፥ ኦሬክ፥ አርካድ፥ ካልኔ ናቸው።

10 And the beginning of his kingdom was Babel, and Erech, and Accad, and Calneh, in the land of Shinar.

11 አሦርም ከዚያች አገር ወጣ ነነዌን፥ የረሆቦትን ከተማ፥ ካለህን፥

11 Out of that land went forth Asshur, and builded Nineveh, and the city Rehoboth, and Calah,

12 በነነዌና በካለህ መካከልም ሬሴንን ሠራ እርስዋም ታላቂቱ ከተማ ናት።

12 And Resen between Nineveh and Calah: the same is a great city.

13 ምጽራይምም ሉዲምን፥ ዐናሚምን፥ ላህቢምን፥ ነፍታሌምን፥ ፈትሩሲምን፥

13 And Mizraim begat Ludim, and Anamim, and Lehabim, and Naphtuhim,

14 ከእነርሱ የፍልስጥኤም ሰዎች የወጡባቸውን ከስሉሂምን፥ ቀፍቶሪምንም ወለደ።

14 And Pathrusim, and Casluhim, (out of whom came Philistim,) and Caphtorim.

15 ከነዓንም የበኵር ልጁን ሲዶንን፥ ኬጢያውያንንም፥

15 And Canaan begat Sidon his firstborn, and Heth,

16 ኢያቡሳውያንንም፥ አሞራውያንንም፥

16 And the Jebusite, and the Amorite, and the Girgasite,

17 ጌርጌሳውያንንም፥ ኤዊያውያንንም፥

17 And the Hivite, and the Arkite, and the Sinite,

18 ዐሩኬዎንንም፥ ሲኒንም፥ አራዴዎንንም፥ ሰማሪዎንንም፥ አማቲንም ወለደ። ከዚህም በኋላ የከነዓናውያን ነገድ ተበተኑ።

18 And the Arvadite, and the Zemarite, and the Hamathite: and afterward were the families of the Canaanites spread abroad.

19 የከነዓናውያንም ወሰን ከሲዶን አንሥቶ ወደ ጌራራ በኩል ሲል እስከ ጋዛ ድረስ ነው ወደ ሰዶምና ወደ ገሞራ፥ ወደ አዳማና ወደ ሰቦይም በኩልም ሲል እስከ ላሣ ድረስ ነው።

19 And the border of the Canaanites was from Sidon, as thou comest to Gerar, unto Gaza; as thou goest, unto Sodom, and Gomorrah, and Admah, and Zeboim, even unto Lasha.

20 የካም ልጆች በየነገዳቸውና በየቋንቋቸው፥ በየምድራችውና በየሕዝባቸው እነዚህ ናቸው።

20 These are the sons of Ham, after their families, after their tongues, in their countries, and in their nations.

21 ለሴምም ደግሞ ልጆች ተወለዱለት እርሱም የያፌት ታላቅ ወንድምና የዔቦር ልጆች ሁሉ አባት የሆነ ነው።

21 Unto Shem also, the father of all the children of Eber, the brother of Japheth the elder, even to him were children born.

22 የሴምም ልጆች ኤላም፥ አሦር፥ አርፋክስድ፥ ሉድ፥ አራም ናቸው።

22 The children of Shem; Elam, and Asshur, and Arphaxad, and Lud, and Aram.

23 የአራምም ልጆች ዑፅ፥ ሁል፥ ጌቴር፥ ሞሶሕ ናቸው።

23 And the children of Aram; Uz, and Hul, and Gether, and Mash.

24 አርፋክስድም ቃይንምን ወለደ ቃይንምም ሳላን፥ ሳላም ዔቦርን ወለደ።

24 And Arphaxad begat Salah; and Salah begat Eber.

25 ለዔቦርም ሁለት ልጆች ተወለዱለት የአንደኛው ስሙ ፋሌቅ ነው፥ ምድር በዘመኑ ተከፍላለችና የወንድሙም ስም ዮቅጣን ነው።

25 And unto Eber were born two sons: the name of one was Peleg; for in his days was the earth divided; and his brother’s name was Joktan.

26 ዮቅጣንም ኤልሞዳድን፥ ሣሌፍንም፥ ሐስረሞትንም፥

26 And Joktan begat Almodad, and Sheleph, and Hazarmaveth, and Jerah,

27 ያራሕንም፥ ሀዶራምንም፥ አውዛልንም፥

27 And Hadoram, and Uzal, and Diklah,

28 ደቅላንም፥ ዖባልንም፥ አቢማኤልንም፥

28 And Obal, and Abimael, and Sheba,

29 ሳባንም፥ ኦፊርንም፥ ኤውላጥንም፥ ዩባብንም ወለደ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ልጆች ናቸው።

29 And Ophir, and Havilah, and Jobab: all these were the sons of Joktan.

30 ስፍራቸውም ከማሴ አንሥቶ ወደ ስፋር ሲል እስከ ምሥራቅ ተራራ ድረስ ነው።

30 And their dwelling was from Mesha, as thou goest unto Sephar a mount of the east.

31 የሴም ልጆች በየነገዳቸውና በየቋንቋቸው፥ በየምድራቸውና በየሕዝባቸው እነዚህ ናቸው።

31 These are the sons of Shem, after their families, after their tongues, in their lands, after their nations.

32 የኖኅ የልጆቹ ነገዶች እንደ ትውልዳቸው በየሕዝባቸው እነዚህ ናቸው። አሕዛብም ከጥፋት ውኃ በኋላ በምድር ላይ ከእነዚህ ተከፋፈሉ።

32 These are the families of the sons of Noah, after their generations, in their nations: and by these were the nations divided in the earth after the flood.